Saturday, June 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
እኔ የምለዉጥምር ዜግነት በኢትዮጵያ ቢፈቀድ ለውጭ ተፅዕኖ በር ይከፍታል

ጥምር ዜግነት በኢትዮጵያ ቢፈቀድ ለውጭ ተፅዕኖ በር ይከፍታል

ቀን:

በጥበበ ሳሙኤል ፈረንጅ

ኅዳር 23 ቀን 2011 ዓ.ም. ‹‹እኔ ምለው›› በሚለው ዓምድ፣ አቶ ይናቸው አሰፋ ወልደ ጊዮርጊስ የፉትንና ዶ/ር ፀጋዬ ደግነህ ደግሞ በዚሁ ምድ ታሳስ 7 ቀን 2011 ዓ.ም. ፉትን በጥሞና አነበበኩ። ዙውን ሳቤን የሚጋራውን ነጥብ አቶ ይናቸው በጽፋቸው አንስተውታል። ሆኖም ዶ/ር ፀጋዬ ለአቶ ይናቸው መልስ በሚመስል የሰጡት አስተያየት ብዙ ነገሮችን ከግምት ያላስገባ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ነገሮችን ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ መመልከታቸውንም አጠራጥሮኛል። የጥምር ዜግነት ጉዳይ በማበራዊ ድረ ገችም ሲያከራክረን የቆየ ጉዳይ ነው። በእኔ እምነት የጥምር ዜግነት አሁን ለው የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ሊፈቀድ አይገባም፡፡ በዚህች ጽፌም ዶ/ር ፀጋዬ ያነሷቸው ጥቂት ነጥቦች ላይ አስተያየት ለመጠት እፈልጋለሁ።

ዶ/ር ፀጋዬ በተደጋጋሚ ያነሷቸው ነጥቦች ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሌላ ገር ዜግነት ሲወስዱ የኢትዮጵያ መንግት ኢትዮጵያውያን አስገድዶ ዜግነት ያስለወጣቸው አስመስለውታል። ብዙዎች የእሳቸውን ሳብ የሚደግፉ ሰዎች በማበራዊ ገች ላይ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ከገሩ ሳይወድ ተገዶ በመውጣቱ ነው የሌላ ገር ዜግነት የወሰደው የሚል መከራከርያ በብዛት ያቀርባሉ። ይ ግን ከጭብጥ ጋር የሚጋጭ ነው። በርግጥ ብዙዎቻችን ከገራችን ተሰን የወጣነው የገራችን መንግት በፈጠረብን ጫና ቢሆንም ስደተነታችን ግን የሌላ ገር ዜግነት እንድንወስድ አያስገድደንም። ብዙዎች የሌላ ገር ዜግነት የሚወስዱት በተለይ ዜግነት በወሰዱበት ገር የፌራል መንግት ሥራ ውጥ መቀጠር ስለሚፈልጉና በሌሎች የግል ጉዳይ ምክንያት ፈልገውና ፈቅደው ነው።

ዶ/ር ፀጋዬ በጽሑፋቸው፣ ‹‹የውጭ ዜግነትን የያዘ ሲሞት እንኳን የኢትዮጵያ ዜግነቱን እንደተወ ይቆጠራል› ወደተባለት ኢትዮጵያ ሄዶ የኢትዮጵያ አፈር ይሆናል፡፡ ታዲያ እንዴት ነው አንድ ሰው የሌላ አገር ዜግነት በተጨማሪ በማግኘቱ ኢትዮጵያዊ አይደለህም የሚባለው?›› ሲሉ ጠይቀዋል። በዚህ አባባላቸው ግን ያላስጨበጡት ግንዛቤ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሌላ ገር ዜግነት ሲወስዱ ወደውና ፈቅደው ታማኝነታቸውን ለሌላ ገር ለማድረግ የሚለው ነው። ከጅምሩ የሌላ አገር ዜግነት የወሰዱ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያዊ ዜግነታቸውን የተት ራሳቸው በመሆናቸው ‹‹ኢትዮጵያዊ አይደለህም›› ከመባላቸው በፊት ‘ኢትዮጵያዊ አይደለሁም’ ብለው ዜግነታቸውን መቀየራቸው ሊጤን ይገባዋል። አንድ ሰው በተለያ ምክንያቶች የሌላ አገር ዜግነት ቢወስድም የትውልድ ገሩ ፍቅር ይጠፋልገሩ ጋር ያለው ማበራዊ ትስስርም ይቀራል ማለት አይደለም። የጥምር ዜግነት ጉዳይ የሰዎችን ስሜት መለኪያ ሳይሆን ከሕግ አንፃር የሌላ አገር ዜግነት የወሰዱ ኢትዮጵያውያን በተለይ በገራችን የፖለቲካ ጉዳይ ሊፈጥሩት የሚችለውን አሉታዊ ጫና ከግምት የከተተ ነው።

ዶ/ር ፀጋዬ በጽፋቸው ‹‹ቅድመ አያቶቻችን እኮ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ያስፈልጋችኋል ወይም ዜጋ ናችሁ ተብለው አይደለም ኢትዮጵያዊ የሆኑት (በጊዜው ይህ አሠራር ባይኖርም እንኳን)፣ ኢትዮጵያንም በደማቸው ጠብቀው ያስተላለፉት። የእነሱ ልጅ ልጆች የሌላ አገር ተጨማሪ ዜግነት በመውሰዳቸው ‹‹የኢትዮጵያ ዜግነታቸውን እንደተው ይቆጠራል›› መባሉ ሳይበቃ፣ ኢትዮጵያዊ አይደሉም የሚለው በብዛት የሚሰማ አስተሳሰብ ግን ትክክል አይደለም፤›› በማለት የአርበኝነት ስሜታችንን ለመኮርኮር ሞክረዋል። ይህ ነጥባቸው ከጥምር ዜግነት ጋር ምን ሊያገናኘው እንደሚችል ግን ግልጽ አይደለም። ቅድመ አያቶቻችን ኢትዮጵያዊ የሆኑት ኢትዮጵያ ውስጥ በመወለዳቸው ነው። በኢትዮጵያዊ ዜግነት ፀንተው የቆዩትም የሌላ አገር ዜግነት ባለመውሰዳቸው ነው። የሌላ አገር ዜግነት የወሰዱ ኢትዮጵያውያን ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው ደግሞ ዜግነት ለተቀበሉበት ሌላ አገር ብቻ ታማኝ ለመሆን ቃል ገብተውና ምለው የሌላ አገር ዜግነት ሲቀበሉ የኢትዮጵያዊነት ዜግነታቸውን እንደሚተው አውቀውና ፈቀድው ነው። ስለዚህ የኢትዮጵያ ሕግ 378/2003 አንቀጽ 20  ቁጥር 1 በማያሻማ ሁኔታ የሌላ አገር ዜግነት የወሰዱ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያዊነት ዜግነታቸውን እንደሚያጡ ይገልጻል። ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሌላ አገር ዜግነት ሲወስዱ መጀመርያ ራሳቸው የተውትን ዜግነት ተከለከሉ ማለት ተገቢ መከራከርያ አይሆንም። የዚሁ አዋጅ አንቀጽ 17 እንደሚያረጋግጠው፣ ማንም ኢትዮጵያዊ ፈቅዶና ፈልጎ የኢትዮጵያ ዜግነቱን ካልቀየረ በስተቀር፣ መንግሥት ዜግነቱን ሊነጥቀው አይችልም።

ዶ/ር ፀጋዬ ያነሱት አንድ ነጥብ የእኔና ሌሎች የእኔን ሐሳብ የሚጋሩ ዜጎችን ሥጋት ያሳያል። ‹‹በሌላ በኩል ሌሎች አገሮች ወደ ውጭ የሚሄዱ ዜጎቻችውን የሄዱበትን አገር ዜግነት በተጨማሪ እንዲወስዱ ያበረታታሉ፡፡ ምክንያቱም የእነሱ ተወላጆች በሄዱበት አገር ተፅዕኖ እንዲፈጥሩና የእነሱን አገር ጥቅም እንዲያስጠብቁላቸውም ነው፤›› ብለዋል፡፡ ምንም እንኳን ዶ/ር ፀጋዬ ለመከራከር የሞከሩት ኢትዮጵያውያን የሌላ አገር ዜግነት በመውሰዳቸው ዜግነት የወሰዱበት አገር ለኢትዮጵያ ጥቅም እንዲሠራ ተፅዕኖ ለማድረግ ይረዳቸዋል የሚል ቢሆንም፣ ለኢትዮጵያውያን ዜግነት የሰጡ አገሮች ኢትዮጵያውያኑ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በአገራችን ፖለቲካ ውስጥ ተሳትፈው ከፍተኛ ሥልጣን የመያዝ ዕድል ቢገጥማቸው፣ ለውጭ አገሮች ጥቅም እንዲሠሩ ዜግነት የሰጣቸው አገር ተፅዕኖ እንደማያደርግ ምን ዋስትና ሊኖረን እንደሚችል አልገለጹልንም።

