Thursday, May 30, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

እኔ የምለዉበኢትዮጵያ የጥምር ዜግነት አስፈላጊነትና መታወቅ የሚገባቸው ነጥቦች

በኢትዮጵያ የጥምር ዜግነት አስፈላጊነትና መታወቅ የሚገባቸው ነጥቦች

ቀን:

በፀጋዬ ደግነህ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያዊነትና የኢትዮጵያ ዜግነት

ባለንበት ዘመን አንድ ስም ትልቅ ትርጉም አለው። ሰው ምርትን ብቻ ሳይሆን የምርቱን ስምና (ብራንድ) የአገበያት ደስታንም አብሮ ይሸምታል። እንደ ጥንታውያን ግሪክ፣ ግብፅ፣ ጣያን ቻይናም ሁሉ የ ገር ሉሲ ኢትዮጵያ ስምም ሌሎች ያላገኙት ትልቅ ብራንድ ነው። ኢትዮጵያዊነት ማለትም የአኗኗር መገለጫ ፍልስፍናም ነው፡፡ ኢትዮጵያ የሚለው ስምም ለገር ከሚሰጠው ትርጉም በላይም ነው። ኢትዮጵያዊነትን ለማግኘት ሲባል ባህር አቋርጠው የሚፈልሱባት ምድር ነች። ኢትዮጵያ የተለያዩ ብረሰቦችን የያች፣ የተለያዩ አኩሪ ባህሎችና ድንቅ ቋንቋዎች ያላችው፣ ተቀራቢ የአኗናር፣ የአመጋብ፣ የኑሮ ደጃና ፈሊጥ ያላቸው ዜጎች በጋራ የሚኖሩባትና በጋራ የሚገነቧት ገር ነች። ኢትዮጵያ የሚለው ቃል የብዙ ሺ ዓመታት ዕድሜ ያስቆጠረ፣ ከእንግሊዝ፣ ጀርመን፣ አሜሪካ፣ ሩሲያ፣ ስፔን፣ ቱርክ፣ ናይጄሪያ፣ ብራ ወዘተ በፊት እስከነ ሥልጣኔው ይኖር የነበረ ሕዝብ መጠሪያ ነው፡፡ በዚህ ስም የሚጠሩ ሰዎች ተመሳሳይ መልክና ገጽ ያላቸው ከመሆናቸውም በላይከየትኛውም ብረሰብ ወይም ገሪቱ አካባቢ ቢ እንኳን በመተያየት ብቻ የሚተዋቁ የደም ዘመዳሞች ናቸው። ለምሳሌ ጥቁር አሜሪካውያን የፈለጉትን ያህል አሜሪካውያን ቢሆኑም አፍሪካ አሜሪካውያን በመባል ከአፍሪካ መምጣታቸው የማይካደውም ከዚህ ጋር በተመሳሰለ ምክንያት ነው። ኢትዮጵያውያ ከአገራቸው ተለይተው መኖር የሚከብዳችው፣ ቢቻላቸው ኢትዮጵያን በሚኖሩበት አገር አስመጥተው መኖር የሚፈልጉ ናቸው። የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳና ጠቅላይ ኒስትር ብይ አህመድ (ዶ/ር) በንግግራቸው እንዳሉትም ኢትዮጵያዊነት ሱስ ኖ የማይለቃው፣ ሲኖሩ በሁለንናዊው ኢትዮጵያ ሆነው ሲሞቱም ኢትዮጵያ የሚሆኑት እጅግ ብዙ ናቸው። የውጭ ዜግነትን የያዘ ሲሞት እንኳን ‹‹የኢትዮጵያ ዜግነቱን እንደተ ይቆጠራል›› ወደተባበት ኢትዮጵያ ሄዶ የኢትዮጵያ አፈር ይሆናል። ታዲያ እንዴት ነው አንድን ሰው የሌላ አገር ዜግነት በተጨማሪ በማግኘቱ ኢትዮጵያዊ አይደለህም የሚባለው?

- Advertisement -

በኢትዮጵያዊነትና በኢትዮጵያ ዜግነት መከል ልዩነት መኖሩን መገንዘብ ያስፈልጋል። ኢትዮጵያዊነት ከዜግነት፣ በኢትዮጵያ ከመኖር ወይም ፓስፖርት ከመያዝ ጋር አንድ አይደለም። ከዚያ በላይ ነውና። መጽፍ ቅዱስ ላይ ‹‹ነብር ዥንጉርጉርነቱን ኢትዮጵያዊ መልኩን ሊቀይር አይችልም›› እንደሚለው ይህም ለረዥም ዓመታት በትውልድ (በደም ግ) ሲዋረስ የመጣና ለግለሰቡም ማንነት (Identity) መገለጫ ስለሆነም ነው። ኢትዮጵያ የሚለው ስም በቅዱስ ቁርን የተጠቀሰና በሆሜር የተነገረ ነው። የታሪክ ተመራማሪዎች እዚህ ላይ ብዙ የተሻለ ነገር ሊሉ የሚችሉ ይመስለኛል። ኢትዮጵያዊነት የአንድ ግለሰብ ማንነት መገ ማለትም ባህሉን፣ ታሪኩን፣ ቋንቋውን፣ አስተሳሰቡን ወዘተ ተደርጎም ሊወሰድ ሲችል፣ የኢትዮጵያ ዜግነት ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ዜግነትን ለወሰዱ ሰዎች፣ የኢትዮጵያዊ ዜግነትን ይዘው በውጭ ለሚኖሩ መብታቸውን የሚጠብቅ፣ ግታቸውን የሚያስቀምጥ፣ ኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ ውጭ ያሉትንም ዜጎቼ የሚላቸውን ሁሉ በሕገ መንግቱ ጥላ ር የሚጠብቃቸው መሆኑን የሚገልጽ ነው። ዜግነት በአጠቃላይ ከአንድ መንግትና ዝብ ጋር የመብትና ግዴታ ውል አድርጎም ማየት ይቻላል። ቅድአያቶቻችን እኮ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ያስፈልጋችኋል ወይም ዜጋ ናችሁ ተብለው አይደለም ኢትዮጵያዊ የሆኑት (በጊዜው ይህ አራር ባይኖርም እንን)፣ ኢትዮጵያንም በደማቸው ጠብቀው ያስተላለፉት። የእነሱ ልጅ ልጆች የሌላ አገር ተጨማሪ ዜግነት በመውሰዳቸው ‹‹የኢትዮጵያ ዜግነታቸውን እንደተው ይቆጠራል›› መባሉ ሳይበቃ ኢትዮጵያዊ አይደሉም የሚለው በብዛት የሚሰማ አስተሳሰብ ግን ትክክል አይደም።

