Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትክብርና ዝናውን ለመመለስ የሰነቀው የመዲናዪቱ ብስክሌት ፌዴሬሽን

ክብርና ዝናውን ለመመለስ የሰነቀው የመዲናዪቱ ብስክሌት ፌዴሬሽን

ቀን:

ኢትዮጵያ ኦሊምፒክን ጨምሮ በተለያዩ አኅጉራዊና ዓለማዊ ውድድሮች ከአትሌቲክስ ቀጥሎ ከምትወከልባቸው ስፖርቶች ብስክሌት ይጠቀሳል፡፡ ይሁንና ስፖርቱ  በፋይናንስ በተለይም በመወዳደሪያ ብስክሌቶች እጥረት ምክንያት ህልውናው ፈተና ውስጥ መግባቱ ውጤቱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ መሆኑ እንደተጠበቀ፣ በዲፕሎማሲው ረገድ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ መሆኑ የሚገልጸው የአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን ነው፡፡

ኢትዮጵያ ከስድስት አሠርታት በፊት በአውስትራሊያ በተከናወነው የሜልቦርን ኦሊምፒክ ተሳትፎ ካደረገችባቸው ስፖርቶች አንዱ የሆነው ብስክሌት አሁን ላይ የፋይናንስ ዕጦት ትልቅ ፈተና ቢሆንበትም፣ ስፖርቱ አዲስ አበባን ጨምሮ በአንዳንድ ከተሞች የመዘውተር ዕድሉ እንዳለ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ብስክሌት ፌዴሬሽን ብስክሌቱን ወደ ቀድሞ ክብሩና ዝናው ለመመለስ በመታተር ላይ ይገኛል፡፡ ይሁንና ስፖርቱ እንደ ጅምሩና ጉዞው ከዘመኑ ጋር ከመዘመን ይልቅ እስከ ቅርብ ዓመታት ድረስ ህልውናው አደጋ ላይ ወድቆ እንደነበርም የአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ረዘነ በየነ ይናገራሉ፡፡

እንደ አቶ ረዘነ ከሆነ ፌዴሬሽኑ ስፖርቱን በአዲስ አበባ ለማስፋፋት ክለብ ለማቋቋም ፍላጎት ካላቸው ድርጅቶችና ኩባንያዎች ጋር በትብብር እየሠራ ነው፡፡ በዕቅዱ መሠረትም አሁን በከተማው ከተቋቋሙት አምስት ክለቦች በተጨማሪ ክለቦችን ለማቋቋም ተስፋ ከሰጡ ተቋማት መካከል የአዲስ አበባ ፖሊስ እንደሚገኝበት ተናግረዋል፡፡ ለዚህም ሲባል ከዓለም አቀፉ ኮካ ኮላ ካምፓኒ ጋር በየዓመቱ የሚታደስ የስፖንሰርሽፕ ስምምነት እንዳላቸው ጭምር ያስረዳሉ፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በቅርቡም በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የተፈጠረውን ወዳጅነት ለማጠናከር ፌዴሬሽኑ የብስክሌት ቱር ማከናወኑን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፣ ይህንኑ አገር አቀፍ ይዘት ያለው እንዲሆን በማድረግ የአዲስ አበባ፣ የኦሮሚያ፣ የድሬዳዋ፣ የአማራና የትግራይ ብስክሌተኞችን ያካተተ የብስክሌት ጉዞ ተደርጎ አስመራ በመግባት ትልቅ የሕዝብ ለሕዝብ ሥራ እንደሠራ ተናግረዋል፡፡

ጠቀሜታውንና ፋይዳውን አስመልክቶ አቶ ረዘነ፣ የኤርትራ አትሌቶች በብስክሌት ትልቅ ስምና አቅም ያላቸው በመሆኑ ከሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ጥንካሬው በተጨማሪ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ጭምር አስረድተዋል፡፡  ለስፖርቱ ሰላም ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው ያከሉት አቶ ረዘነ፣ ጉዟቸውን ከጀመሩበት ከአዲስ አበባ ደብረ ብርሃን፣ ደሴና በሁሉም ከተሞች የነበረው የሕዝብ አቀባበልና ከበሬታ መረዳት የቻሉት ኢትዮጵያውያን ለሰላም ያላቸውን ትልቅ ስሜት መረዳት የቻሉበት ትልቅ መድረክ ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ ጠንካራ የብስክሌት ተሳትፎ ከሚታይባቸው ትግራይ  አንዱ ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት የአዲስ አበባ ብስክሌት ወቅታዊ ብቃትና ደረጃ እንዴት ይታያል ለሚለው ጥያቄ አቶ ረዘነ፣ ‹‹በከተማዋ የሚገኙ ድርጅቶችና ካምፓኒዎች ክለብ ለማቋቋም ፍላጎቱ አላቸው፡፡ ይሁንና የመወዳደሪያ ብስክሌቱን ጨምሮ ስፖርቱ የሚፈልጋቸው ቁሳቁሶች ከሌላው ስፖርት በተለይ ውድ መሆኑ ፌዴሬሽናችን ብስክሌቱን በሚፈለገው ልክ ለማስፋፋት አልቻለም፤›› ብለው ሌላው ተግዳሮት ደግሞ በኢትዮጵያ ብስክሌቱን ጨምሮ ክለቦች ሲቋቋሙ በግለሰቦች ፍላጎት ላይ መመሥረቱ በስፖርቱ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ ቀላል የማይባል ተፅዕኖ እያሳደረ ስለመሆኑ ጭምር ይናገራሉ፡፡

ስለሆነም በኢትዮጵያ ብስክሌቱን ጨምሮ ስፖርቱ ሲመሠረት በግለሰብ ፍላጎት ላይ የተመሠረተ እንዳይሆን መንግሥትና የሚመለከታቸው አካላት በቅንጅት ሊሠሩ እንደሚገባ ጠይቀዋል፡፡ እዚህ ላይ በተለይ የስፖርት ሚዲያው የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጠየቁት ኃላፊው፣ ይህ ችግር ባልተቀረፈበት አሠራር በሁሉም ስፖርቶች ኅብረተሰቡና መንግሥት የሚፈልጉት ለውጥ ሊመጣ እንደማይችል ጭምር ተናግረዋል፡፡ የአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን ዓመታዊ በጀት 150,000 ብቻ መሆኑ ዕውን በዚህ በጀት ምን መሥራት ይቻላል? ሲሉም የአግራሞት ጥያቄ ጠይቀዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...