Friday, December 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየስደተኞች ቁጥር ወደ 144 ሚሊዮን ከፍ ብሏል

የስደተኞች ቁጥር ወደ 144 ሚሊዮን ከፍ ብሏል

ቀን:

ዓለም አቀፉ የፍልሰቶች ድርጅት (አይኦኤም) እ.ኤ.አ. በ2018 ብቻ 3,400 ስደተኞች ሕይወታቸውን እንዳጡ አስታውቋል፡፡ አብዛኞቹ ሕይወታቸውን ያጡት በጀልባ ተጭነው ወደ አውሮፓ አገሮች ለመግባት ሙከራ ሲያደርጉ ባህር ውስጥ ሰጥመው ሲሆን፣ ቀሪዎቹ ደግሞ ጥቅጥቅ ደኖችንና በረሃ አቆራርጠው ድንበር ለመሻገር በሚያደርጉት አደገኛ ጉዞም ሕይወታቸው መጥፋቱን ድርጅቱ ይፋ ያደረገው ሪፖርት ያሳያል፡፡

አይኦኤም እ.ኤ.አ. 2000 ላይ ‹‹ታኅሣሥ 9 የስደተኞች ቀን›› ብሎ መደንገጉ የሚታወስ ነው፡፡ በወቅቱ 150 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች የሚሌኒየም በዓልን ያከበሩት በስደት በሚኖሩባቸው አገሮች ላይ ሳሉ ነበር፡፡ ከዚያ ወዲህ ባሉት 18 ዓመታት ውስጥም የስደተኞች ቁጥር በየዓመቱ እያሻቀበ መጥቷል፡፡ እ.ኤ.አ. 2000 ላይ 150 ሚሊዮን የነበረው የዓለም የስደተኞች ቁጥር በ18 ዓመታት ውስጥ ወደ 244 ሚሊዮን አድጓል፡፡ 40 ሚሊዮን የሚሆኑ የዓለም ሕዝቦች ደግሞ ድንበር ባያቋርጡም በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚኖሩበትን አካባቢ እንደቀየሩ፣ ግማሽ ያህሉ በግጭትና በእርስ በርስ ጦርነት ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ መሆኑን ሪፖርቱ ያሳያል፡፡

እነዚህ የውስጥ ተፈናቃዮችና ድንበር የሚያቋርጡ ስደተኞች እንቅስቃሴ በአደጋ የተከበበ ነው የሚለው ድርጅቱ ስደት ከሥጋት የፀዳ እንዲሆን ለየአገሮቹ ጥሪ አቅርቧል፡፡ የዚህ ዓመት መሪ ቃል ‹‹ስደት ከሰብአዊ ክብር ጋር›› የሚል ሲሆን፣ ዜጎች የየአገሮቹ ድንበር ሲያቋርጡ ሰብአዊ ክብራቸው በማይነካ መልኩ እንዲሆን አይኦኤም ጠይቋል፡፡

የዓለም ሕዝብ ቁጥር መጨመርን ተከትሎ የሚያሻቅበው የስደተኞች ቁጥር እ.ኤ.አ. በ2015 የነበረው የስደተኞች ቁጥር እ.ኤ.አ. በ1970 ከነበረው በሦስት እጥፍ በልጧል፡፡

እ.ኤ.አ በ2015 የነበሩት 244 ሚሊዮን ስደተኞች ከጠቅላላው የዓለም ሕዝብ 3.3 በመቶ እንደሚሆን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ 48 በመቶ የሚሆኑ ስደተኞች ሴቶች መሆናቸውን፣ አማካዩ የስደተኞች ዕድሜም 39 መሆኑን የአይኦኤም አኀዝ ያመለክታል፡፡

የአብዛኞቹ ስደተኞች መዳረሻ አሜሪካ ስትሆን፣ እ.ኤ.አ. በ2015 በአሜሪካ የሚኖሩ ስደተኞች ቁጥር 46.6 ሚሊዮን ነበር፡፡ ቀጥሎ የምትመጣው ጀርመን ደግሞ በተመሳሳይ ዓመት ውስጥ 12 ሚሊዮን ስደተኞችን፣ ሩሲያ 11.6 ሚሊዮን፣ ሳዑዲ ዓረቢያ 10.2 ሚሊዮን፣ እንግሊዝ 8.5 ሚሊዮን ስደተኞችን ተቀብለዋል፡፡

በአጠቃላይ 62 በመቶ የሚሆኑት ስደተኞች መዳረሻቸውን የሚያደርጉት የእስያና የአውሮፓ አገሮችን ነው፡፡ አገሮች የሚያስተናግዱት የስደተኛ ቁጥር ከሕዝብ ቁጥራቸው አንፃር ሲታይ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የሕዝባቸው 88.4 በመቶ የውጭ አገር ዜጎች ናቸው፡፡ 75.5 በመቶ የሚሆነው የኳታር ነዋሪም እንዲሁ ስደተኛ ነው፡፡ በኩዌትም 73.6 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች ስደተኞች መሆናቸውን የአይኦኤም ያሳያል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...