ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ ከአገር አቀፍና ክልላዊ እንዲሁም በቅርቡ ከባህር ማዶ ከመጡ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት የተናገሩት፡፡ ኅዳር 18 ቀን 2011 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አዳራሽ በተዘጋጀው መድረክ፣ የውይይት መነሻ ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለከርሞ በሚጠበቀው አገራዊ ምርጫ የሚኖረውን የጨዋታ ሕግ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር አብሮ ማዘጋጀት፣ ለሚገኘው ውጤትም ተገዢ መሆን አስፈላጊነቱን ጠቁመዋል።