‹‹እኛ ኢትዮጵያውያን አንዳችን የቆምነው በአንዳችን የተከፈለ የሕይወትና የአካል፣ የደምና የአጥንት መስዋዕትነት ነው!››
የሰላም ሚኒስትርና የኢሕአዴግ የሴቶች ሊግ ሊቀመንበሯ ወ/ሮ ሙፍሪያት ካሚል፣ በመቐለ ከተማ ታኅሣሥ 7 ቀን 2011 ዓ.ም. በተካሄደው የኢሕአዴግ የሴቶች ሊግ ጉባዔ ላይ ከተናገሩት የተወሰደ፡፡ ሊቀመንበሯ በእንባና በሳግ በታጀበው ተማጽኖአዊ ዲስኩራቸው አያይዘውም ‹‹እኔው ውስጥ እናንተ አላችሁ እናንተ ውስጥ እኔ አለሁ፤›› ካሉ በኋላ፣ ‹‹ታዲያ እርስ በርሳችን በእብሪት፣ በትእቢት፣ በንቀት ዓይን ላይ በመተያየት አንዳችን የአንዳችን መጥፋት፣ መንበርከክ፣ መጎተት፣ አንገት መድፋት እንዲኖር ፈለግን?›› ሲሉም ጠይቀዋል፡፡
ሊጉ 4ኛ መደበኛ ጉባዔውን እስከ ታኅሣሥ 9 ያካሄደው ‹‹በተደራጀ የሴቶች ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለሁለንተናዊ አገራዊ ለውጥ›› በሚል መሪ ቃል ነው፡፡