Tuesday, April 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊየቀድሞው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ሽኝት

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ሽኝት

ቀን:

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለአንድ ቀን ብሔራዊ የሐዘን ቀን ያወጀላቸው የቀድሞ ፕሬዚዳንት አቶ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ሥርዓተ ቀብር ዛሬ ረቡዕ ታኅሳስ 10 ቀን 2011 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከመፈጸሙ በፊት፣ ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ጀምሮ በሚሌኒየም አዳራሽ የአስከሬን ስንብት ይደረጋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ጽሕፈት ቤት እንዳስታወቀው፣ ከስንብት በኋላ ቤተሰቦቻቸውና ከፍተኛ የመንግሥት ሹማምንት በተገኙበት ሥርዓተ ቀብራቸው ሲፈጸም ለክብራቸው መድፍ ይተኮሳል፡፡ የቀብር ሥነ ሥርዓት አስተባባሪ ብሔራዊ ኮሚቴ ባወጣው የሥርዓተ ቀብር መርሐ ግብር መሠረት ማክሰኞ ታኅሳስ 9 ቀን 2011 ዓ.ም. በመኖሪያ ቤታቸው ከፍተኛ የፌደራልና የክልል ሹማምንትና የውጭ አገሮች ዲፕሎማቶች  በተዘጋጀው  መዝገብ ላይ የሐዘን መልዕክቶቻቸውን ማስፈራቸው ታውቋል። ብሔራዊ የሐዘን ቀን መታወጁን ተከትሎ በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች፣ እንዲሁም በውጭ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች ለአንድ ቀን ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብምወስኗል። በ94 ዓመታቸው ያረፉት አቶ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያን ከ1994 እስከ 2006 ዓ.ም. 12 ዓመታት በፕሬዚዳንትነት ካገለገሉ በኋላ፣ ዜና ዕረፍታቸው እስከተሰማበት ጊዜ ድረስ በተፈጥሮና አካባቢ ጥበቃ እንዲሁም በተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎች ሲሳተፉ ቆይተዋል። ባደረባቸው ሕመም ምክንያት ሕክምና ሲከታተሉ የቆዩት ፕሬዚዳንት ግርማ በ94 ዓመታቸው ያረፉት ቅዳሜ ታኅሳስ 6 ቀን 2011 ዓ.ም. አጥቢያ ላይ እንደነበር ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰው መሆን ምንድን ነው? ቅርስና ማኅበራዊ ፍትሕ

በሱራፌል ወንድሙ (ዶ/ር) ዳራ ከጎራዎች፣ ከመፈራረጅ፣ ነገሮችን ከማቅለልና ከጊዜያዊ ማለባበስ ወጥተን...

ኢኮኖሚው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሳት ያሠጋል

በጌታቸው አስፋው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሱ የሚያሠጉኝ አንድ ሁለት ብዬ ልቆጥራቸው የምችላቸው...

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል በሕግ አምላክ ይላል

በገነት ዓለሙ የአገራችንን ሰላም፣ የመላውን ዓለም ሰላም ጭምር የሚፈታተነውና አደጋ...

በሽግግር ፍትሕ እንዲታዩ የታሰቡ የወንጀል ጉዳዮች በልዩ ፍርድ ቤት ሳይሆን በልዩ ችሎት እንዲታዩ ተወሰነ

የኤርትራ ወታደሮች በሌሉበትም ቢሆን ይዳኛሉ ተብሏል በፅዮን ታደሰ የሽግግር ፍትሕ የባለሙያዎች...