Friday, June 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልለግብርና ሳይንቲስቱ ስሜ ደበላ የተሠራው ዘጋቢ ፊልም

ለግብርና ሳይንቲስቱ ስሜ ደበላ የተሠራው ዘጋቢ ፊልም

ቀን:

የኤርትራ ጉዳይ በኦድዮ ሲዲ

በግብርና ምርምር ዘርፍ ትልቅ ሚና ካበረከቱት አንዱ የግብርና ሳይንቲስቱ ስሜ ደበላ (ዶ/ር) ናቸው፡፡ ተወዳጅ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን የኚህን የአገር ባለውለታ ሕይወት ታሪክ ሥራ የሚዘክር የ47 ደቂቃ ዘጋቢ ፊልም አዘጋጅቷል፡፡  የዘጋቢ ፊልሙ ዋና አዘጋጅ ዕዝራ እጅጉ እንደገለጸው፣ ከሳይንቲስቱ ቤተሰቦች ጋር በመሆን የተሠራው ዘጋቢ ፊልም የልጅነት፣ የትምህርት፣ የሥራ፣ የምርምር እንዲሁም የቤተሰብ ሕይወት ይዳስሳል፡፡

በቢራ ገብስ ላይ ምርምር ያደረጉት ዶ/ር ስሜ ገጸ ታሪካቸው እንደሚያሳየው፣ ከአራት አሠርታት በፊት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምክትል ኮሚሽነር ነበሩ፡፡  የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩትንም ከምሥረታ አንስቶ ያደራጁና ለስድስት ዓመታት ማዕከሉን በዋና የሥራ መሪነትም አገልግለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዴሚ እንዲመሠረት ከሐሳብ አመንጪዎቹ አንዱም የነበሩት ዶክተሩ ሕይወታቸው ከማለፉ በፊት በድምፅና በምስል ያስቀመጧቸው ሰነዶች በዘጋቢ ፊልሙ ውስጥ መካተታቸው ተገልጿል፡፡

ዘጋቢ ፊልሙ ኅዳር 13 ቀን 2011 ዓ.ም. በግብርና ምርምር ተቋም ለቀድሞ ባልደረቦቻቸውና ለተመራማሪዎች ለዕይታ መብቃቱንና ከወራት በኋላ በዲቪዲና በኦዲዮ ሲዲ ታትሞ እንደሚሰራጭ አዘጋጁ ገልጿል፡፡

በተያያዘ ዜና ተወዳጅ ሚድያና ኮሚኒኬሽን (ተሚኮ) በኦድዮ ሲዲ ያዘጋጀው የአቶ ዘውዴ ረታ ‹‹የኤርትራ ጉዳይ›› መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ኅዳር 15 ቀን ረፋድ ላይ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ተመርቋል፡፡ በ1992 ዓ.ም. የታተመው ግዙፍ መጽሐፍ 26 ሰዓታት በተፈሪ ዓለሙ ተተርኮ በአንድ ዲቪዲ የቀረበውን በዋናነት ያዘጋጀው ዕዝራ እጅጉ ሲሆን፣ ከመጽሐፉ ደራሲ ዘውዴ ረታ ቤተሰቦች ጋር በመተባበር መታተሙን ተሚኮ አስታውቋል፡፡ በዕለቱ የተውኔቱ አበበ ባልቻ ከመጽሐፉ ገጾች የተቀነጨቡትን አንብቧል፡፡

በኦድዮ ቡክ ምረቃው ዕለት ‹‹የኤርትራ ጉዳይ›› በሚል ርዕስ የ14 ደቂቃ ምጥን ዘጋቢ ሲቀርብ፤ በኢሳያስ አስራት ተደርሶ  በሚሊዮን ጸጋዬ የተተወነው ‹‹የብርቱ ሰው ወግ›› ባለ አንድ ሰው ተውኔትም ለዕይታ በቅቷል፡፡  ተውኔቱ ጸሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ ኤርትራን ከኢትዮጵያ ጋር ለመቀላቀል ያደረጉትን እልህ አስጨራሽ ትግል የሚያሳይ ነው፡፡ ተሚኮ ባለፉት ሁለት ዓመታት 13 ባለውለታዎችን ታሪክ በኦድዮና በዲቪዲ ማሳተሙንም ገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...