ጅማ ዩኒቨርሲቲ ኅዳር 29 ቀን 2011 ዓ.ም. ከ1,200 በላይ የሕክምና ዶክተሮችን ሲስመርቅ አዲሱ ነገር መራቂዎቹ የአፍሪካ ቀንድ ሦስት መሪዎች መሆናቸው ነው፡፡ በምርቃትቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ የጂቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ዑመር ጊሌህ፣ እንዲሁም የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር ተገኝተው የእንኳን ደስ አላችሁ ንግግር ሲያደርጉ በተለይ ፕሬዚዳንት አልበሽር ደግሞ ለአሥር ተማሪዎች የውጭ አገር ትምህርት ዕድል በነፃ ሰጥተዋል፡፡