የኢትዮጵያ ሕገ መንግት አንቀጽ ስድስት ‹‹ወላጆቹ/ወላጆ ወይም ከወላጆቹ/ከወላጆ አንደኛው ኢትዮጵያዊ የሆነ/የሆነች የኢትዮጵያ ዜጋ ነው/ናት›› ይላል። ይኸው ነው። ስለኢትዮጵያ ዜግነት በ2003 ዓ.ም. የወጣው አዋጅም ስለ‹‹ኢትዮጵያዊነት›› ሳይሆን ስለኢትዮጵያ ዜግነት ነው የሚደነግገው። የሌላ ገር ዜግነትን በማግኘት የኢትዮጵያ ዜግነት የሚቀርበትንም በአንቀጽ 19 ሲደነግግ ዜግነቱን ለመተው መፈለጉን በማሳወቅ የዜግነት መልቀቂያ ምስር ወረቀት ይሰጠዋል ሲል አንቀ 20 ደግሞ በራሱ ፍላጎት የሌላ ገር ዜግነት ካገኘ ዜግነቱን በራሱ ፈቃድ እንደተወ ይቆጠራል ይላል። እነዚህ አንቀች ብዙ ሊያከራክሩ የሚችሉ ናችው።

ትውልደ ኢትዮጵያ

ትውልደ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያውያ ሙሉ የሚሆን መጠሪያ ነው። የሌላ ገር ዜግነት ለወሰዱ ብቻ መሆን የለበትም። የትውልኢትዮጵያ መታወቂያ አዋጅ (270/2002) በጣም ጥሩ ጅምር ነው። ጥሩ ተምሳሌት ነው። ቢሆንም በብዙ አገሮች እንደሚታየው የጥምር ዜግነትን መፍቀድ ብዙ ጥቅም አለው። በጀርመን ቋሚ መቆያ ፈቃድ ያለው የውጭ ገር ዜጋ ልክ ኢትዮጵያ ስጥ የትውልደ ኢትዮጵያ  መታወቂያ የሚሰጠውን ያህል መብት አለው። በዚህ ‹‹የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጎችን በትውልድ አገራው የተለያዩ መብቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ›› በወጣው አዋጅ ረት አንድ የተወላጅነት መታወቂያ ያለውን ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሚኒስትር፣ ጳጳስ፣ የባንክ ገ ቃል አቀባይ ወይም ግ አስከባሪ መሆን አይችልም ብሎ አላስቀመጠም። ገደቡም በብሔራዊ ምርጫ መምረጥንና መመረጥን፣ በደንነት፣ በመከላከያ፣ ውጭ ጉዳይ መሳሰሉት ላይ ነው። በተቃራኒው ካየነውም አንድ ትውልደ ኢትዮጵያዊ በመደበኛነት እስካልሆነ ድረስ በማናቸውም የገር መከላከያ፣ የገር ደንነት ወይም በውጭ ጉዳይና መሰል የፖለቲካ የመንግት መሪያ ቤት መራት ይችላል ማለት ነው (አንቀጽ 6)። እዚህ ላይ በብዙ መመርያዎች መተዳደያ ደንቦች ላይ ኢትዮጵያዊ ብቻ የሚለውን ከወሰድን ትውልደ ኢትዮጵያዊንም ያጠቃልላል ማለት ነው። ይንን የማይቀበሉ ሕጎች፣ ደንቦች መመያዎች፣ ውኔዎች ወይም አራሮች ተፈጻሚነት እንደማይኖራቸና ለአጁ ተባራዊነት የመተባበር ግዴታን ይህ አጅ ይደነግጋል (አንጽ 15-16)።

ችግሩ ይህን አዋጅ ለማስፈጸም የሚወጣው መመያ ነው። የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ የባን አክሲን ላይ ችግርን ሊፈታ ልቻለም ነበር፡፡ በየአምስት መቱ መታደስ ንዳለት የሚገልጽ፣ ሲታደስም አዲስ የወጣበትን ዋጋ መሶ የሚያስከል፣ የማሳደሻው ጊዜው ካፈ በየቀኑ የማሳደሻ ክፍያ በፐርሰንት የሚጨምር፣ ውጭ ለሚኖሩ ለማሳደስ ወራን መጠበቅ የሚያስፈልግ ነው። በአዋጁ አንቀ 14 ይኼንን የመታወቂያ ካርድ ስለሚሰረዝበትም ሁኔታዎች ይደነግጋል።

