Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመልሶ ማልማት ምክንያት ነባር ነዋሪዎች አይፈናቀሉም አለ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመልሶ ማልማት ምክንያት ነባር ነዋሪዎች አይፈናቀሉም አለ

ቀን:

ነዋሪዎች በነበሩበት ቦታ የተሻለ ኑሮ እንዲያገኙ የሚያመቻች ጥናት እየተካሄደ ነው

በምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) የሚመራው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ከዚህ በኋላ በሚያስተዳድረው ክልል ውስጥ በመልሶ ማልማት ፕሮግራም የሚፈናቀል አንድም ሰው እንደማይኖር አቋም ያዘ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከያዘው አቋም በመነሳት የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ የመልሶ ማልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ፣ ከመልሶ ማልማት ቦታዎች የሚነሱ የኅብረተሰብ ክፍሎች በነበሩበት ቦታ እንዳሉ የተሻለ ኑሮ ስለሚያገኙበት ጥናት መጀመሩን አስታውቋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የመልሶ ማልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ተሾመ ለታ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ አስተዳደሩ በመልሶ ማልማት የያዛቸው ቦታዎች ላይ የነበሩ ሰዎች በሚካሄደው ልማት እንዴት መካተት እንዳለባቸው ምክረ ሐሳብ ማቅረብ የሚያስችል ጥናት እየተካሄደ ነው፡፡

‹‹ከቦታቸው የሚነሱ ሰዎች የሚቆዩበት ቦታና ግንባታው ከተካሄደ በኋላ እንዴት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ እያጠናን ነው፤›› ሲሉ አቶ ተሾመ ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የመልሶ ማልማት ፕሮግራም፣ ነባር ነዋሪዎችን ከማኅበራዊ መስተጋብራቸው ነጥሎ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የሚያሰፍር ነበር፡፡ ነባር ነዋሪዎች ወደ ማስፋፊያ ቦታዎች ሲዛወሩ ደግሞ በቦታቸው ላይ የቆዩ ነባር አርሶ አደሮችም ይፈናቀላሉ፡፡

‹‹ከዚህ ቀደም ነዋሪዎችን በማፈናቀል ሲካሄድ የቆየው መልሶ ማልማት ችግር ያለበት ነበር፤›› ያሉት አቶ ተሾመ፣ ‹‹አሁን የተጀመረው ስያሜው መልሶ መልማት ቢሆንም፣ ከቀድሞ መልሶ ማልማት ጋር ብዙ ልዩነቶች አሉት፤›› ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተያዘው በጀት ዓመት በለገሃር፣ በአምስት ኪሎ፣ በጌጃ ሠፈርና በደጃች ውቤ የመልሶ ማልማት ሥራዎችን ለማካሄድ አቅዷል፡፡

እነዚህ ቦታዎች ላይ ያሉ ነዋሪዎች በቦታቸው ተመልሰው ይሰፍራሉ ተብሏል፡፡ ቀደም ሲል በተከለሉ የመልሶ ማልማት ፕሮግራም ቦታዎች በተለይ በፍርድ ቤት ክርክር፣ በዕግድና በወሰን ማስከበር ምክንያቶች ቦታዎችን ነፃ አድርጎ ወደ ልማት መግባት አልተቻለም፡፡ በዚህም ምክንያት የሥራ አፈጻጸሙ ደካማ ነበር ተብሏል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በበርካታ ቦታዎች ለመልሶ ማልማት ፕሮግራም ተብሎ በርካታ ቤቶች ቢፈርሱም፣ ግንባታቸው ተካሂዶ አገልግሎት መስጠት የጀመሩት በጣም ጥቂት ናቸው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...