Sunday, April 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየተጠሪነት ወሰን ያልተበጀለት የኢትዮጵያ ስፖርት

የተጠሪነት ወሰን ያልተበጀለት የኢትዮጵያ ስፖርት

ቀን:

ሕጋዊ ሰውነት ኖሯቸው በመንቀሳቀስ ላይ ከሚገኙ መንግሥታዊ ተቋማት መካከል ስፖርቱ ይጠቀሳል፡፡ ዘርፉ በተለያየ አደረጃጀት መልክ ተጉዞ አሁን የደረሰበት ደረጃ ላይ ቢገኝም፣ ቅርፅ ያለው የተጠሪነት ወሰን ሳይበጅለት አንዴ ከባህል፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ከወጣትና ከሌሎችም ለስፖርቱ ቅርበት አላቸው ተብሎ ከሚታመንባቸው ተቋማት ጋር ሲጋባና ሲፋታ ዕድሜውን መግፋቱ፣ ዘርፉ ራሱን የቻለ ተቋማዊ ቅርፅ ብቻ ሳይሆን፣ ለተጠያቂነትና ግልጽነት እንዲሁም ለውጤታማነት በሩን ዘግቶ እንዲቆይ ምክንያት መሆኑን የሚያምኑ አሉ፡፡

አበው ‹‹በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ›› እንዲሉ ስፖርቱ በተለይም እግር ኳሱ በኅብረተሰቡ ዘንድ የቆየውን አብሮ የመኖር እሴት የሚያጠፋ፣ አለፍ ሲልም ለንብረትና ሕይወት መጥፋት ምክንያት መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡ ችግሩን መፍታትና ማስወገድ ይችላሉ ተብሎ የታመነባቸው የተለያዩ የውይይት መድረኮች ቢደረጉም፣ እስካሁን ባለው ያመጡት አንዳች ለውጥ እንደሌለ በይደር የተላለፈውን የፕሪሚየር ሊግ ዓመታዊ መርሐ ግብር በመመልከት መናገር ይቻላል፡፡

በአዲሱ የመንግሥት አስተዳደር በወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል የሚመራው የሰላም ሚኒስቴርና የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ታኅሣሥ 4 ቀን 2011 ዓ.ም. ‹‹ስፖርት ለሰላምና ብሔራዊ መግባባት›› በሚል ስድስት ኪሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ባህል ማዕከል በስፖርታዊ ጨዋነት ዙሪያ ስፖርት ኮሚሽኑን ጨምሮ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ውይይት ማድረጋቸው ታውቋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ውይይቱን አስመልክቶ በስፖርት ኮሚሽኑ ይፋዊ ድረ ገጽ እንደተገለጸው ከሆነ፣ በስፖርቱ ዘርፍ ውጤታማ ለመሆን መከናወን የሚገባቸው ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች እያሉ፣ ከእግር ኳሱ ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ አዝማሚያዎች ጥሩ እንዳልሆኑ ታይቷል፡፡ እንደሚታወቀው ስፖርት የዓለም ሕዝቦች ቋንቋ፣ የቆዳ ቀለምና ሃይማኖት ሳይገድባቸው በአንድ መድረክ የባህል እሴቶቻቸውን የሚለዋወጡበት ከመሆኑ ባሻገር ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ትልቅ እየሆነ መጥቷል፡፡

የዚህ አንድ አካል የሆነው የኢትዮጵያ ስፖርት፣ ዘርፉ ለሚያበረክተው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ባይታደልም፣ በስፖርቱ ማዘውተሪያዎች የሚታደሙ ዜጎች እርስ በእርስ ሊኖራቸው የሚገባው የሕይወት መስተጋብር ላይ መጥፎ አሻራውን ማሳረፍ እንደማይገባው ይታመናል፡፡ ይሁንና ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እግር ኳሳዊ የሆኑ ውድድሮች በተቃራኒው ሆነው ማዘውተሪያዎች የጠብ አወድማ እየሆኑ ለሰው ልጆች አካልና ንብረት መጥፋት ዓይነተኛ ምክንያት ሆነዋል፡፡

የዘርፉ ሙያተኞች ለዚህ መንስዔው ብለው እንደ መከራከሪያ የሚያቀርቡት፣ እግር ኳሱን ጨምሮ የአገሪቱ ስፖርት ሲመሠረት ግልጽ የሆነ የተጠሪነት ወሰን የሌለው መሆኑ፣ ይህ ደግሞ ዘርፉ በሚፈለገው ልክ ውጤታማ እንዳይሆን፣ ተጠያቂነትና ግልጽነት እንዲጠፋ፣ ሰዎች በፈለጉት ጊዜና ሰዓት ገብተው የፈለጉትን አድርገው እንዲወጡ የልብ ልብ መስጠቱን ይገልጻሉ፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ስፖርቱ ከወጣቶች ጋር በመሆን በሚኒስቴር ደረጃ እንደነበረ፣ አሁን ደግሞ በአዲሱ የመንግሥት አስተዳደር ኮሚሽን ሆኖ ተጠሪነቱ ለባህልና ቱሪዝም ሆኖ ሚኒስትር ዴኤታ እንዲኖረው ተደርጓል፡፡ ኮሚሽኑ ደግሞ በዋናና ምክትል ኮሚሽነሮች ይመራል፡፡

