Friday, September 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናሦስት የመንግሥት ሚዲያ ተቋማት የፈረሰውን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች ተረከቡ

ሦስት የመንግሥት ሚዲያ ተቋማት የፈረሰውን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች ተረከቡ

ቀን:

ሦስት የመንግሥት ሚዲያ ተቋማት በቅርቡ የፈረሰውን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት 180 ሠራተኞች ተረክበው በተለያዩ የሥራ መደቦች መመደባቸው ታወቀ፡፡

ሪፖርተር ከምንጮች ማወቅ እንደቻለው ሠራተኞቹ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ)፣ በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) እና በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በተለያዩ የሥራ ክፍሎች ከታኅሳስ 1 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ተመድበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ባዋቀሩት አዲስ ካቢኔ፣ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት እንዲፈርስ ተደርጎ፣ በምትኩ በጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ውስጥ የፕሬስ ሴክሬታሪያት መቋቋሙ ይታወሳል፡፡

ለቀድሞው የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ተሰጥቶት የነበረው ሥልጣንና ኃላፊነት ወደ አዲሱ ፕሬስ ሴክሬታሪ የተላለፈ ሲሆን፣ ከጥቂት ሠራተኞች በስተቀር 180 ሠራተኞች በሦስቱ የሚዲያ ተቋማት እንዲመደቡ መደረጉን ከሠራተኞችና ከሚዲያ ተቋማቱ ኃላፊዎች ለማወቅ ተችሏል፡፡

በዚህም መሠረት ኢዜአ 67 ሠራተኞችን መረከቡ ሲታወቅ፣ የፕሬስ ድርጅት እንዲሁ 57 ሠራተኞችን ተረክቧል፡፡ ኢቢሲ በበኩሉ 56 ሠራተኞችን መቀበሉን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

የሠራተኞቹ ዝውውር በምን መሥፈርት እንደተካሄደ ለማወቅ ባይቻልም፣ ከምደባ ውሳኔው ጋር የሠራተኞቹ በጀትም ወደ ተዛወሩባቸው ተቋማት ተዘዋውሯል ተብሏል፡፡

ምንጮች ቁጥራቸውን ባይገልጹም የተወሰኑ ሠራተኞች ግን ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ተዛውረው በፕሬስ ሴክሬታሪያቱ ሥር ሥራ ጀምረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...