Thursday, December 7, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየህዳሴው ግድብ 750 ሜጋ ዋት የቅድመ ማመንጨት ሥራ ከሁለት ዓመት በኋላ ይጀምራል...

የህዳሴው ግድብ 750 ሜጋ ዋት የቅድመ ማመንጨት ሥራ ከሁለት ዓመት በኋላ ይጀምራል ተባለ

ቀን:

የግድቡ ሥራ በአራት ዓመታት ይጠናቀቃል ተብሏል

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሥራ ማስተካከያዎች ተደርገውበት ከሁለት ዓመታት በኋላ 750 ሜጋ ዋት የቅድመ ኃይል ማመንጨት ሥራ እንደሚጀምር የግድቡ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ገለጹ።

የጥራትና የጊዜ መጓተት ችግሮች በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) በኩል በተፈጠሩ ግድፈቶች ሳቢያ ይጠናቀቃል ከተባለውም ጊዜ ዘግይቶ በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ የግድቡ ግንባታ 65 በመቶ ላይ ይገኛል። በሜቴክ እንዲገነቡ ውል የተገባባቸው የብረት መዋቅርና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎች መጓተትና የጥራት ጉድለቶች የግድቡን ግንባታ ሥራ በተቀመጠለት ጊዜ እንዳይካሄድ አድርጓል ያሉት የግድቡ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ተክሌ ሆሮ (ኢንጂነር) በኤሌክትሮ ሜካኒካልና መሰል ሥራዎች ተስተካክለው በሁለት ዓመታት ውስጥ የመጀመርያው ምዕራፍ ግንባታ እንደሚጠናቀቅም ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል። በጠቅላላው የግድቡ ግንባታ ሥራ በአራት ዓመታት ውስጥ እንደሚጠናቀቅም አስታውቀዋል።

ግድቡ የሚገኝበትን የግንባታ ሒደትና ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ በተጠራው የውይይት መድረክ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) በበኩላቸው ምንም እንኳ የግድቡ የሲቪል ሥራዎች 82 በመቶ ቢጠናቀቅም፣ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎቹ 23 በመቶ ብቻ በመከናወኑ ጠቅላላ ድምር አፈጻጸሙን 65 በመቶ ላይ ገድቦት ቆይቷል።

በመሆኑም ላለፉት ሰባት ዓመታት በግንባታ ላይ የሚገኘውና አራት ዓመታት የተጓተተው የህዳሴው ግድብ ሌላ አራት ዓመታት ይፈልጋል። እስካሁን ከ98 ቢሊዮን ብር በላይ ቢወጣበትም ለማጠናቀቅ የሚጠይቀው ተጨማሪ ገንዘብ ገና በቅርብ ጊዜ ውስጥ ይፋ ይደረጋል ተብሏል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...