የዘፉን የተጠሪነት ወሰን አስመልክቶቶ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የኮሚሽኑ ሙያተኞች እንደሚገልጹት፣ ‹‹ስፖርቱ ከቀደሙት ዓመታት ጀምሮ ወጥና ግልጽ የሆነ የተጠሪነት ወሰን ኖሮት እንዲቀጥል አለመደረጉ ለሚገኝበት ውጥንቅጥ መንስዔ ነው፡፡ አዳዲስ የመንግሥት አስተዳደር በተዋቀረ ቁጥር የስፖርቱ አወቃቀርም እንደ አዲስ ይደራጃል፡፡ በዘርፉ እስካሁን ባለው የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ ዕቅድ አውጥቶ የፈጸመ፣ የገመገመና ያስፈጸመ አመራር የለም፡፡››

መንግሥት አሁን የጀመረውን ጊዜያዊ እሳት የማጥፋት ሥራ በመተው ለስፖርቱ ትክክለኛውን የመፍትሔ አቅጣጫ ማለትም ቆጥሮ የሰጠውን ቆጥሮ የሚረከብ ተቋም መፍጠር ያንንም የማስፈጸም ግዴታ እንዳለበት ጭምር ሙያተኞቹ ይናገራሉ፡፡ በተለይም የሌላ ሙያ ባለቤት የሆኑ የመንግሥት አካላት በስፖርቱ ያላቸው የወሳኝነት ሚና ያነሰ እንዲሆን ድርሻውን እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡ 

መንግሥት በክለብ ድጋፍ ስም እያቆጠቆጠ የመጣውን የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል አስመልክቶ አሁን እያደረገ ያውን እንቅስቃሴ ግን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ሙያተኞቹ ያምናሉ፡፡ በዚሁ መሠረት በሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚልና በባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ሒሩት ካሰው (ዶ/ር) መድረክ መሪነት የተደረገው የስፖርታዊ ጨዋነት ውይይት ወቅቱን የጠበቀ፣ ነገር ግን የውይይቱ ተፈጻሚነት ወደ መሬት የማውረዱ ሥራ ለነገ ሊባል እንደማይገባው ጠይቀዋል፡፡

በውይይቱ ክልሎችን ጨምሮ የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ አመራሮች፣ የኮሚሽኑ ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የፀጥታ ኃላፊዎችና ሌሎችም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት መሳተፋቸውን መግለጫው ያስረዳል፡፡ በዚህም ከስፖርታዊ ጨዋነት ጋር ተያይዞ በአማራና በትግራይ ክለቦች መካከል ተቋርጦ የነበረው የፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር በነበረው የተዟዙሮ ጨዋታ እንዲቀጥል የሁለቱ ክልሎች አመራሮችና የክለብ ኃላፊዎች ስምምነት ላይ መድረሳቸው ታውቋል፡፡

ስፖርቱን በበላይነት የሚያስተዳድረው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሒሩት (ዶ/ር) ለስፖርቱ ውጤታማነትም ሆነ አሳሳቢ እየሆነ ለመጣው ስፖርታዊ  ጨዋነት ከላይኛው መንግሥታዊ መዋቅር ጀምሮ በየደረጃው ኅብረተሰቡ፣ በዋናነት ደግሞ የስፖርት አመራሩ በጥምረትና በጋራ መሥራት እንደሚያስፈልግ መናገራቸው በመግለጫው ተካቷል፡፡

የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት በበኩላቸው፣ ‹‹ስፖርት አክብሮትንና ትብብርን ለማጠናከር ዓይነተኛ መሣሪያ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ በሕግ መመራቱ፣ በራሱ ቋንቋና መርህ መሠረት ዴሞክራሲን በራሱ መርህና መመርያ በመተዳደር ለስፖርቱ ብቻ ሳይሆን ለሰው ልጅ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር እምቅና ትልቅ አቅም ያለው መሣሪያ ነው፤›› ብለው፣ የስፖርቱን መልካም እሴት መጠበቅና ማስጠበቅ የእሳቸውን ተቋም ጨምሮ የእያንዳንዱ ድርሻ እንደሆነ ተናግረዋል ተብሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰው መሆን ምንድን ነው? ቅርስና ማኅበራዊ ፍትሕ (ክፍል አንድ)

በሱራፌል ወንድሙ (ዶ/ር) ዳራ ከጎራዎች፣ ከመፈራረጅ፣ ነገሮችን ከማቅለልና ከጊዜያዊ ማለባበስ ወጥተን...

ኢኮኖሚው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሳት ያሠጋል

በጌታቸው አስፋው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሱ የሚያሠጉኝ አንድ ሁለት ብዬ ልቆጥራቸው የምችላቸው...

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል በሕግ አምላክ ይላል

በገነት ዓለሙ የአገራችንን ሰላም፣ የመላውን ዓለም ሰላም ጭምር የሚፈታተነውና አደጋ...

በሽግግር ፍትሕ እንዲታዩ የታሰቡ የወንጀል ጉዳዮች በልዩ ፍርድ ቤት ሳይሆን በልዩ ችሎት እንዲታዩ ተወሰነ

የኤርትራ ወታደሮች በሌሉበትም ቢሆን ይዳኛሉ ተብሏል በፅዮን ታደሰ የሽግግር ፍትሕ የባለሙያዎች...