የጥምር  ዜግነት  አስፈላጊነት

ጥምር ዜግነት ማለት ጥምር መብትም፣ ጥምር ግዴታ ወይም ላፊነትም ነው። አንድ ኢትዮጵያዊ ከኢትዮጵያ ወጥቶ በሌላ  ገር ሲኖር በራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና በሌሎች ምክንያቶች የተነሳ ይወቱ ላይ የሚፈርበትን ጫና ለማቃለል፣ በሚኖርበት ገር መብቱን ለማስከበር፣ ግዴታውን ገሩ ነዋሪዎች እኩል ለመወጣት የሚያስችለው በተለይም የሚኖርበት ገር ለዜግነት የሚጠይቃቸውን መስፈርቶችን ሲያሟላ የሚኖርበትን ገር ዜግነትን ይወስዳል። በአብዛኛው  ገሮች ንንም ለማሟላት በወንጀል ተከሶ ያልተፈረደበት፣ የሚኖርበትን ገር ቋንቋ የሚናገር፣ ቋሚ   ወይም ንብረት ያፈራ፣ የሚኖርበትን ገር  የሚያውቅ  መሆኑንና መልካም ሰው መሆኑንም ታይቶ ነው። አንድ ኢትዮጵያዊ ኼን አሟልቶ የሌላውን አገር ዜግነት ሲወስድ የሚኖርበት ገር ጥምር ዜግነትን  የማይፈቅድ ከሆነየኢትዮጵያ ዜግነቱን እን ይጠይቃል።  ወይም ለመልቀቁ ማስረጃ ያቀርባል።ሎች አገሮች ጥምር ዜግነት እንዳለው ወይም መልሶ የመጀመ ዜግነቱን ቢይዝ አዲሱ (ሁለተኛው) ዜግነት የማይሰረዝ ለመሆኑ ሰርተኬት ይሰጠዋል። ሌሎች አገሮች ደግሞ ምንም አይጠይቁም። በተቃራኒው አንድ ኢትዮጵያዊ የሌላ አገር ዜግነትን ከወሰደ ኢትዮጵያ ዜግነቱን እንደተወ እንደሚቆጠርና ይህንን አስመልክቶ የዜግነት መልቀቂያ  ሰርተኬት እንደሚሰጠው ኢትዮጵያ በአዋጅ ተደንግጓል። ርግጥ ይህ አዋጅ አንዳንድ ቦታዎች ላይ  ግልየማይሆንበትና አተረጓጎምና የአሠራር ክፍተት የሚታይበት ነው። ጥምር ዜግነት ክልክል ነው የሚል የለም። ድሜያቸው ለአቅ አዳም ያልደረሰውን በተዘዋዋሪም ጥምር ዜግነትን አይገድብም (አንቀ 20 ቁጥር 2)።

የጥምር ወይም ጥምር ዜግነት ሳቤዎች ላይ የተዛቡ አስተያየቶች በአተባበር ደጃ ይታያሉ።  አንድ ጥምር ዜግነት ያለው ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ ሲኖር ሁለት ዜግነት ይኖረዋል ወይም ሁለት ፓስፖርት ይኖረዋል ማለት አይደለም።  አንድ የአሜሪካ ወይም የእንግሊዝ ተጨማሪ ዜግነት ያለው ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ ሲያሻው የኢትዮጵያ ዜግነቱን፣ ሲከፋው የአሜሪካ ወይም የእንግሊዝ ፓስፖርትን ይጠቀማል፡፡ ኢትዮጵያ ያለው የውጭ አገር ኤምባሲ ይሄዳል ማለት አይደለም። የጥምር ዜግነት ተፈቅዶ ወደ ኢትዮጵያ የተጨማሪ ዜግነት መግለጫ የሆነን የመጓጓዣ ሰነድ (ፓስፖርት) ይዞ የሚመጣ ሰውልክ የኢትዮጵያን መሬት ሲረግጥ የሌላኛው ዜግነት አይራም። እንደ ማንኛውም  ኢትዮጵያዊ ዜጋ ነው የሚሆነው። ችግር ደርሶብኛል ብሎ ወደ ሌላኛው አገር ኤምባሲ ቢሄድ አቤቱታው ተቀባይነት የለውም። ወይም ከዚህ አገር አውጡኝ ማለት አይችልም። ይህ ማለት በአንድ ጊዜ አንድ ዜግነት ብቻ ነው መጠቀም የሚቻለው፡፡ ይህ ራር ጀርመንን ጨምሮ በብዙ አገሮች የተለመደ ሲሆንበራዊ አድሎችን ‹‹ሶሻል ዲስ ባላንስን›› ማስተካያም ነው። ኢትዮጵያን ለቆ ሲሄድ ግን በፈለገበት አገር ዜግነት ይጠቀማል።

የሁለተኛ ዜግነት የሚጠቀመው ሁለተኛ ዜግነት በወሰደበት አገር ላይ ወይም የኢትዮጵያ ዜግነቱ ከሁለተኛ ዜግነቱ በአብላጫ ሊረዳው የማይችልበት ስተኛ አገር ላይ ይሆናል። ለምሳሌ አንድ ፈረን የሚኖርና ወደ ሌላ አገር ራ የሚመላለስ ሰው የፈረን ፓስፖርቱ ለብዙ አገሮች ቪዛ ስለማያስፈልገው ብዙ ቦታ ምክንያት ያለ ችግር ይሄዳል።  በኢትዮጵያ ፓስፖርት ግን ለምሳሌ ከአንዱ አውሮፓ አገ ወደ እንግሊዝ ልሂድ ቢል ቪዛ ለማግኘት ስት ሳምንት ሊፈጅበት ይችላል፡፡ ፓስፖርቱ በእንግሊዝ ኢምግሬሽን (ቦርደር ኤጀንሲ) ጋር ስለሚቆይ በመሀልም ወደ ሌላ አገር ሊሄድም አይችልም። ወደ ዜግነት አጠቃቀም ስንሄድ እንደተጠቀሰው ብዙ አገሮች የአገራቸውን ፓስፖርት ይዞ ለመጣ ሰ እግሩ አገራቸው ላይ ሲረግጥያውኑ የዚሁ አገር ዜግነቱ ላይ ሲጀምር፣ ሁለተኛው ዜግነት ደግሞ ገሩ እስከሚወጣበት ጊዜ ድረስ ያቆማል። በአርጀንቲና ለምሳሌ ያውኑ ሳይሆን ከዘጠና ቀናት በላይ ከቆየ የአርጀንቲና ዜግነቱ ብቻ ነው የሚያገለግለው።

