የቀድሞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንትና ለጥቂት ወራት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥና ቺፍ ኢኮኖሚስት በመሆን ያገለገሉት አቶ በቃሉ ዘለቀ፣ የአቢሲኒያ ባንክ ፕሬዚዳንት በመሆን ሥራ ጀመሩ፡፡
አቶ በቃሉ ከመንግሥታዊ ኃላፊነታቸው ከለቀቁ በኋላ አቢሲኒያ ባንክ በመቀላቀል ሥራ የጀመሩት ማክሰኞ ታኅሳስ 30 ቀን 2011 ዓ.ም. ነው፡፡
አቶ በቃሉ ይህንን ኃላፊነት የተረከቡት የአቢሲኒያ ባንክን ላለፉት አምስት ዓመታት በፕሬዚዳንትነት ሲያገለግሉ ከቆዩት አቶ ሙሉጌታ አስማረ ነው፡፡
አቶ ሙሉጌታ በአቢሲኒያ ባንክ የነበራቸውን የዘጠኝ ዓመታት ቆይታ በፈቃደኝነት በመልቀቅ ከአዲሱ ፕሬዚዳንት ጋር የሥራ ርክክብ ፈጽመዋል፡፡