Tuesday, December 5, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየትምባሆ የአልኮልና የመድኃኒት ቁጥጥር አዋጅ የበለጠ ጥብቅ እንዲሆን ጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ጠየቁ

የትምባሆ የአልኮልና የመድኃኒት ቁጥጥር አዋጅ የበለጠ ጥብቅ እንዲሆን ጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ጠየቁ

ቀን:

የትምባሆ፣አልኮል፣መድኃኒትና ምግብ ነክ ምርቶችን ለመቆጣጠር ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ አዋጅ የበለጠ ጥብቅ እንዲሆን የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ምክር ቤቱን ጠየቁ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕፃናት ወጣቶችና ማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ረቂቅ አዋጁን በዝርዝር ለመመርመር ዛሬ ረቡዕ ታኅሳስ 24 ቀን 2011 ዓ.ም. ባካሄደው ሕዝባዊ የውይይት መድረክ ላይ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚር አማን በረቂቅ አዋጁ ላይ የተቀመጡ ክልከላዎች በቂ አለመሆናቸውን በመገንዘብ ክልከላዎቹ የበለጠ ጥብቅ እንዲሆኑ የማሻሻያ ሳብ ለቋሚ ኮሚቴው አቀረቡ።

ካቀረቧቸው ጥብቅ የማሻሻያ ክልከላዎች መካከል እንደ ቢራ ያሉ የአልኮል ምርቶች በኤሌክትሮኒክ ሚዲያዎች ማለትም በሬዲዮና በቴሌቪዥን ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት እስከ ሌሊት 12፡00 ሰዓት ብቻ እንዲተዋወቁ በረቂቁ ላይ የተቀመጠው ድንጋጌ ተሻሽሎ፣ የአልኮል ምርቶች በተጠቀሱት ሚዲያዎች ሙሉ ለሙሉ እንዳይተዋወቁ ክልከላ እንዲጣል የሚል የማሻሻያ ሐሳብ አቅርበዋል። 

የአልኮል ምርቶች ማለት የአልኮል ይዘታቸው ከሁለት በመቶ በላይ መሆኑን የሚገልጸው የረቂቅ አዋጁ ትርጓሜ ተሻሽሎ የአልኮል ይዘቱ 0.5 በመቶ በላይ በሚል እንዲሻሻልም የጠየቁ ሲሆን፣ ለዚህ ያቀረቡት ምክንያትም አልኮል የሚያመርቱ ኩባንያዎች ከሁለት በመቶ በታች የሆኑ የአልኮል ምርት ዓይነቶችን በማምረት የአልኮል መጠጦች በተጠቀሱት ሚዲያዎች እንዲተዋወቁ ዕድል የሚሰጥ በመሆኑ ነው።

የአልኮል መጠጦችን ለማስተዋወቅና ገበያውን ለማስፋት ከፍተኛ ሽልማቶችን የሚያስገኙ ዕጣዎችን በቆርኪ ላይ ማያያዝ ክልከላ እንዲደረግበትም ሐሳብ አቅርበዋል።

ሚኒስትሩ እነዚህ ጥብቅ ማሻሻያዎች እንዲደረጉ ቋሚ ኮሚቴውን በጽሑፍ መጠየቃቸውን ተናግረዋል። ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት በሕዝባዊ ውይይት መድረኩ ላይ የተገኙ የጤና ባለሙያዎች፣ ታዋቂ አርቲስቶች፣ ወጣት ተማሪዎችና ሌሎች ባለድርሻዎች ረቂቅ አዋጁ የበለጠ ጥብቅ እንዲሆንና የአልኮል ማስታወቂያ እንዲቆም በተደጋጋሚመጠየቃቸው ነው። 

የትምባሆና አልኮል ሽያጭን በተመለከተ ረቂቅ ሕጉ ላይ ሁለቱም ምርቶች 18 ዓመት ዕድሜ በታች እንዳይሸጡ የሚደነግገው አንቀጽ ተሻሽሎ 21 ዓመት በታች እንዲባል ጠይቀዋል። ይኼን ሐሳብም በሕዝባዊ የውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት አብዛኞቹ ደግፈውታል።

የኢትዮጵያ ትምባሆ ኢንተርፕራይዝ የሥራ ኃላፊዎች በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው ረቂቅ የቁጥጥር ሕጉ በኩባንያው ላይ ሊያደርስ ይችላል ያሏቸውን ሥጋቶች አንስተዋል።

ካነሷቸውም ሥጋቶች መካከል ዋነኛው በረቂቁ የተቀመጡ የቁጥጥር ሕጎች የኮንትሮባንድ የሲጋራ ንግድን ያበረታታል የሚል ነው። ይኼም ከሥጋት ባለፈ ተጨባጭ መሆኑን ለማስረዳት በአሁኑ ወቅት እንኳን የአገሪቱ የሲጋራ ገበያ 44 በመቶው በኮንትሮባንድ በሚመጡ ምርቶች የተያዘ መሆኑን አንስተዋል።

የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ በዚህ ጉዳይ ላይ በሰጡት ምላሽ አጠቃላይ የኮንትሮባንድ ንግድን በተመለከተ መንግሥት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን ጠቅሰው፣ የሲጋራ ኮንትሮባንድ ንግድን በተመለከተ ግን የትምባሆ አምራች ኩባንያዎች ጥብቅ የቁጥጥር ሕግ መንግሥታት እንዳያወጡባቸው ሲሉ ራሳቸው የኮንትሮባንድ የሲጋራ ንግድ እንዲስፋፋ በማድረግ አልያም መስፋፋቱን በመደገፍ መንግሥት የቁጥጥር ሕግ ቢያወጣ ኮንትሮባንድ እንዲስፋፋ ከማድረግ የዘለለ ትርጉም እንደማይኖረው ለማስመሰል እንደሚሞክሩ ለመድረኩ አስረድተዋል።

ከመድኃኒት አስመጪዎችም በርከት ያሉ ሥጋቶች የተነሱ ሲሆን፣ ቋሚ ኮሚቴው የተነሱትን በግብዓትነት ወስዶ ተጨማሪ የውይይት መድረክ መጥራት አስፈላጊ መሆኑን ካመነበት የሚከለክለው ነገር ባለመኖሩ ሊጠራ እንደሚችል ገልጿል።

ይሁን እንጂ ረቂቅ አዋጁ የንግድ ጥቅማቸውን የሚነካባቸውም ሆኑ ሌሎች ለቋሚ ኮሚቴው አመራሮችና አባሎች በግል ስልካቸው ላይ በመደወል ማስቸገር እንደሌለባቸውና ተግባሩ እንዲቆም አሳስበዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...