እንደ አርሜንያ ያሉ አገሮች ዜግነታቸው የማይለቀቅ መሆኑን በማስቀመጥ አንድ ሰው የሌላ አገር ፓስፖርት ስለያዘ ብቻ ዜግነቱን ያጣል የሚሉትን አይቀበሉም። ይህም በብዛት የሚታወቀው Jus Sanguins (Right Of Blood) የሚለው ሲሆንአንድ የዚህ አገር ትውልድ ያለው መቼውንም ዜግነቱን አያጣም። እዚህ ላይ ቤተ እስራኤሎችን፣ ሩሲያዊያን፣ ጀርመኖች፣ ያኖችን ወዘተ መውሰድ ይቻላል።  በሌላ በኩል ሌሎች አገሮች ወደ የሚሄዱ ዜጎቻቸውን የሄዱበትን አገር ዜግነት በተጨማሪ እንዲወስዱ ያበረታታሉ። ምክንያቱም ነሱ ተወላጆች በሄዱበት አገር ፅዕ እንዲፈጥሩነሱን አገር ጥቅም እንዲያስጠብቁላቸውም ነው።

በተጨማሪም እንደ ጀርመን ያሉ አገሮች ዜግነትን እዚያ አገር ውስጥ ለተወለደ ይሰጣሉ። ይህም ዜግነትን በቦታው በመወለድ Jus Soli (Right Of Soil) ነው። 60 በመቶ የሚሆነው የስዊዘርላንድ ዜጋ ከስዊዘርላንድ ውጪ ይኖራልይህም የጥምር ዜግነትን ለዜግነት ረታቸው እንዲያደርጉ አስችሏቸል። አውሮፓ ውስጥ የጥምር ዜግነት በአብዛኛው በተለይም ከአውሮፓ ብረት ለመጡት ይሰጣል። ጀርመን ለአውሮፓ ብረት ዜጎች ሁለቱንም ዜግነት ለመያዝ ይፈቅዳል። ከአውሮፓ ብረት ው ለመጣ ሰው የጀርመንን ዜግነትን ከሚያገኝ ይልቅ የጀርመን ዜጋ ሆኖ የእነዚህን ገሮች ዜግነት ቢጠይቅ ይቀላል። ከአውሮፓ ብረት ው ላሉ አገሮች ወጣቶች ደግሞ የመምረጥ ሞዴል ሲኖር፣ የጀርመን ዜግነትን ብቻ ይዘው የሌላ የጥምር ዜግነት የሚፈቅድን አገር ዜግነት ለመውሰድ ለሚያመለቱ የጀርመኑ እንዳይሰርዝባችው የዜግነት ማቆያ ሰርተፊኬትን ምክንያታቸውን አቅርበው ያገኛሉ። ዜግነትን የማይለቁ አገሮች ዜጎች ለምሳሌ እንደ አፍጋኒስታን ያሉ የጀርመንን ዜግነት ደርበው መያዝ ይችላሉ።

ጥምር ዜግነት 1990ዎቹ ጀምሮ እየተበራከተ በተለይም ባለፉት 15 ዓመታት በተለያዩ ለማችን ክፍል በፍጥነት እየተስፋፋ የመጣ፣ ዝኃነት ባላቸው በተለይም አምባገነን ባልሆኑ አገሮች የሚተገበር፣ መንግትና መሻሻል የተከሰተበት፣ የዜግነት ጉዳይ ቦርዶችንካውንስል በመፈጠር እየተስፋፋ ይገኛል። በተለይም  ብዙ ዜጎቻቸው  ከትውልድ አገራቸው የሚፈልሱባቸው አገሮች መልካም መፍት ዘመናዊ የዜግነት ማሻሻልን እያደረጉ ይገኛሉ። ከላይ እንደተጠቀሰው ለአንድ ሰው ከቁሳዊ ጥቅሞች በላይ መንፈሳዊ ርካታው ከፍተኛ ነው። በትውልድ ወይም በደም ያገኘውን ዜግነቱን ተገፈሃል ሲባል ልቦናዊ ጉዳት ነው። በተለይም በሄደበት አገር  ለፍቶጥሮ፣ መከራን ችሎ፣ ፈተናን አሸንፎ  ያገኘውና በሚኖርበት አገር እኩል የሚያደርገውን የሌላ ገር የዜግነት መብትለኢትዮጵያ ግን ከኢትዮጵያ ዜግነቱ የሚያስነሳው ወይም እንደ ቅጣት ሆኖ የትውልድ ወይም የደም ዜግነቱን ማሳጣቱ ጥሩ አይደለም። ጥምር ዜግነትን እንደ መሠረታዊ ሰብዊ መብት መመልከትም ተገቢ ነው። 

