Wednesday, December 7, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየአዲስ አበባ ምክር ቤት ለአዳዲስ መሥሪያ ቤቶች ስምንት ሹመቶችን አፀደቀ

  የአዲስ አበባ ምክር ቤት ለአዳዲስ መሥሪያ ቤቶች ስምንት ሹመቶችን አፀደቀ

  ቀን:

  ከታኅሳስ 25 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ለሦስት ቀናት መደበኛ ጉባዔውን ያካሄደው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ስምንት ሹመቶችን አፀደቀ፡፡

  የመጀመርያው አቶ እንዳወቅ ሀብቴ (ኢንጂነር) በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል፡፡ ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ነበሩ፡፡

  ሁለተኛው አቶ ዮሐንስ ምትኩ ሲሆኑ፣ የሰላምና የፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል፡፡ የሰላምና የፀጥታ ቢሮ እንደ አዲስ የተቋቋመ ነው፡፡ ይህ ቢሮ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንንና የደንብ ማስከበር አገልግሎት ጽሕፈት ቤትን ይመራል፡፡ አቶ ዮሐንስ ቀደም ሲል የከተማው ፍትሕ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ነበሩ፡፡

  ሦስተኛዋ ወ/ሮ ፍሬሕይወት ተፈራ ሲሆኑ፣ የዓቃቤ ሕግ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል፡፡ ወ/ሮ ፍሬሕይወት ቀደም ሲል የፍትሕ ቢሮ ኃላፊ ነበሩ፡፡ አራተኛው አቶ አብዱልፈታ የሱፍ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል፡፡ አቶ አብዱልፈታ ቀደም ሲል የንግድ ቢሮ ኃላፊ ነበሩ፡፡

  አምስተኛው አቶ ጀማሉ ጀንበር የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል፡፡ አቶ ጀማሉ የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ነበሩ፡፡ ስድስተኛው አቶ ኃይለ ሰማያት መርሐ ጥበብ እንደ አዲስ የተቋቋመው የወጣቶችና በጎ ፈቃደኛ ማስተባበርያ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል፡፡

  ሰባተኛዋ ወ/ሮ ዓለም ፀሐይ ጳውሎስ የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል፡፡ ስምንተኛው በድጋሚ የተቋቋመውን የባህል፣ የኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ እንዲመሩ ነብዩ ባዬ (ረዳት ፕሮፌሰር) ተሹመዋል፡፡

  ምክር ቤቱ ከእነዚህ አስፈጻሚዎች በተጨማሪ አቶ ተስፋዬ መለሰ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት፣ ወይዘሪት ፍራኦል ቶሎሳን ደግሞ ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ ሹሟል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ‹‹የወደፊቷ ዓለም ዲጂታል ትሆናለች ሲባል ሰውን ማዕከል ማድረግ አለበት››

  የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሪስ፣ በኢትዮጵያ በተካሄደው...

  መልካም ምኞት የተገለጸለት የዓለም እግር ኳስ ንጉሡ ፔሌ

  በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ የተያዘው የዓለም እግር ኳስ ንጉሡ...

  ‹‹እኔ እኮ ብቻዬን አይደለሁም››

  አንድ አዋቂ ወደ ሌላ አዋቂ መኖሪያ ሄዶ እንዲህ ብሎ...

  የናይጄሪያ ፕሬዚዳንትና የኢትዮጵያው ምሁር ገጠመኝ

  አንድ ሰኞ ቀን ከሌጎስ አንድ ሰዓት ተኩል ብቻ የሚወስደው...