Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበመዋቅር ለውጡ ቦታ ያላገኙ የአዲስ አበባ አመራሮች በሙያቸው ይመደባሉ ተባለ

በመዋቅር ለውጡ ቦታ ያላገኙ የአዲስ አበባ አመራሮች በሙያቸው ይመደባሉ ተባለ

ቀን:

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተካሄደ የመዋቅር ለውጥ የመሥሪያ ቤቶች ቁጥር በመቀነሱ፣ በርካታ አመራሮች ከሥልጣናቸው ተነስተው በሙያቸው ይመደባሉ ተባለ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስፈጻሚ አካላትን እንደገና ለማዋቀር የተዘጋጀው ረቂቂ አዋጅ ዓርብ ታኅሳስ 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ለከተማው ምክር ቤት ቀርቦ ፀድቋል፡፡ በወቅቱ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) እንዳብራሩት፣ የመዋቅር ለውጥ በመደረጉ ምክንያት ቦታ ያላገኙ አመራሮች በሙያቸው ይመደባሉ፡፡

በመዋቅር ለውጡ 110 የነበሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሥሪያ ቤቶች ወደ 63 ዝቅ እንዲሉ ተደርጓል፡፡ በአዲሱ መዋቅር 38 ተቋማት በነበሩበት ሲቀጥሉ፣ 14 ተቋማት እንደ አዲስ ተደራጅተዋል፡፡ ስድስቱ ተቋማት ከሌሎች መሥሪያ ቤቶች ጋር ተዋህደዋል፡፡ አምስት አዳዲስ መሥሪያ ቤቶች ተቋቁመዋል፡፡

አዲስ የተቋቋሙት መሥሪያ ቤቶች የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ፣ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን፣ የወጣቶች በጎ ፈቃድ ማስተባበርያ ቢሮ፣ የግንባታ ኢንተርፕራይዝና የግንባታ ዲዛይን ጽሕፈት ቤት ናቸው፡፡

አስተዳደሩ በከፍተኛ ደረጃ መሥሪያ ቤቶቹን የቀነሰ በመሆኑ በኃላፊነት ቦታ ላይ የነበሩ ባለሥልጣናት ከቦታቸው ተነስተዋል፡፡ መረጃዎች እንደጠቆሙት ባለሥልጣናቱ ወደ ኃላፊነት የመጡት በሹመት ቢሆንም፣ የመሥሪያ ቤቶች ቁጥር በመቀነሱ የተወሰኑት የቢሮ ኃላፊዎች አማካሪ እንዲሆኑ፣ የተቀሩት ደግሞ በሙያቸው ተመድበው እንዲሠሩ ተወስኗል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ1,500 በላይ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ይገኛሉ፡፡ በአጠቃላይ ከ95 ሺሕ ያላነሱ ሠራተኞች አሉ፡፡ ምክትል ከንቲባው አዋጁ በፀደቀበት ወቅት እንደተናገሩት፣ በከተማው የተጀመረውን የለውጥ ሒደት በትክክለኛ መንገድ ለማስኬድ ሪፎርሙ ትልቅ ድርሻ አለው፡፡

‹‹አዲሱ አወቃቀር ሪፎርሙን መሬት ለማድረስ ከፍተኛ ሚና ያለው ሲሆን፣ ይኼም አደረጃጀት ውጤታማነትንና የተቋማት ተጠያቂነትን ያሰፍናል፤›› በማለት ገልጸው፣ ‹‹የታጠፈው ሥራ ሳይሆን ተቋም ነው፤›› ሲሉም ለውጡ የሚኖረውን ጠቀሜታ አብራርተዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...