Sunday, September 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለቀበሌ ቤቶች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ሊዘጋጅ ነው

ለቀበሌ ቤቶች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ሊዘጋጅ ነው

ቀን:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ የጀመረውን የቀበሌ ቤቶች ቆጠራ አጠናቆ፣ የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ እንዲሰጠው አመለከተ፡፡ የቤቶች አስተዳደር ኤጀንሲ ባለፈው ዓመት በጀመረው ቆጠራ በተለይ በመሀል አዲስ አበባ በቂርቆስ፣ በአራዳ፣ በአዲስ ከተማ፣ በልደታና በጉለሌ ክፍላተ ከተሞች 140 ሺሕ ቤቶች፣ የማስፋፊያ ክፍላተ ከተሞች በሆኑት ቦሌ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ የካና ንፋስ ስክል ላፍቶ ክፍላተ ከተሞች ከሚገኙት ጋር በጠቅላላው 158 ሺሕ ቤቶች እንዳሉት በመጀመርያው ዙር ጥናት ማረጋገጡ ታውቋል፡፡

ለእነዚህ የቀበሌ ቤቶች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንዲሰጠው በአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ሥር ለሚገኘው የይዞታ አስተዳደር የሽግግር ጊዜ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት አመልክቷል፡፡ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ ከታኅሳስ ወር 2011 ዓ.ም. ጀምሮ በሚቀጥሉት አምስት ወራት ካርታውን አዘጋጅቶ እንደሚያስረክብ ተገልጿል፡፡

ይኼንን ሥራ በጋራ ለማካሄድ ስምምነት ላይ መደረሱ ታውቋል፡፡ የስምምነቱ ተሳታፊ የሚሆኑት የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ፣ የይዞታ አስተዳደር የሽግግር ጊዜ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት፣ እንዲሁም ባለቤት የሆነው የቤቶች አስተዳደር ኤጀንሲ ናቸው ተብሏል፡፡

ኤጀንሲው ባካሄደው ቆጠራ ምን ያህል ቤቶች እንዳሉት ከማወቅ በተጨማሪ በሕገወጥ መንገድ የተያዙ፣ ከግለሰብ ይዞታ ጋር የተቀላቀሉ፣ ጭራሽ ደግሞ ወደ ግል ንብረትነት በሕገወጥ መንገድ የዞሩ ቤቶች እንዳሉት አውቋል፡፡ ኤጀንሲው የሚያስተዳድራቸውን የቀበሌ ቤቶች ካርታ በስሙ የሚያሠራ ሲሆን፣ ተከራይተው የሚገለገሉ ለሥራው መቃናት መተባበር ይኖርባቸዋል ተብሏል፡፡

በሕገወጦች የተያዙ ቤቶች ላይ የማስተካከያ ዕርምጃ እንደሚወሰድ ከኤጀንሲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ በ1996 ዓ.ም. ባካሄደው ጥናት፣ በከተማው በአጠቃላይ  384 ሺሕ ቤቶች ነበሩ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹን ቁጥር የሸፈኑት የቀበሌ ቤቶች ናቸው፡፡

ነገር ግን በልማት ምክንያት በተለይ ከመሀል ከተማ በርካታ የቀበሌ ቤቶች የፈረሱ በመሆናቸውና ቆጠራም ባለመካሄዱ የመረጃ ክፍተት ነበረበት ተብሏል፡፡

 

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...