Wednesday, June 12, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዓለምየአሜሪካ ጦር ከሶርያ መውጣት

የአሜሪካ ጦር ከሶርያ መውጣት

ቀን:

አሜሪካ በሶርያ ያሏትን ወታደሮች በሙሉ እንደምታስወጣ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የተናገሩት ከሁለት ሳምንታት በፊት ነበር፡፡ ‹‹ሁሉም ወደ አገራቸው ይመለሳሉ፡፡ አሁን ይመለሳሉ፤›› ብለው ፕሬዚዳንቱ ሲናገሩ፣ የአገሪቱ ባለሥልጣናትም የአሜሪካ ወታደሮች ሶርያን በ30 ቀናት ውስጥ እንዲለቁ ጊዜ መሰጠቱን አሳውቀው ነበር፡፡

የወቅቱ የአሜሪካ ውሳኔ በሰሜን ምሥራቅ ሶርያ ለሚገኙትና ከአሜሪካ ለወገኑት ኩርዶች ዱብ እዳ ነበር፡፡ ኩርዶችን እንደ ሽብርተኛ ለምትቆጥረው ቱርክ ደግሞ ብስራት፡፡

ለዓመታት በዘለቀው የሶርያ እርስ በርስ ጦርነት አሜሪካና ሩሲያ የእጅ አዙር ጦርነታቸውን ቢተውኑበትም የአሜሪካ ወታደሮቿን ከስፍራው አስወጣለሁ ማለት እፎይታን ይሰጣል ከተባለ ከ15 ቀናት በኋላ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ሐሳባቸውን ቀይረዋል፡፡ ‹‹አሁኑኑ›› ያሉት ቃላቸው ታጥፎም ‹‹ወታደሮቻችን ቀስ በቀስ ከሶርያ ወጥተው ከቤተሰቦቻቸው እንዲቀላቀሉ እናደርጋለን›› ብለው በአዲሱ ዓመት ዋዜማ ትዊት ማድረጋቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

- Advertisement -

የአሜሪካ ጦር ከሶርያ መውጣት

 

የፕሬዚዳንት ትራምፕ ውሳኔ የአሜሪካ መከላከያ ሠራዊት ባለሥልጣናትን ብቻ ሳይሆን ከአሜሪካ ጋር ወግነው አይኤስን የሚዋጉትን ጭምር ያስገረመ ሲሆን፣ ከአሜሪካ ለተጣመሩት ኩርዶችም እፎይታን ሰጥቷል ተብሏል፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ወታደሮቻቸውን ከሶርያ እንደሚያስወጡ መናገራቸውን ተከትሎ ከቱርክ ጥቃት ይሰነዘርብናል በሚል የሰጉት ኩርዶች በሰሜናዊ ሶርያ የሚገኘውን ማንቢጅ ከተማ ከቱርክ ጥቃት ለመከላከል የሶርያን መንግሥት ዕርዳታ ጠይቀው ነበር፡፡

የሶርያ መንግሥት ወታደሮች ባለፈው እሑድ በከተማዋ አቅራቢያ ተገኝተው የነበረ ቢሆንም፣ የአሜሪካ ወታደሮች በስፍራው በመኖራቸው ምንም ዓይነት ግጭት ላለመፍጠር ተመልሰው መሄዳቸውን መቀመጫውን በእንግሊዝ ያደረገውና በሶርያ የሰብዓዊ መብት ጥሰትን የሚቃኘው ድርጅት አሳውቋል፡፡

አሜሪካ ከ2,000 የሚበልጡ ወታደሮቿ በሶርያ የሚገኙ ሲሆን ወታደሮቿን ለማስወጣት የወሰነችውም አይኤስ ተመትቷል በሚል እሳቤ ነበር፡፡ ፕሬዚዳንቱ ትራምፕ ወታደሮቻቸውን እንደሚያስወጡ ቃል የገቡት ይህንንኑ ታሳቢ አድርገው ነው፡፡ ሆኖም አይኤስ በሶርያ ሰሜን ምሥራቅ አካባቢዎች በየቦታው በመደበቅ አነስተኛ የሚባሉ ጥቃቶች እየፈጸመ በመሆኑ የአሜሪካ ወታደሮች በአንዴ ሙሉ ለሙሉ እንዳይወጡ ፕሬዚዳንት ትራምፕ መወሰናቸው ታውቋል፡፡