ይህ ድል ለሁሉም ኢትዮጵያውያን እኩል ነው። የፈለገ፣ በተለያየ መንገድ መውጣት የቻለና ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልቶ የሌላ አገር ዜግነት የወሰደ ኢትዮጵያዊ በሚኖርበት አገርበተለይም በቴክኖሎጂና በኢኮኖሚ ከኢትዮጵያ በአንፃራዊነት የተሻለ ከሆነ በውአገር ዜግነቱና መብቱ በመጠቀም የሚያገኘውን እሴት ወደ ኢትዮጵያ ለማሸጋገር ይቀለዋል። ለምሳሌ አንድ የተወለደ ያደገና የዚህ አገር ዜግነት ያለው ስፖርተኛ በተለይም እግር ኳስ፣ ቦክስ፣ ዋና፣ ክረምት ስፖርትበመሳሰሉት የኢትዮጵያ ዜግነቱ ካለው በፕሮፌሽናል  ውድድርም ሆነ ኢትዮጵያን ወክሎ ለም አቀፍ መድረኮች ሊሳተፍና ኢትዮጵያን ሊያኮራ ይችላል። ኢትዮጵያም ውስጥ ስፖርቱን ሊያስፋፋ ይቻላል። የሌላ ዜግነትን ወስጄ ይንን ገር እወክላሁ ለሚሉትም የአቀፍ የውድድር መስርቶች እንደተጠበቁ ሆኖ ኢትዮጵያን ሊያስወክልም ይችላል። ውጭ ያፈራውን ሀብትም ያለ ጋት ለመጠቀም ያስችላል።

ጥምር ዜግነት የያዙ በፖለቲካ መሳተፋቸው ችግሩ አይታየኝም። ለኢትዮጵያ ድገት ብዙ ለሚዳክው፣ ገሩን ዘመዱን የሚረዳው፣ ራሱን ዝቅ አድርጎ ያጠራቀመውን ሀብት ኢትዮጵያ ላይ የሚያስ፣ ኢትዮጵያ ትጠራሃለች ሲሉት አቤት የሚለው፣ አንድ ዶላር በቀን ለማበርከት ለተዘጋጀው በአብዛኛው የውጭ ገር ዜግነትን የያዘውን ኢትዮጵያዊ ከትውልድ ገሩ ጋር የሚኖው ቁርኝነት ማጠናሪያና ትርጉም መስጫ ይሆናል። በብዛት የሚታየው የተደረሰበትን ውጤት እንጂ ምን ያህል ጠጠማ አቀበትና የብቸኝነት ጉዞ እንደሆነ ብዙው ያስፖራ ያቀዋል። የሚሄድበት አገርና ሰውም የመጣባቸውን ሰው ሊቀበሉት ወይም ላይቀበሉት ሊያከብሩት ወይም ሊንቁት ሊያደንቁት ወይም ይወቱን ሊያከብዱበት፣ የትውልድ ገሩን ሊያስረሱት ወይም ማንነቱን ሁልጊዜ የሚያስታውሱት ሊሆኑ ይችላሉ።

ጀርመን አገር የጀርመን ዜጋ ያልሆነ የውጭ አገር ዜጋ እንኳ በማንኛውም ፖለቲካ ፓርቲ አባል መሆን ይችላል። በፖለቲካ ፓርቲ ውስጥም ላፊነት መውሰድና መመረጥም ይችላል። የማይችለው በጀርመን ብሔራዊ ምርጫ መሳተፍ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ጥምር ዜግነት ቢኖር በፖለቲካ ላይ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ከላይ እንደተገጸው ኢትዮጵያ ሲገቡ የኢትዮጵያ ዜግነት ብቻ ተግባራዊ ስለሚሆንየግዴታና የታማኝነት ግጭት ውስጥ አይገቡም። ለምሳሌ ትልቁ ከሆኑት አንዱ የጀርመን ‹ሪጅናል ስቴትየታችኛው ሳክሶንያ (Lower Saxony) ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት ዴቪድ መክኤል ስተር የመጀመያው የጥምር ዜጋ ርዕሰ መስተዳድር የነበሩ ሲሆኑየእንግሊዝና የጀርመን ዜጋ ናቸው። አንዳንድ አገሮች የፕሬዚዳንትነት፣ የጠቅላይ ሚኒስርነት፣ የጦር አዛዥ ቦታዎች ላይ ያለ ሰው ነዚህ ቦታ ሲመረጥ ሁለተኛው ዜግነቱ እንዲረጋ ያደርጋሉ። ይህ ማለት ዜግነቱን ይለቃል ማለት ሳይሆንበሁለተኛው ዜግነቱ  የሚጠቀምባቸው  መብቶቹ ይረጋሉ ማለት ነው። ራው እስከሚቆይበት ጊዜ ድረስ ፓስፖርቱን ለሁለተኛ አገሩ ይመልሳል።  ግልጋሎቱን ሲጨርስ ተመልሶ በፓስፖርቱ መጠቀም ይችላል። ይንን መሰል ገድብ ያላቸው የአፍሪካ ገሮች አሉ። ለምሳሌ የግብየጥምር ዜግነት በወታደራዊና በደንነት በሚሩት ላይ ገደብ ያደርጋል።

በተጨማሪም ጥምር ዜግነት እሳቤነቱ ተበታትነው ከሚኖሩ ያስፖራዎች፣ በትውልድ ኢትዮጵያውያንና ከነሱ ለተወለዱ ልጆቻቸውና ልጅ ልጆቻቸው መብትና ጥቅምን፣ ይህም ኢትዮጵያን በቅጡ ለማያውቋት ትውልደ ኢትዮጵያውያንና ልጆቻቸው ሰብዊ መብትና ማበረታቻ ተደርጎ ማየትን ያስፈልጋል። አንድ በዜግነት አሜሪካዊ ነገር ግን ትውልደ ኢትዮጵያዊ፣ ከወላጆቹ ገርና ዝብ ጋር መርጦ ሳይሆን ጥሎበት የተሳሰረን ልጅ የኢትዮጵያዊነትን ዜግነት መከልከል ሰብዊነትን መጋፋት አይሆንምን?

ዛሬ ሦስት ዮን የደረሱት ውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያኖች ነገ ስድስት ሚሊዮን ማደጋቸው አይቀርምበተለያዩ መስክም ዕኖ ፈጣሪዎችን የሚያፈሩ መሆናቸውን መገንዘብ ያስፈልጋል። በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያ ከእነሱም የተወለዱ፣ የተቀየጡ በመላ ለም ላይ በተለያዩ መስኮች ላይ ይገኛሉ፡፡ እነዚህም የኢትዮጵያ ድብቅ/ምቅ ሀብትና የኢትዮጵያ ዓይን ናቸው።

የጥምር ዜግነት ተፈቅዶ የሚደነግግ ሲወጣ ንን አስከትሎ በመመያዎች አጨቃጫቂና አከራካሪ ሁኔታዎችንመገደብ የጥምር ዜግነቱ የማይራበትን ሁኔታዎችን ማስቀመጥ ይቻላል። ለምሳሌ ሁለኛ ዜግነት የሰጠው ገር ከኢትዮጵያ ጋር በጦርነት ላይ ያለ ከሆነ፣ በድንበር ግጭት ላይ የሚገኝ፣ በጠረፍ ላይ የሚገኙ ዝቦችን በተመለከተ የተለያዩ የይገባኛል፣ ብት፣ የንብረት ካሳ ሚያነሱ ሮችን በተመለከዜግነት ላይ ጊዜያዊ ገደቦችን በተለይም በከፍተኛ የመንግት ቦታዎች ላይ (ፕሬዳንትነት፣ በጠቅላይ ሚኒስርነት፣ በጦር  አዛዥነት፣ በደንነት ላፊዎች) ሊያስቀምጥ ይችላል። በአጠቃላይም የሚያስፈልግ ሆኖ ሲገኝም ጥምር ዜግነት የሚፈቀድላችው ሮችን ዝርዝርም ሊያወጣ ይችላል።

የጥምር ዜግነት ቢፈቅድም እስከ ዛሬ የነበረው የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ወረቀት የግድ መቀጠል አለበት። ይውም  ጥምር ዜግነት ከማይፈቅድባቸው አገሮች የውጭ ዜግነትን የወሰደሰው በኢትዮጵያ መብቶች እንዲጠቀምና አስፅኦ እንዲያበክት ያስችለዋል። ለምሳሌ ጥምር ዜግነት የማይፈቅድበትን ህንድ፣ ባህሬን፣ ወዘተ የመሳሰሉትን ይመለከታል። በተጨሪም ያለበት አገር የጥምር ዜግነት ቢፈቅድም እንኳን ግለቡ በግሉ ኢትዮጵያ ሲገባየኢትዮጵያ ዜግነት መብትና ታዎች የማይፈልግ ከሆነና በሁለተኛው ዜግነቱ ብቻ መጠቀም ለሚፈልግና ከኢትዮጵያዊያን ጋር በጋብቻ ለሚኖሩ  የውጭ አገር ዜጎች የሚጠቅም ነው።

የጥምር  ዜግነትን  በተመከት ያሉ የግዛቤ ግጭቶች

በአንዳንድ ቦታ በጥምር ዜግነት ላይ ተቃውሞ፣ ፍራቻና ፎቢ አልፎም ጥላቻ ይታያል። ይህም በአብዛኛው ለኢትዮጵያ ከመቆርቆር፣ ሉዓላዊነቷ እንዳይደፈር ከመጋት፣ ባህልና ክብራችን እንዳይነካ ከመፍራት ሲሆን፣ ሌላው ደግሞ ስጥምር ዜግነት ባለን ሳናውቀው በምንቃወመው ሁኔታ (Unconscious Bias)፣  ከግንዛቤ ማጣት፣ ኢፍትሐዊ ነው ብሎ ስለሚታሰብም ይሆናል፡፡ ሌላው ለምሳሌ በጀርመን የጥምር ዜግነት ተቃዋሚዎች የሆኑ የቀኝ ክንፍና ዘረኞች የሚሉትን ካየን ጀርመናዊነት ይጠፋል፣ መጠቀሚያ እንሆናለን፣ ‹‹እኔ አንድ ዜግነት ብቻ ሮኝ እንዴት ሌላው ሁለት ይኖረዋል›› የሚሉና ከቅናትና ጭፍን ጥላቻም የመነጨ ነው። ጥምር ዜግነት ለኢትዮጵያ ከሚያስገኘው ጥቅምና ጉዳት ማመዛዘን ያሻል ጉዳትም ካለ ይንንም በደት በውስጥ በመመያ መገደብ ያስፈጋል።  ስለጥምር ዜግነት ያለ ጭፍን አመለካከትን ጉዳቱ ላይ ብቻ ከማተኮር ይልቅ፣ ጥቅሙን አንጥሮ ተመልክቶ ይንንም ለመጠቀም መጣር ተገቢ ነው።

የጥምር ዜግነትን አስመልክቶ የሌላ አገር ዜግነትን በተጨማሪ የሚወድ ሰው ለኢትዮጵያ በከተኛ የመንግልጣን ላፊነትን ለመውሰድ ታማኝና ሞራላዊ ተምሳሌት ሊሆን አይችልም የሚሉ አስተያቶች አሉ። ይንን በስት ከፍለን ማየት ተገቢ ነው።

አንደኛ የሚወስነው ከኢትዮጵያ ጋር በጦርነት ያለ ገር ዜጋ እስካልሆነ ድረስ፣ የግለሰቡ ማንነት፣ ለኢትዮጵያ ያለው ፍቅር፣ የራ ክህሎቱ፣ የትምህርት ደረጃው፣ ልምዱ፣ ያበከታቸው ማበራዊ ግልጋሎቶች፣ ለኢትዮጵያ ያበረከው ግልጋሎት ወይም የያዘው ራዕይ ከሁሉም በላይ ይንን ሰው እፈልገዋልሁ ብሎ የሚመርጠው እንጂ ‹‹ታማኝ ሊሆን አይችልም›› ብለው በሚጠረጥሩት ሰዎች አይደም። አንድ ግለሰብ ሁለኛ ዜግነት ያገበት አገ ለምንስ በጥርጣሬ ይታያል? ሁለት ልጆች ያሉት ሰው ሁለቱን መውደድ አይቻለውምን? ይህ ግሰብስ ኢትዮጵያን እኮ አብልጦ ሁለተኛ ዜግነት ከሰጠው አገር ቢድስ አይደል ፊቱን ወደ ኢትዮጵያ ያዞረው ወይም ለፖለቲካ ምርጫ የሚወዳደረው።

ሁለተኛ የኢትዮጵያን ጥቅም አሳልፎ ይሰጣል ተብሎ የሚታበው ጥርጣሬያዊ መላምት በተላቢጦሽ ካየነው የኢትዮጵያ ዜጋ ብቻ ያለው ሰውስ ይንን አያደርግም ማለት ነው? ጥምር ዜጋ ያለውስ ይንን ሊያደግ የሚችልበት ማረጋጫ አለ? ለኢትዮጵያ የሩ እንድ ካርል ሃይንስ ቦምና ሪቻርድ ፓንክረስት የኢትዮጵያ ዜነት አልነበራቸውምን (የክብር ሆነ አልሆነ ለውጥ የለውም)?

ስተኛ በለም ላይ የጥምር ዜግነት ያላችው አገሮች ብዙ ናው። ይህ የጥርጣሬ መላምት ሌላ አገር ተፈጽሞስ ያውቃል ወይ ብሎ መጠቅ ያስፈልጋል።

ኢትዮጵያን ለረዥም ጊዜ የጥምር ዜግነት የሌላት አገር ነች፡፡ እንደ ጃፓን፣ ቻይና የመሳሰሉት ነችና ይህ መቀጠል አለበት የሚል ሳብም ሊኖር ይችላል። በመጀመርያ የማይፈቀድባችው አገሮችን ምሳሌ ከመውሰድ ይልቅ የሚፈድባቸውን በቅድሚያ መውሰድ ተገቢ ነው። ሌላው ይህ ለዘመናት የፈጀው የአንድ ዜግነት አስ ለኢትዮጵያ ምን ጠቀመ ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል። ወደ ውጭ መፍለስና የሌላ ዜግነትን ከመውሰድ አላስቆመንም። እንኳን ወጣት ቀርቶ አረጋውያንስ እየፈሱስ አይደል። አንዳንዱ ሰውስ ልጆቹን አሜሪካ፣ እንግሊዝ ጀርመን ውስጥ እንዲወልዱ በመሄድ እነዚህ ልጆች የነዚህ አገር ዜጎች እንዲሆኑስ ያደርጉ የለምን። የድሮ የኢትዮጵያ ጎች ሲውጡ እኮ የሌላ ገር ዜግነት የወሰደ ኢትዮጵያ በጣም ትንሽ ነበር። አሁን ደግሞ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተሰደው የወጡበት፣ የሰዎች ዝውውር በጣም የፈጠነበት፣ የአገሮች ወሰኖች ትርጉም የተቀየረበትና ዘመነ ዲጂታል ላይ ነው ያለነው

አንድ ትልቅ ጥንቃቄ መደረግ የሚገባው ነገር ሁለተኛ ዜግነት የሰጠ አገርን ማክበርና ትርጉም መስጠት ያስፈልጋል። ‹‹ፓስፖርታቸውን እመልስላቸዋለሁ›› ‹‹ፓስፖርቱን ቀዶ የኢትዮጵያን መውሰድ ይቻላል››፣ ወዘማለቱ እነዚህ አገሮች በችግር ጊዜ ደርሰው ከትውልድ ወይም በደም ዜጎቻቸው ጋር እኩል አድርገው፣ የሞክራሲን አየር አስተንፍሰው፣ ሀብት ማፍራትንና መራትን ያስቻሉ ገሮችንሕዝብን በማዋረድ የኢትዮጵያ ዜግነትን ማስመለስ ለኢትዮጵያ ዜግነት ክብርን አለመስጠት ነው። በተለይም ንን ከስሜትና ከፖለቲካ ነፃ ሆነን ማየት እጅግ ተገቢ ነው።

ጥምር ዜግነት በውጭ ያለውን ኢትዮጵያዊ ገሩ፣ ዝቡና ከመንግ ጋር የሚያስተሳስረው፣ በአገሪቱ በራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ ተግዳሮቶች ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲሳተፍ የሚያስችለው ሲሆንለመምረጥ ለመመረጥም የሚያስችለው መብትን ልክ ብዙ የኢትዮጵያ ጎረቤት አገሮች ጥምር ዜግነትን ተግባራዊ እንዳደጉት ሁሉ ያስችለዋል። ግብ ሱዳንና ኬንያን መውሰድ ይቻላል። ለምሳሌ ኬንያ በቅርቡ ሕገ መንግቱን በማሻሻል ጥምር ዜግነትን ፈቅዳለች። የኢትዮጵያ መንግ አሁን የጥምር ዜግነትን አስመልክቶ ጥናት ላይ መሆኑ ትልቅ ጅምር ነው። ራሱ የትውልደ ኢትዮጵያዊ አዋጅ አንድ ርምጃ ወደፊት መሆኑን እንደተጠበቀ ሆኖ ግንንን ማስጨረስና ወደ ጥምር ዜግነት መቀየሩ ወሳኝ ርምጃ ለኢትዮጵያ ነው። በኢትዮጵያ ጥምር ዜግነትን ለመተግበር የገ መንግሥቱን አንቀጽ 6 ማሻሻል አያስፈልግም። ምክንያቱም በአንቀጽ 6 ላይ ከወላጆቹ ቢያንስ አንዱ ኢትዮጵያዊ የሆነ የኢትዮጵያ ዜጋ መሆኑን ስለሚገል። ማሻሻያ የሚያስፈልገው በአዋጅ ቁጥር 378/2003 ስለኢትዮጵያ ዜግነት የወጣው አዋጅ በዋናነት አንቀ 19-20 ይሆናል። ንን ሳብ ማሻሻል የሚፈልጉ ወይም ተቃራኒውን የሚያሳዩ ሳቦች መንሸራሸር እንደሚገባቸው ሳልጠቁም አላልም።

ከአዘጋጁ፡- ጸሐፊው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአገር ቤት ካጠናቀቁ በላ ጀርመን አገር በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን በማስተርስ ዲግሪ፣ በኢኮኖሚክስ የዶክትሬት ዲግሪ ከሁምቦልት ዮኒቨርሲቲ መመረቃቸውን፣ በፕሮጀክት ማኔጅመንት ስፔሻላይዝድ በማድረግ ለ16 ዓመታት በዳይምለር መርቼስ ቤንዝ ኩባንያ በመጀመርያ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዲፖርትመንት በፕሮጀክት ፖርትፎልዮ ማኔጅመንትና ኢንተርፕራይዘር አርክቴክቸር ማኔጅመንት፣ አሁን ደግሞ በሰው ሀብት (ሂዩማን ሪሶርስ) ዲፓርትመንት በብዝኃትነት (ዳይቨርሲቲ) ማኔጀርነት እየሠሩ መሆኑን፣ ለመርቼዲስ ቤንዝ በብራንድ አምባሳደርነት ከሚወከሉ በርካታ ሠራተኞች አንዱ መሆናቸውን፣ በተጨማሪም በተጋባዥ ሌክቸረርነት በፕሮጀክት ማኔጅመንት በተለያዩ የጀርመን ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚያስተምሩ፣ ለተለያዩ መሥሪያ ቤቶች፣ ለዩኒቨርቲዎችና ለክልል አመራሮች የፕሮጀክት ማኔጅመንትና የሥራ ባህል ሴሜናሮች በነፃ መስጠታቸውን፣ በኢትዮጵያ የመጀመያ የሆነውን የፕሮጀክት ማኔጅመንት መጽሐፍ በአማርኛ ጽፈው ለጥቅም ማዋላቸውን፣ በበርሊንና በአዲስ አበባ ከተሞች መሀልም ግንኙነት እንዲፈጠር ንግግር እንዲጀመር ጥረት ማድረጋቸውን፣ ዝንባሌያቸው እንደሆነ የሚናገሩትን የጁጂትሱ ስፖርት ወደ ኢትዮጵያ በማስገባትና የጁዶ ስፖርት እንዲስፋፋ በማድረግና በነፃ ዕርዳታ ማድረጋቸውን፣ በዚህ የስፖርት ዘርፍም በጀርመን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ማሠልጠናቸውንና በአፍሪካ ፌዴሬሽን በምክትል ፕሬዚዳንትነትና በዓለም አቀፍ ፌዴሬሽን የሥነ ምግባር ኮሽን በምክትል ፕሬዚዳንትነት እያገለገሉ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ጽሑፉ የእሳቸውን አመለካከት የሚያንፀባርቅ መሆኑን እየገለጽን፣ በኢሜይል አድራሻቸው [email protected] ማግኘት ይቻላል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት የኬንያው ፕሬዚዳንት ያስተላለፉትን መልዕክት ተመልክተው ባለቤታቸውን በነገር ይዘዋቸዋል]

የኬንያው ፕሬዚዳንት ከሕዝባቸው ለቀረበባቸው ቅሬታ የሰጡትን ምላሽ ሰማህ? እንኳን ምላሻቸውን...

የኢትዮ ኤርትራ ሰሞነኛ ሁኔታና ቀጣናዊ ሥጋቱ

“ግንቡን እናፍርስ ድልድዩን እንገንባ” የሚል ፖለቲካዊ መፈክር ጎልቶ በሚሰማበት፣...

ኦሮሚያ ባንክ ከተበዳሪ ደንበኞቼ ውስጥ 92 በመቶ የሚሆኑት አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ናቸው አለ

ኦሮሚያ ባንክ ለደንበኞቹ ከሰጠው ብድር ውስጥ ለአነስተኛና ለመካከለኛ ኢንተርፕራይዞች...

ሽቅብና ቁልቁል!

ጉዞ ከመገናኛ ወደ ሲኤምሲ ጀምረናል። ተሳፋሪዎች የዕለት ጉርሳቸውን መሸፈን...