‹‹የአንኮበሩ ሰው በጄኔቫ›› የተሰኘውና በአማርኛና በእንግሊዝኛ የተዘጋጀው ግለ ታሪክ እሑድ ታኅሣሥ 7 ቀን 2011 ዓ.ም. በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ይመረቃል፡፡ ግለ ታሪኩ ከአራት አሠርታት በላይ በጄኔቫ ስዊዘርላንድ የኖሩና የሠሩት የኢንጂነር ተረፈ ራስወርቅ ሲሆን፣ መጽሐፉ በዓለም አቀፋዊ ሥራ ተሰማርተው ከ70 በላይ አገሮችን ተዘዋውረውና ያዩትን የሕይወትና የሥራ ተሞክሯቸውን ይዟል፡፡ ባለ 400 ገጹ ግለ ታሪክ ዋጋው 200 ብር መሆኑን የዝግጅቱ አስተባባሪ ተወዳጅ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን አስታውቋል፡፡