ዶ/ር ፀጋዬ ለመከራከርያ በተደጋጋሚ ያነሱት የጀርመንን የጥምር ዜግነት ነው። እንደ ጀርመን አገር ሌሎች ጥቂት አገሮች ጥምር ዜግነት ቢፈቅዱም፣ የጀርመን አገር የፖለቲካ ሁኔታና የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ እጅግ ይለያያል። የአሜሪካንም አገር እንደ ምሳሌ ብንወስድ፣ የአሜሪካን ዜግነት የሚቀበሉ ሰዎች ፍፁም ታማኝነታቸው ለአሜሪካ ብቻ እንዲሆንና ለሌላ አገር መንግሥት ተገዥ እንዳይሆኑ ያስገድዳል። እንደ አውስትራሊያ ያሉ አገሮች ጥምር ዜግነት ቢፈቅዱም ጥምር ዜግነት የያዙ ሰዎች ግን የምክር ቤት አባል እንዲሆኑም ሆነ ከፍተኛ ሥልጣን እንዲይዙ አይፈቅድም። እ.ኤ.አ. በ2016 የዚሁ የጥምር ዜግነት ጉዳይ በአውስትራሊያ ውስጥ ትልቅ ውዝግብ በመፍጠሩ ጥምር ዜግነት ያላቸው በርካታ የምክር ቤት አባላት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ከሥልጣናቸው እንዲለቁ ተደርገዋል። እንደ ደቡብ አፍሪካ ባሉ አገሮች ጥምር ዜግነት ቢፈቀድም፣ ጥምር ዜግነት የያዙ የደቡብ አፍሪካ ዜጎች ከአገር ሲወጡ ወደ አገር ሲገቡ፣ እንዲሁም በአገር ውስጥ ሲኖሩ ሊጠቀሙበት የሚችሉት የደቡብ አፍሪካን ፓስፖርት ብቻ መሆኑንም ሕጉ ይደነግጋል። የአሜሪካ ሕግም ተመሳሳይ ግዴታ ይጥላል።

ከዚህ በተጨማሪ ሊነሱ የሚችሉ የግብር አከፋፍል ጉዳዮች በአገር ላይ ሊፈጸም የሚችል ክህደት የአገር እምነት አጉድሎ መሸሽ ከተፈለገ፣ ጥምር ዜጋ ላለው ሰው ለመሸሽ ቀላል መሆኑ ከብዙ በጥቂቱ ሊጠቀሱ የሚችሉ ፈተናዎች ናቸው። ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት፣ የትኛውም አገር ለአንድ ሰው ዜግነት ሲሰጥ ዜግነት ሰጪው አገር ለዜግነት ተቀባዩ የሚሰጠው አንዱ ግዴታ ምንም ይሁን ምን ዜግነት የተቀበለበትን አገር ፍላጎት (Interest) እንዲያስጠብቅ ነው። ዜግነት የሰጠውን አገር ፍላጎት ካላስጠበቀ እንደ አገር ክህደት ይቆጠራል። ለምሳሌ አንድ የአሜሪካ ዜግነት የወሰደ ትውልደ ኢትዮጵያዊ፣ የኢትዮጵያ የምክር ቤት አባል ቢሆንና የአሜሪካንን አገር ፍላጎት የሚነካ ሕግ፣ ነገር ግን የኢትዮጵያን ጥቅም ፍላጎት የሚጠብቅ የሕግ ረቂቅ ቢወጣ፣ የሚያደላው ለየትኛው ሊሆን ይችላል? መልሱ እንደየሰው ሁኔታ ቢለያይም፣ የጥቅም ግጭት (Conflict of Interest) ስለሚኖር ያንን የሚያግድ ነገር (Guardrail) ሊኖር ይገባል። እንዲህ ዓይነት አወዛጋቢ ነገሮች እንዳይፈጠሩም አጋጅ ሊሆነው የሚችለው ጥምር ዜግነትን አለመፍቀድ ነው። ከዚህ በተጨማሪም ሕግ ቢጣስና የሌላ አገር ዜግነት ያለው ሰው ላይ ዕርምጃ ለመውሰድ ቢሞከር የሚያጋጥሙ ችግሮች ይኖራሉ። ጥምር ዜጋ ያለው ሰው የገቢ ግብር የሚከፍለው ለማነው? ይህም መልስ ይፈልጋል። የግብር ዕዳ ቢኖርበትና ሀብቱን ወደ ሌላ የዜግነት አገሩ ቢያሸሽ የኢትዮጵያ መንግሥት ግብር እንዴት ከዚህ ሰው ሊሰበሰብ ይችላል?

