Thursday, September 21, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

የተከፈተው የሑመራ – ኦምሓጀር መስመር

ትኩስ ፅሁፎች

ኢትዮጵያንና ኤርትራን በሑመራ – ኦምሓጀር መስመር በምድር ትራንስፖርት የሚያገናኘው አውራ ጎዳና ታኅሣሥ 29 ቀን 2011 ዓ.ም. በሁለቱ መሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) እና በፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ በወግ ተከፍቷል፡፡ በሁለቱ አገሮች ብሔራዊ መዝሙር ታጅቦ በኦምሓጀር በተካሄደው ሥነ ሥርዓት የትግራይና የአማራ ርዕሳነ መስተዳድር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) እና ገዱ አንዳርጋቸው፣ እንዲሁም የጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኰንን ተገኝተዋል፡፡ ባለፈው መስከረም መባቻ የቡሬ – ደባይሲማ፣ የዛላምበሳ – ሰርሓ እና የራማ – ዓዲ ዃላ መንገዶች በሁለቱ መሪዎች መከፈታቸውና በቅርቡም የተወሰኑት ተመልሰው መዘጋታቸው ይታወሳል፡፡ ፎቶዎቹ የመስመሩ አከፋፈት ከፊል ገጽታን ያሳያሉ፡፡

(ፎቶ ከሓዳስ ኤርትራ ጋዜጣ፣ ፎቶ ከማኅበራዊ ድረ ገጽ)

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች