Saturday, June 10, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልየአፍሪካ ምርጥ አልበም ክብርን ከሦስት ሽልማቶች ጋር የተቀዳጀችው ቤቲ ጂ

የአፍሪካ ምርጥ አልበም ክብርን ከሦስት ሽልማቶች ጋር የተቀዳጀችው ቤቲ ጂ

ቀን:

በጋና መዲና አክራ በተከናወነው የመላ አፍሪካ የሙዚቃ ሽልማት (አፍሪማ) ኢትዮጵያዊቷ ድምፃዊት ብሩክታዊት ጌታሁን (ቤቲ ጂ) በሦስት ዘርፎች አሸንፋለች፡፡

ባለፈው ቅዳሜ ኅዳር 15 ቀን 2011 ዓ.ም. ምሽት ለአምስተኛ ጊዜ በተደረገው የአፍሪካ ማድረክ ለክብር ከበቁት መካከል ቤቲ ጂ የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ አልበም እንዲሁም የምሥራቅ አፍሪካ ምርጥ ሴት አርቲስት በመሰኘት ገዝፋ ታይታለች፡፡ በተጨማሪም የአፍሪካ ተስፋ የተጣለባት ምርት አርቲስት ዘፈንም ጨብጣለች፡፡

ድምፃዊት ቤቲ የዓመቱን ምርጥ አልበም ሽልማቷ በ‹‹ወገግታ›› አልበሟ፣ የምሥራቅ አፍሪካ ምርጥ ሴት አርቲስት ሽልማትን በ‹‹መንገደኛ›› በሚለው  ሥራዋ ስታሸንፍ፤ ደግሞ ‹‹ኧረ ማነው?›› በሚለው ሙዚቃዋ ደግሞ ተስፋ የተጣለባቸው በሚለው   አግኝታለች፡፡

ቤቲ ጂ ሦስቱን ሽልማቶቿን ከተቀበለች በኋላ በማኅበራዊ ገጿ ‹‹ድምፅ በመስጠት ላገዛችሁኝ አድናቂዎቼ ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው፤›› ብላለች፡፡

‹‹ሽልማቱ የመጀመርያ እንጂመጨረሻ አይደለም›› ያለችው ቤቲ ጂ ‹‹ኢትዮጵያን ወክዬ ስቆም አኮራችሁኝ፤ ከጎኔ ነበራችሁ፤ አንድ ላይ ሆነን የአገራችንን ስም እናስጠራለን›› በማለት ከጎኗ ለቆሙ ሁሉ ምስጋናዋን ሳታቀርብ አላለፈችም፡፡

ሚዩዚክ አፍሪካ በድረ ገጹ እንደዘገበው፣ ቤቲ ለዘንድሮው የአፍሪካ 2018 ውድድር ካሸነፈችባቸው ሦስቱ ዘርፎች በተጨማሪ በሌሎች ሦስት ዘርፎች ማለትም በምርጥ የአፍሪካ ጃዝ አርቲስት፣ ምርጥ የአፍሪካ ሮክና የዓመቱ ምርጥ አርቲስት ዘርፎች ተወዳድራ ነበር፡፡

ከሦስት ዓመት በፊት በተከናወነው የአፍሪማ 2015 ሽልማት ድምፃዊት ፀደኒያ ገብረ ማርቆስ ‹‹የት ብዬ›› በሚለው ሥራዋ ምርጥ የምሥራቅ አፍሪካ ሴት አርቲስት ክብርን መቀዳጀቷ ይታወሳል፡፡

ሃቻምና በተካሄደው የአፍሪካ 2016 ሽልማት ሔኖክና መሐሪ ብራዘርስ ‹‹እወድሻለሁ›› በሚለው ሥራቸው በምርጥ የአፍሪካ ኣር ኤንቢ እና ሶል ዘርፍ ማሸነፋቸው፣ በዓምናው የአፍሪማ 2017 ሽልማት፣ ሐመልማል አባተ ‹‹ሐረር›› በሚለው ሥራዋ በአፍሪካ ትራዲሽናል ምርጥ አርቲስት ተብላ ማሸነፏ አይዘነጋም፡፡

በቅዳሜ ምሽቱ መድረክ ለሽልማት የበቁት በሥራ ላይ ያሉት አርቲስቶች ብቻ አይደሉም፡፡ ለነባር ሙዚቀኞችና የቡድን መሪ እንዲሁም ለአገር ገዢ ክብርን ሰጥቷል፡፡ ሁለቱ አንጋፋዎች ከደቡብ አፍሪካ ዩቮኔ ቻካ ቻካና እ.ኤ.አ. በ1969 የተመሠረተው የኦሳዴቢ ቡድን መሪ የነበረው የጋናው ቴዲ አሴይ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

ለሦስት አሠርታት በሙዚቃው ዓለም ጉዞዋ በርካታ አልበሞችን ያወጣችው ቻካ ቻካ የአምስተኛው አፍሪማ በኩል ተሻለሚ (ሌጀንደሪ አዋርድ) ክብርን አግኝታለች፡፡

የሌጎስ አገረ ገዢው አኪንውኑሚ አምቦዴ በሌጎስ ግዛት ኪነ ጥበብና ቱሪዝም እንዲስፋፋና እንዲያድግ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ልዩ ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡ አገረ ገዢው በተለይ የሚጠቀስላቸው ዐቢይ ተግባራቸው እ.ኤ.አ. ከ2014 እስከ 2017 የተደረጉትን የአፍሪማ መድረኮች በማስተናገዳቸው ነው፡፡

የመላው አፍሪካ ሙዚቃ ሽልማቶች (All Africa Music Awards) በምሕፃሩ አፍሪማ እ.ኤ.አ. በ2014 የተመሠረተ ሲሆን፣  ዓመታዊ መሰናዶውን  ከአፍሪካ ኅብረት ጋር በመተባበር ያዘጋጃል፡፡

በሙዚቃ ሥራዎቻቸው፣ በተሰጥኦቸው በፈጠራቸው የላቁትን አፍሪካውያን በማክበር የአፍሪካን ባህላዊ ቅርስ ለማስተዋወቅ መመሥረቱ ይወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አያሌ የውኃ “ጠርሙሶች”ን በጫንቃ

መሰንበቻውን በአይቮሪ ኮስት መዲና አቢጃን የምትኖር አንዲት ሴት፣ በሚደንቅ...

ወልቃይትን ማዕከል ያደረገው የምዕራባዊያን ጫና

በትግራይ ክልል የተከሰተው የዕርዳታ እህል ዘረፋ የዓለም አቀፍ ተቋማት...

ከቀጣዩ ዓመት በጀት ውስጥ 281 ቢሊዮን ብሩ የበጀት ጉደለት ነው ተባለ

ለቀጣዩ በጀት ዓመት ከቀረበው 801.65 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ በጀት...