በተደጋጋሚ እንደታየው ትውልደ ኢትዮጵያውያን አገር ለመርዳት  ሊሳተፉባቸው የሚችሉ በርካታ ነገሮች አሉ። በእኔ እምነት በፖለቲካ ውስጥ መሳተፍ የሚፈልጉ የሌላ አገር ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ የሌላውን አገር ዜግነታቸውን መተው አለባቸው። ዶ/ር ፀጋዬ በአገር ላይ ክህደት ለመፈጸም ዜግነት መቀየር አያስፈልግም ሲሉ ያንፀባረቁት ሐሳብ በቂ መከራከርያ አይደለም። ክህደት የሚፈጽም ‹‹አንድ›› ዜግነት ያለው ኢትዮጵያዊ በቀላሉ ከአገር ሊያመልጥ የሚችልበት መንገድ የለውም። ስለዚህ ክህደት በሚፈጽመው ሰው ላይ አስፈላጊውን ዕርምጃ መውሰድ ይቻላል። ሆኖም ጥምር ዜግነት ያለው ኢትዮጵያዊ በተለይ ሁለተኛ ዜግነት የሰጠውን አገር ጥቅም ለማስጠበቅ በኢትዮጵያ ላይ ክህደት ቢፈጽም፣ በአስቸኳይ ከአገር ለማምለጥና ገንዘብ በቀላሉ ማሸሽ ይችላል፡፡ ጥቅሙን ያስከበረለት ሁለተኛ አገር ሊከራከርለት ይችላል፡፡ ያልተጠበቀ ዲፕሎማሲያዊ ቀውስም ሊፈጥር ይችላል። ክህደት መፈጸምም ሆነ አለመፈጸም የየግለስብ ህሊና የሚወስነው ነው። ግን አንድ ሰው የሌላ አገር ዜግነት ሲወስድ ዜግነት የሰጠው አገር ለዜግነት ተቀባዩ፣ ለዚያ አገር ብቻ መቶ በመቶ ታማኝ እንዲሆን ያስገድዳል። ሁለት ዜግነት ያላቸው ሰዎች የሁለቱ አገሮች ጥቅም ቢጋጭ መቶ በመቶ ለሁለቱም አገሮች ታማኝ ሊሆኑ አይችሉም። መጽሐፍ ቅዱስም፣ ‹‹ለሁለት ጌቶች መገዛት›› እንደማይቻል ያስተምራል። ቀደም ብዬ እንዳልኩት በኢትዮጵያ ውስጥ መራጭ ወይም ተመራጭ መሆን የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን፣ የሁለተኛ አገር ዜግነታቸውን የማይተውበት ምክንያት ለዚህ ጸሐፊ ግልጽ አይደለም።

