የእግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት (ገና) በዓል ታኅሣሥ 29 ቀን 2011 ዓ.ም. ሲከበር ብዙዎች ችግረኞችን በመርዳት ማሳለፋቸው በየሚዲያው ተዘግቧል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)ን ጨምሮ ታዋቂ ሰዎችና ግለሰቦች የተቸገሩትን በበዓል ለመጎብኘት በየሥፍራው ጎራ ያሉበት ዕለትም ነበር፡፡ በየአካባቢው ያሉ የወጣትና የእምነት ማኅበራትም ቅርጫ ሥጋ፣ ዘይት፣ ሽንኩርት፣ እንቁላል በማድረግ በየተቸገሩት ቤት እየተዘዋወሩ ሲያከፋፍሉ ውለዋል፡፡ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚር አማን የተገኙት በሙዳይ በጎ አድራጎት ደርጅት ነበር፡፡ ለሙዳይ በጎ አድራጎትም፣ ከዋሽንግተን ሜዲካል ሴንተርና የኤቢኤች አጋሮች እንዲሁም ከአሜሪካን ሜዲካል ሴንተር (ሳማሪታን ሜዲካል ሴንተር) 80 ሺሕ እና 40 ሺሕ ብር በተከታታይ በድርጅቱ ለሚደገፉ ሰዎች ከብት መግዣ ተበርክቶለታል፡፡