Wednesday, October 4, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ፔትሮ ቻይና የበጀት ዓመቱን የነዳጅ ግዥ ጨረታ አሸነፈ

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ለ2011-2012 በጀት ዓመት የሚቀርብ ነዳጅ ለመግዛት ያወጣውን ዓለም አቀፍ ጨረታ፣ ፔትሮ ቻይና የተሰኘ ኩባንያ እንዳሸነፈ ታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት 1.35 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ናፍጣ፣ 240,000 ሜትሪክ ቶን የአውሮፕላን ነዳጅና 350,000 ሜትሪክ ቶን ቤንዚን ለመግዛት እንደሚፈልግ በመግለጽ ዓለም አቀፍ ጨረታ በመስከረም 2011 ዓ.ም. ማውጣቱ ይታወሳል፡፡ የጨረታ ሰነዱን 36 ኩባንያዎች የገዙ ቢሆንም የቴክኒክና ፋይናንስ ዕቅዳቸውን አሟልተው ለጨረታ ኮሚቴው ያስገቡት ትራፊጉራ፣ ፔትሮ ቻይናና ቪቶል ኦይል የተባሉ ኩባንያዎች ብቻ እንደሆኑ፣ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታደሰ ኃይለ ማርያም ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

አቶ ታደሰ ጨረታው ጥቅምት 29 ቀን 2011 ዓ.ም. መከፈቱን ገልጸው፣ የጨረታ ኮሚቴው የተጫራቾቹን ኩባንያዎች የቴክኒክ ዕቅድ ሲገመግም እንደቆየ ተናግረዋል፡፡

ሦስቱም ኩባንያዎች የቴክኒክ ግምገማውን ማለፋቸውን የገለጹት አቶ ታደሰ፣ የፋይናንስ ጨረታው ረቡዕ ኅዳር 12 ቀን 2011 ዓ.ም. መከፈቱን አስረድተዋል፡፡ የጨረታው ውጤት ወዲያውኑ መታወቅ የነበረበት ቢሆንም ኩባንያዎቹ ያቀረቡት ዋጋ በጂቡቲና በኤርትራ ወደቦች በመሆኑ አማካይ የዋጋ ሥሌት መሥራት በማስፈለጉ አሸናፊ ተጫራች እንዳልተገለጸ አቶ ታደሰ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ትንሽ የፋይናንስ ትንተና መሠራት ስላለበት ውጤቱን በመጪው ሳምንት እናሳውቃለን፤›› ብለዋል፡፡

እሳቸው ይህን ቢሉም ምንጮች ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ከሦስቱ ኩባንያዎች ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ፔትሮ ቻይና ነው፡፡ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የተወሰነ መጠን ነዳጅ በአሰብ ወደብ ለማስገባት በማሰብ ተጫራች ኩባንያዎች የሚያቀርቡት ዋጋ በጂቡቲና በአሰብ ወደቦች እንዲሆን በጠየቀው መሠረት፣ ኩባንያዎቹ አማራጭ ዋጋ እንዳቀረቡ ታውቋል፡፡

ፔትሮ ቻይና ለኢትዮጵያ አዲስ ኩባንያ አይደለም፡፡ በ2009 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት ያወጣውን ጨረታ በማሸነፍ የ2009-2010 ዓ.ም. ነዳጅ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች