Tuesday, May 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትአምስተኛው የጎዳና ላይ ሩጫ በርካታ አትሌቶችን አሳትፏል

አምስተኛው የጎዳና ላይ ሩጫ በርካታ አትሌቶችን አሳትፏል

ቀን:

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከዓመታዊ ውድድሮቹ አንዱ የሆነውን የጎዳና ላይ ሩጫ በቢሾፍቱ ከተማ አከናውኗል፡፡

እሑድ ታኅሣሥ 7 ቀን 2011 ዓ.ም. በተካሄደው አምስተኛው የ30 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ ከክለብ፣ ከከተማ አስተዳደር፣ ከክልል እንዲሁም በግላቸው የተሳተፉ ከ400 በላይ አትሌቶች ተሳትፈዋል፡፡

በቢሾፍቱ ከተማ በተከናወነው 30 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ በወንዶች ፅዳት አበጀ 1፡31.56 ሰዓት ከኤሌክትሪክ አንደኛ፣ ጀግሳ ታደሰ 1፡32.06 ሰዓት ኦሮሚያ ክልል ሁለተኛ፣ ፍቅር በቀለ 1፡32.09 ሰዓት ከፌዴራል ፖሊስ ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችለዋል፡፡

በሴቶች ሮዛ ደረጀ 1፡46.33 ሰዓት ከፌዴራል ማረሚያ ቤት አንደኛ፣ ታደለች በቀለ 1፡46.44 ሰዓት ከኦሮሚያ ማረሚያ ቤት ሁለተኛ፣ ዝናሽ መኮንን ከኦሮሚያ ፖሊስ 1፡46.53 ሰዓት ሦስተኛ ደረጃ በመያዝ በበላይነት ማጠናቀቅ ችለዋል፡፡

በውድድሩ ነባርና አዳዲስ አትሌቶች የተሳተፉ ሲሆን ለዓለም አቀፍ የጎዳና ውድድሮች ከወዲህ በቂ መሰናዶ ለማድረግ ጠቃሚ እንደሆነላቸው አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል፡፡

ዓለም አቀፍና አኅጉር አቀፍ ውድድሮች ፊታቸውን ወደ ጎዳና ማዞራቸውን ተከትሎ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የሚያዘጋጃቸው ውድድሮች ለአትሌቶች ወሳኝ ናቸው፡፡

ዓለም አቀፍ ውድድር አዘጋጆቹን በሚሰናዷቸው የጎዳና ውድድሮች አዳዲስ ኢትዮጵያውያን አትሌቶችን ስም መስማት እየተለመደ መጥቷል፡፡ ለዚህም የአገር ውስጥ ውድድሮች ጥቅማቸው የጎላ እንደሆነ ማሳያ ነው፡፡

በብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ላይ ሲነሳ ከነበረው ተቃውሞ ባሻገር የውድድሮችን ቁጥር ማብዛትና በውድድሩ የአትሌቶችን ተሳትፎ ቁጥር ለመጨመር ሽልማቱንና የውድድሩን ደረጃን ከፍ ማድረግ እንደሚገባ በብዙዎች ይነሳል፡፡

በብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ላይ ከሚነሱት ቅሬታዎች መካከል አንዱ የውድድሮች እጥረት መኖሩ ተጠቃሽ ነው፡፡ ለዚህም በአሁን ሰዓት በግላቸው እንዲሁም በማናጀሮቻቸው አማካይነት በተለያዩ መድረኮች ላይ የሚሳተፉ አትሌቶች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ይነገራል፡፡

በተለይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ደግሞ ዓለም አቀፍ የውድድር መርሐ ግብርን ከግምት ውስጥ አስገብቶና ተቀራራቢ የአየር ንብረት ያላቸውን ቦታዎች መርጦ ውድድር ማዘጋጀት እንዳለበት ይነገራል፡፡

ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ሐሙስ ታኅሣሥ 4 ቀን 2011 ዓ.ም. በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ዓመታዊ መርሐ ግብሩንና የብሔራዊ አትሌቶች ምርጫ መሥፈርት እንዲሁም የቅድመ ዝግጅት ቀን ገደብ አስቀምጧል፡፡

በአገር ውስጥ የሚያዘጋጃቸው ውድድሮችም ዓለም አቀፍ ዕውቅናን እንዲያገኙ ከዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ማኅበር ጋር እንደሚወያይም በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ተብራርቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመስቀል አደባባይ የመግቢያ ክፍያ ለምን?

ወጣቶች፣ ሕፃናትና አረጋውያን ሳይቀሩ መንፈሳቸውን የሚያድሱበት እንዲሁም ሐሳባቸውን በነፃነት...

በሕገ መንግሥቱ የተዋቀረው ‹‹የብሔር ፖለቲካ›› እና ‹‹ሥርዓቱ›› ያስከተለው መዘዝና መፍትሔው

(ክፍል አራት) በዓቢዩ ብርሌ (ጌራ) ባለፈው ጽሑፌ (በክፍል ሦስት) አሁን ያለው...

የኢትዮጵያ ኅብረተሰብና የመንግሥት መሪ ምሥል

በበቀለ ሹሜ በ2015 ዓ.ም. መጋቢት ወር ውስጥ ይመስለኛል በ‹ሸገር ካፌ›...

ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ ያደረገው አዋጅ የፍትሐዊነት ጥያቄ አስነሳ

በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ስምንት ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ በማድረግ ተቋማዊና...