Sunday, June 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናደኢሕዴን ከጠቅላላ ጉባዔ አቅጣጫ በማፈንገጥ ዞኖች ክልልነትን እያፀደቁ ነው አለ

ደኢሕዴን ከጠቅላላ ጉባዔ አቅጣጫ በማፈንገጥ ዞኖች ክልልነትን እያፀደቁ ነው አለ

ቀን:

የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) በደቡብ ክልል የሚስተዋለው የዞኖች የክልልነት ጥያቄን በዞን ምክር ቤቶች የማፅደቅ ተግባር ሕገ መንግሥታዊ ቢሆንም፣ ድርጅቱ በአሥረኛ ጉባዔው ካስቀመጠው አቅጣጫ ውጪ ነው አለ፡፡

ድርጅቱ ይኼንን ያለው ሰኞ ኅዳር 17 ቀን 2011 ዓ.ም. ያካሄደው አስቸኳይ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ሲጠናቀቅ ነው፡፡

የድርጅቱ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ከስብሰባው በኋላ በሰጡት መግለጫ፣ ውሳኔዎች ለአፈጻጸም አስቸጋሪ በሆነ መንገድ እየተላለፉ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

- Advertisement -

የደኢሕዴን ጉባዔ ከኢሕአዴግ 11ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ አንድ ቀን ቀደም ብሎ መስከረም 22 ቀን 2011 ዓ.ም. ሲጠናቀቅ፣ በክልሉ ለረዥም ጊዜ ሲንከባለሉ የመጡ የሕዝብ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጣቸውና የልማት ተጠቃሚነት ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችም በአዲስ አደረጃጀቶች እንዲፈቱ አቅጣጫ ማስያዝን አስታውቆ ነበር፡፡

ለዚህም አፈጻጸም የተለያዩ ኮሚቴዎች ሲዋቀሩ፣ የክልሉ መንግሥትም የልማትና የመሠረተ ልማት ጥያቄዎችን መመለስ የሚያስችሉ መፍትሔዎችን ለመስጠት ጥናት እያደረገ መሆኑን፣ ካሁን በፊት ከሪፖርተር ጋር ቆይታ ያደረጉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

ይሁንና በሐምሌ 2010 ዓ.ም. በዞኑ ምክር ቤት ፀድቆና በክልል ምክር ቤት ከወር በፊት ተቀባይነትን በማግኘት ሕዝበ ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ የሚገኘው የሲዳማ የክልልነት ጥያቄን ተከትሎ፣ በርካታ የክልሉ ዞኖች በዞን ምክር ቤቶች ደረጃ የክልልነት ጥያቄን እያፀደቁ ይገኛሉ፡፡ እስካሁንም ወላይታ፣ ካፋና ጉራጌ ዞኖች የክልልነት ጥያቄዎችን ያፀደቁ ሲሆን፣ በሌሎች ዞኖችም በተለያዩ ጊዜያት በሚስተዋሉ ሠልፎች ተመሳሳይ ሐሳቦች ሲንፀባረቁ ይስተዋላል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የሐዲያ ዞን አንዱ ነው፡፡

እነዚህን ጥያቄዎች ለማስተናገድ ዝርዝር ጥናት መደረግ እንዳለበትና ሕዝቡን ያሳተፈ ሥራ መከናወን አለበት የሚሉት የድርጅቱ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ ለዚህ የሚያግዝ የጥናት ቡድንም ተቋቁሟል ብለዋል፡፡ ጥያቄዎቹም ለሕዝቡ ይጠቅማሉ ወይ የሚለው በጥናቱ ከተመለሰ በኋላ፣ የመፍትሔ ሐሳብ በማቅረብ መፈጸም እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡

ምንም እንኳን ድርጅቱ ይኼንን ቢልም የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 47 ሁሉም ብሔሮች በፈለጉ ጊዜ ክልል የመመሥረት መብት የሚሰጥ ሲሆን፣ ይህ በብሔሩ ምክር ቤት ሁለት ሦስተኛ ድምፅ ሲደገፍና ለክልል ምክር ቤት በጽሑፍ ጥያቄ ሲቀርብ በአንድ ዓመት ውስጥ እንዲፈጸም ይደነግጋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...