Sunday, July 14, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየተራዘመውን የሕዝብና የቤቶች ቆጠራ በመጋቢት ወር መጨረሻ ላይ ለማድረግ ዝግጅት ተጀመረ

የተራዘመውን የሕዝብና የቤቶች ቆጠራ በመጋቢት ወር መጨረሻ ላይ ለማድረግ ዝግጅት ተጀመረ

ቀን:

አራተኛውን የሕዝብና የቤቶች ቆጠራ በመጋቢት ወር መጨረሻ ላይ ለማድረግ እንቅስቃሴዎች ተጀመሩ፡፡ መንግሥት ግን ማረጋገጫ እንዳልሰጠ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በዋናነት በማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሥር ያሉ የተለያዩ የሥራ ዘርፎች ለቆጠራው ዝግጅት እንዲያደርጉ እንደተነገራቸው የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ኅዳር ወር 2010 ዓ.ም. መደረግ የነበረበት የሕዝብና የቤቶች ቆጠራ በፀጥታ ምክንያቶች በተለይም በሶማሌና ኦሮሚያ ክልሎች በነበሩ ግጭቶችና የሕዝቦች መፈናቀል፣ እንዲሁም በተጓተቱ ግዥዎች ምክንያት በታቀደው ጊዜ ሳይከናወን መቅረቱ ይታወሳል፡፡ በዚህም ምክንያት ቆጠራው በፓርላማ በፀደቀ ውሳኔ መሠረት ለ2011 ዓ.ም. መተላለፉ ይታወሳል፡፡

ይሁንና ባለፈው ሳምንት የተለያዩ ውይይቶች ከተካሄዱ በኋላ፣ ቆጠራው መጋቢት 29 ቀን 2011 ዓ.ም. እንደሚደረግ ስምምነት ላይ መደረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በውይይቶችም እስካሁን ድረስ በተለያዩ አካባቢዎች የሚቀሰቀሱ ግጭቶችና ያልቆመው የዜጎች መፈናቀል በቆጠራው ላይ ተፅዕኖ ማሳደራቸው እንደማይቀር፣ መንግሥትም ፖለቲካዊ ውሳኔ እንደሚሰጥ መግባባት ላይ መደረሱን አንድ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የኤጀንሲው የሥራ ኃላፊ ገልጸዋል፡፡

መጋቢት 29 ቀን 2011 ዓ.ም. ቆጠራው መካሄድ ይጀምራል በሚለው ላይ መቶ በመቶ ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ማረጋገጫ ገና እንዳልተሰጠና የመንግሥት ውሳኔ እየጠበቀ እንደሆነ፣ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢራቱ ይገዙ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሚዲያው በሕዝብ የህሊና ችሎት ከተዳኘ በቂ ነው!

መሰንበቻውን ድንገት ሳይታሰብ ያለ ማስጠንቀቂያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ...

የባህር በር ጉዳይ

በታምሩ ወንድም አገኘሁ ድሮ ድሮ ገና ልጅ ሆኜ ፊደል እንደቆጠርኩ...

አገሩ ፖለቲካዊ ስክነትና መደማማጥ ያስፈልገዋል

በንጉሥ ወዳጀነው    ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ ቤት ነች፡፡ ‹‹ጥያቄዬ ተመለሰልኝ››፣...

የመንግሥት የሰብዓዊ መብት ተቋም ለምን የመንግሥት ሚዲያን ማስተማር አቃተው

በገነት ዓለሙ የአገራችን የ2016 የበጀት ዓመት መሰናበቻና የአዲሱ የ2017 በጀት...