Thursday, June 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ሥነ ፍጥረትአምባራይሌ

አምባራይሌ

ቀን:

አምባራይሌ አጠቃላይ ቁመናው ከቀንዱ ጥምዝ ጋር የአጋዘን ይመስላል፡፡ በመጠኑ ግን አነሰ ያለ ነው፡፡ የወንዱ ክብደት ከ92 እስከ 108 ኪሎ ግራም፣ የሴቶቹ ደግሞ ከ56 እስከ 70 ኪሎ ግራም ይሆናል፡፡ ሴቶቹና ወጣቶቹ የቀይ ቡኒ ሲሆኑ፣ ወንዶቹ ደግሞ ሰማያዊ የመሰለ ግራጫ ናቸው፡፡ ይህም ቀለማቸው ዕድሜአቸው እየገፋ ሲሄድ እየጠቆረ ይሄዳል፡፡ ጐላ ብለው የሚታዩ ነጫጭ መስመሮች ከጀርባቸው ወደ ደረትና ሆዳቸው ይዘልቃሉ፡፡ ጫፉ ቁር የሆነ ጐፈሬም ጭራ አላቸው፡፡ ቀንድ ያላቸው ወንዶቹ ብቻ ናቸው፡፡ ሁለት ተኩል ጥምዝ ያለው ቀንድ አላቸው፡፡ ደረትና ሆዳቸው ነጣ ያለ ነው፡፡  በኢትዮጵያና በሶማሊያ፣ በኬንያና በታንዛኒያ ብቻ ይገኛሉ፡፡ የሚኖሩት ከባሕር ወለል በላይ፣ ከ1200 ሜትር ከፍታ በታች በሆኑ ቦታዎች ነው፡፡ እንዲህ ያለውም አካባቢ የግራርና የቆላ አባሎ (Commiphora) ዛፎች ያሉበት ነው፡፡

  • ሰለሞን ይርጋ (ዶ/ር) ‹‹አጥቢዎች›› (2000)       
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ከቀጣዩ ዓመት በጀት ውስጥ 281 ቢሊዮን ብሩ የበጀት ጉደለት ነው ተባለ

ለቀጣዩ በጀት ዓመት ከቀረበው 801.65 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ በጀት...

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከተለመደው አሠራር ወጣ ያለውን ‹‹የወደፊት ግብይት›› ሥርዓት በይፋ አስጀመረ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከተለመደው የማገበያየት ተግባሩ ወጣ ያለና በኢትዮጵያ...

የባንክ ማቋቋሚያ መሥፈርት እንደሚጠነክር ሚኒስትሩ ተናገሩ

 ባንኮች ስለውህደት እንዲያስቡም መክረዋል በኢትዮጵያ ውስጥ ባንክ ለማቋቋም የሚያስፈልገው መሥፈርት...