Wednesday, February 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየዕርምጃ ቀን በኢትዮጵያ

የዕርምጃ ቀን በኢትዮጵያ

ቀን:

ሰዎች የዕድሜና ፆታ ገደብ ሳይኖርባቸው ከሚያዘወትሩባቸው መድረኮች አንዱ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ነው፡፡ ከሦስት አሠርታት ወዲህ የዕርምጃ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ በቋሚነት እንዲከናወን ቀን ተቆርጦለት ዘንድሮ ለ27ኛ ጊዜ ባለፈው ጥቅምት ወር በተለያዩ አገሮች ተከናውኗል፡፡ በኢትዮጵያ ደግሞ በሁለት ወር ዘግይቶ ጥር 5 ቀን 2011 ዓ.ም. በተመረጡ 13 ከተሞች እንደሚደረግ የስፖርት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የስፖርት ምክትል ኮሚሽነር አቶ ጌታቸው ባልቻ ሐሙስ ታኅሣሥ 25 ቀን በሰጡት መግለጫ፤ አምስት ኪሎ ሜትር በሚሸፍነው የእግር ጉዞ በሚታሰበው የዕርምጃ ቀን ከ85,000 ሰው በላይ ይሳተፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል፡፡

የእግር ጉዞው አምራች ዜጋ ለመፍጠር፣ የኅብረተሰቡ ማኅበራዊ ግንኙነት የሚዳብርበት፣ ከዚያም ሲያልፍ ዜጎች ጤንነታቸውን ለመጠበቅና ለመዝናናት እንዲሁም አካላቸውን ለማጎልበትና አዕምሮዋቸውን ለማበልጸግ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ምክትል ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የዘገየው ግን ይሁንታ ያለው ተግባር

ኅብረተሰቡ የሚሳተፍባቸውን ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ጨምሮ ስፖርቱ በመሠረታዊነት የሚተገበርባቸው የዕቅድ መርሐ ግብሮች መቆጣጠር ይቻል ዘንድ በአገር አቀፍ ደረጃ የስፖርት ፖሊሲ የወጣው በ1990 ዓ.ም. ነበር፡፡ ከሁለት አሠርታት በኋላ በአሁኑ ወቅት እየተነገረ የሚገኘውና ኅብረተሰቡን በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች (ማስ ስፖርት) የማሳተፍ ዕቅድ በፖሊሲው ተካቶ ይገኛል፡፡

ይሁን እንጂ የብዙኃን ስፖርትን ለማስፈን አልዘገያችሁምወይ ተብሎ ለምክትል ኮሚሽነሩ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ በተለይም ‹‹ዘግይቷል›› የሚለውን እንደሚጋሩት ተናግረዋል፡፡ የስፖርት ፖሊሲው በአፈጻጸም ደረጃ ምንም እንኳን ክፍተት እንዳለበት ባይካድም፣ ስፖርቱን ለማስፋፋት አሁን ላይ በሕግ ሙሉ ሥልጣን ያለው ስፖርት ኮሚሽን እንደመሆኑ ኅብረተሰቡ በጋራ የሚሳተፍበትን መድረክ በቋሚነት ማመቻቸት ግዴታ እንዳለበትም አስረድተዋል፡፡ እንደ እሳቸው አገላለጽ በስፖርት ኮሚሽኑ ጭምር ብዙውን ጊዜ ትኩረት ተሰጥቶ ሲሠራባቸው የቆየው፣ በውድድርና አልፎ አልፎ በሥልጠና ላይ ብቻ ነው፡፡

ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በስፖርት ፖሊሲው መሠረት የተመቻቸ ነገር ባይኖርም፣ ከመንግሥት ተቋማት እስከ ታችኛው የኅብረተሰብ ክፍል በየደረጃው ኅብረተሰቡ ለሚሳተፍባቸው መድረኮች ትኩረት በማድረግ ልሂቃን (ኤሊቶች) የሚፈጠሩበት ዕድል እንዳለ አቶ ጌታቸው ያምናሉ፡፡ ‹‹ስፖርት ለሁሉም›› በፖሊሲ ደረጃ ተካቶ እንዲቀጥል፣ ስፖርት ኮሚሽኑ ከጤና ጥበቃና ከትምህርት ሚኒስቴሮች ጋር በሙያተኞች የተደገፈ ጥናት ተደርጎ ስምምነት ላይ መደረሱንም አስረድተዋል፡፡ በስፖርት ኮሚሽኑ የመቶ ቀናት ዕቅድ ውስጥ ስፖርት ለሁሉም መካተቱንም ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

ቀጣይነቱን አስመልክቶ ምክትል ኮሚሽነሩ፣ ‹‹በአገሪቱ እንዳለው ነባራዊ እውነታ ከሆነ የተገኘውን አጋጣሚ በመጠቀም ነው ኤሊቶችን የምናገኘው፡፡ ይህ ደግሞ በዘመናዊ ዓለም አያስኬድም፣ ኤሊቶችን ማፍራት የሚቻለው ውድድሮችን ከታች ከኅብረተሰቡ መጀመር ሲቻል ነው፤›› ይላሉ፡፡

በመጪው ጥር የሚደረገው የዕርምጃ ቀን ከተቀመጡለት ዝርዝር ዓላማዎች ውስጥ ጠንካራና ጤናማ አምራች ዜጋን ለማበራከት፣ ለሕክምና የሚወጡ ወጪዎችን ለመቀነስ፣ የኅብረተሰቡን ማኅበራዊ ግንኙነት ለማጠናከርና ኅብረተሰቡ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ባህሉ እንዲያደርግ የሚሉት ይገኙበታል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...