‹‹ቅኝ ገዥዎች አፍሪካን ለመቀራመት ሲሉ በከፋፈሉልን መስመር ተለያየን እንጂ አብዛኞቹ የአፍሪካ ሕዝቦች ከአገሮች የፖለቲካ ድንበር የተሻገረ ኅብረትና አንድነት አላቸው፡፡ . . .ሕዝቦች በመካከላቸው ካለው ጥቃቅን ልዩነቶች ይልቅ አንድነታቸው ላይ ሲያተኩሩ እንደ ኦርዮን ነገሥታት ሺሕ ዘመናትን ተሻግረው ያበራሉ፣ በአንፃሩ ልዩነታቸው ሲያቀነቅኑ ግን ይፈረካከሳሉ፡፡ እንደ አገርም መቆም አይችሉም፡፡›› ይህ ነፀብራቀ ሐሳብ የያዘው ‹‹ቀንና ቃል›› የተሰኘው የቴዎድሮስ መስፍን (ዶ/ር) ልብ ወለድ ነው፡፡ ልቦለዱ መልካም እሴቶች ብሎ ካመላከታቸው ውስጥ አንድነት አንዱ ሲሆን፣ ሌላው የኢትዮጵያ ተስፋ በሚልም ‹‹አሁን ለታላቅነት ተራው የኛ ነው፡፡ የኢትዮጵያውያን . . .›› ሲልም ጠቁሟል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ንግድ ሥራ ትምህርት ቤት መምህሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ የደረሰው ‹‹ቀንና ቃል›› ታኅሣሥ 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ለንባብ በቅቷል፡፡