ጥሬ ዕቃዎች
1 ኪሎ ቴላፒያ አሳ
400 ሚሊ ሊትር ወተት (8 የቡና ስኒ 250 ግራም ወይም ሩብ ኪሎ ሩዝ)
6 የሾርባ ማንኪያ የገበታ ቅቤ ወይም ማርጋሪን
200 ሚሊ ሊትር ወይን ጠጅ ወይም ቪኖ (4 የቡና ሲኒ)
4 የሾርባ ማንኪያ ደቃቅ የስጎ ቅጠል
ጨውና ቁንዶ በርበሬ
አዘገጃጀት
- ሩዙን አጥቦ በውኃ ማብሰል፤
- አሳውን በደንብ አጥቦ እሾሁን ማውጣት፤
- በትልቅ መጥበሻ ቅቤውን ማቅለጥና አሳውን ሳይቆራረጥ መጥበሻ ላይ ማስገባት፤
- አሳውን በሁለቱም በኩል እያገላበጡ መጥበስ፤
- ወይን ጠጁን ጨምሮ ለአምስት ደቂቃ ሳያገላብጡ ማብሰል፤
- ወተቱን ጨምሮ ለሦስት ደቂቃ ማብሰል፤
- የስጎ ቅጠል፣ ጨውና ቁንዶበርበሬ ሩዙ ውስጥ መጨመርና ማደበላለቅ፤
- አሳውን እና ሶሱን ሩዝ ላይ አድርጎ ማቅረብ፡፡
- ጆርዳና ኩሽና ‹‹የምግብ አዘገጃጀት›› (2007)