የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)፣ በወቅታዊ የአገር ጉዳዮችን አስመልክቶ ሰሞኑን ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ካደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ የተወሰደ፡፡ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች በቁጥር ከመብዛት ሰብሰብ በማለት ትርጉም ያለው በርዕዮት ዓለም ላይ የተመሠረተ ፓርቲ መመሥረት ይጠበቅባቸዋል ያሉት ሊቀመንበሩ፣ በተመሳሳይ ኅብረተሰቡም ከዚህ በፊት ከነበረው ከስሜትና ከንዴት እንዲሁም ከቂም በቀል ወጥቶ የሚመጣውን ሥርዓት ለመቀበል የባህሪ ለውጥ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