በእኔ እምነት የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በሕግ አውጪ ወይም ሕግ አስፈጻሚ ተቋማት ውስጥ እንዲገቡ ማድረግ ለተጨማሪ ፖለቲካ ቀውስ ይዳርገናል። ባለፉት ዓመታት በአገራችን ፖለቲካ እንዳየነው አቶ በረከት ስሞኦንም ሆኑ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ሲወቀሱበት የነበረው ነገር፣ የኤርትራዊነት ደም ስላለባቸው ለኤርትራ ያደላሉ የሚል ነበር። ጥምር ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያውያን የፖለቲካ ሥልጣን ቢይዙ ታማኝነታቸው ለኢትዮጵያ አይደለም የሚል የፖለቲካ አቧራ መነሳቱ አይቀርም። ዛሬ እንኳን ኦሮሞ ከሆንክ ለኦሮሞ፣ ትግሬ ከሆንክ ለትግሬ ነው የምታደላው የሚለው አስተሳሰብ ፖለቲካውን ምን ያህል እንዳጨቀው እያየን ነው። ሰው ‹‹በዘሩ የሚመዘንበት አገር ውስጥ›› የሌላ አገር ዜግነት ይዞ ሥልጣን ይያዝ ብሎ መከራከር ወቅቱ አይደለም። በዚህ የፖለቲካ ድባብ ውስጥ ሆነን ጥምር ዜግነት ይፈቀድ ማለት ያልተጠበቀ ቀውስ መጋበዝ ይሆናል። የአሜሪካ ዜግነት ያለው የአሁኑ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሥልጣን ሲይዝ፣ በርካታ የሶማሊያ ምሁራን የአሜሪካ ዜግነቱን እንዲሰርዝ ጠይቀውታል። ከእነዚህም አንዱ የሕግ ባለሙያው ጉሌድ አህመድ ጃማ ነበር። ጉሌድ የሶማሊያን የአሁኑን ፕሬዚዳንት የአሜሪካ ዜግነቱን እንዲሰርዝ በጠየቀበት ጽሑፍ፣ ጣምራ ዜግነት የአገርን ጥቅም ከማስጠበቅ አንፃር የሚፈጥረውን ብዥታ ከመጠቆሙም በላይ፣ የውጭ ኃይሎች በአገር ውስጥ ጉዳይ ጣልቃ እንዲገቡ በር የሚከፍት መሆኑን አስምሮበታል። ጥምር ዜግነት ከተፈቀደ እኛም ለውጭ ተፅዕኖ በር ነው የምንከፍተው። በቅርቡ በተደረገው የአሜሪካ የፕሬዚዳንትነት ምርጫ ተወዳዳሪ የነበሩት የቴክሳሱ የሕዝብ እንደራሴ ቴድ ክሩዝ፣ የካናዳ ዜግነታቸውን ለመሰረዝ ተገደዋል። ይህም የሆነው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ከሆኑ ለካናዳ ያደላሉ ከሚል ሥጋት የመነጨ ነው።

ዶ/ር ፀጋዬ ማሳመኛ ለማድረግ የተጠቀሙብትና በተደጋጋሚ በጽሑፋቸው ያነሱት፣  ‹‹በዓለም ላይ የጥምር ዜግነት ያላችው አገሮች ብዙ ናቸው›› የሚል ነው።ይህ ከጭብጥ ጋር ይጋጫል፡፡ በአፍሪካ አገሮች እንኳን ከ47 ሮች ጥምር ዜግነት የሚፈቅዱ 12 ብቻ ናቸው። ከ22 የስያ ገሮችም ጥምር ዜግነት የሚፈቅዱት ሰባት ብቻ ናቸው። ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጥምር ዜግነት ሳይኖራቸው ገራችን ኢኮኖሚና በራዊ ኑሮ ከፍተኛ አስተዋጾ ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ ይህም ቀጣይነት አለው።ኢትዮጵያውያንን ከአገር ጋር የሚያስተሳስራቸው ዜግነታቸው ብቻ አይደለም። ዶ/ር ፀጋዬ እንደገለጹትኢትዮጵያዊነትና የኢትዮጵያ ዜግነትን መያዝ የተለያዩ ናቸው።ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሌላ አገር ዜግነት ስለያዙ የኢትዮጵያዊነት ስሜታቸው ይሸረሸራል፡፡ ለትውልድ ገራቸው ድገት የሚያደርጉት ጥረት ይገታል ማለት አይደለም። በእኔ እምነት በተለያዩ መስኮች የመሳተፍ ድል ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ሆኖም በርሰ ብሔርነት ሕግ በማውጣት በወታደራዊና በደንነት ሪያ ቶችእንዲሁም በመራጭነት ሊሳተፉ አይገባም። በእነዚህ ዘርፎች ለመሳተፍ ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው ኢትዮጵያውያን የወሰዱትን የሌላ አገር ዜግነት በመሰረዝ በእነዚህ ዘርፎች ግልጋሎት ሊሰጡ ይችላሉ።

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እየገለጽን፣ በኢሜይል አድራሻቸው [email protected] ማግኘት ይቻላል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...