አይኤስ ሰሞኑን በኩርዶች በሚመራው የሶርያ ዴሞክራቲክ ኃይል ላይ ከፍተኛ ጥቃት ማድረሱም ተዘግቧል፡፡

እ.ኤ.አ. ከ2015 ወዲህ የእግረኛ ጦሯን በሶርያ ያስገባችው አሜሪካ በኋላ ላይ አይኤስን የሚዋጉትን ኩርዶች ለማሠልጠን ልዩ ኃይሏን መላኳም ይታወሳል፡፡ በሒደትም የጦር ኃይሏን በሶርያ ሰሜን ምሥራቅ አስፍራለች፡፡ አይኤስን እንዋጋለን ከሚሉ አገሮች ጋር ጥምረት በመፍጠርም ሶርያን የጦር አውድማ አድርገዋል፡፡ ጦርነቱ አይኤስን እንዋጋለን በሚል ቢሆንም፣ የሶርያ መንግሥት ኬሚካል ጦር መሣሪያ ተጠቅሟል በሚል የሶርያ የጦር ሠፈሮችን በአየር በመደብደብም ተሳትፋለች፡፡

የሶርያው ፕሬዚዳንት በሽር አልአሳድ ከሥልጣን ይውረዱ በሚል እ.ኤ.አ. በ2011 የተጀመረው ተቃውሞ ዓይነቱን ቀይሮ ጥንታዊቷና ታሪካዊቷን ሶርያ ባልተጠበቀ መንገድ ለውድመት የዳረጋት ሲሆን፣ ለዚህም አሜሪካ፣ ሩሲያና ኢራን በሶርያ ሜዳ የውክልና ጦርነታቸውን ማካሄዳቸው እንደ ዋና ምክንያት ይጠቀሳል፡፡

ሦስቱም አገሮች እግረኛ ጦራቸውን በሶርያ ያሰማሩ ሲሆን፣ ኢራንና ሩሲያ የሶርያው ፕሬዚዳንት በሽር አልአሳድ የጀርባ አጥንት ናቸው፡፡ አሜሪካ የበሽር አል አሳድ ተቃዋሚ መሆኗ ደግሞ በአገሪቱ በነበረው የእርስ በርስ ጦርነት ላይ ቤንዚን አርከፍክፏል፡፡

አሁን ላይ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ‹‹በሶርያ ላይ ያነሳሁት እጄን ታጥቤያለሁ›› በሚል ዓይነት ሶርያ ውስጥ ያለውን አይኤስ የመዋጋቱን ሥራ ለሩሲያ፣ ቱርክና ኢራን እያስተላለፉ ነው ሲል የቢቢሲው ዘጋቢ ጆናታን ማርከስ ዘግቧል፡፡

በሶርያ ከስምንት ዓመት በፊት የተቀሰቀሰው የተቃውሞ ሠልፍ ወደ እርስ በርስ ጦርነት አምርቶ በሺዎች የሚቆጠሩትን ቀጥፏል፡፡ ጦርነቱን ተከትሎ ‹‹የመካከለኛው ምሥራቅ ገነት›› የምትባለው ሶርያ ወደ ሲኦልነት ተቀይራለች። ከአሥራ ሦስት ሚሊዮን የሚበልጡ ዜጎቿ ተፈናቅለዋል፤ ከአምስት ሚሊዮን በላይ ተሰደዋል።

የተሸኘው የአውሮፓውያኑ ዓመት ከዚህ ቀደም ከተመዘገበ ሞት ዝቅተኛው የተመዘገበበት ነው፡፡ ባለፈው ዓመት 19,666 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፣ በ2017 የሟቾች ቁጥር 33 ሺሕ ነበር፡፡ ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ትልቁ ሞት በ76 ሺሕ የተመዘገበበት  2014 ነበር፡፡ በ2018 ከሞቱት 6,349 ሰላማዊ ሰዎች ሲሆኑ ከነዚህ 1,437ቱ ሕፃናት መሆናቸውን የሰብዓዊ መብት ቡድኑ አስታውቋል፡፡

የአሜሪካ ጦር ከሶርያ መውጣት

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...