Friday, December 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናኢዜአ አገራዊ መግባባትንና የአገር ገጽታን ለመገንባት የሚሠራ ሚዲያ ሆኖ እንዲቋቋም ረቂቅ ሕግ...

ኢዜአ አገራዊ መግባባትንና የአገር ገጽታን ለመገንባት የሚሠራ ሚዲያ ሆኖ እንዲቋቋም ረቂቅ ሕግ ቀረበ

ቀን:

ላለፉት 75 ዓመታት የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን በመሆን በማገልገል ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) የአገሪቱን የልማት፣ የዴሞክራሲና የሕዝቦችን በመፈቃቀድ ላይ የተመሠረተ ግንኙነትና አንድነት፣ እንዲሁም የአገሪቱን ገጽታ ለመገንባት የሚሠራ ሆኖ በድጋሚ እንዲቋቋም ረቂቅ ሕግ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ፡፡

ረቂቅ ሕጉ ሐሙስ ጥር 2 ቀን 2011 ዓ.ም. ለምክር ቤቱ የቀረበ ሲሆን፣ አገራዊ የዜና ተቋም ሆኖ ብሔራዊ መግባባት የመፍጠርና የአገሪቱን ገጽታ የመገንባት ተልዕኮ እንዲሰጠው፣ ይኼንንም ለመወጣት የተሻለ ተቋማዊና የአሠራር ነፃነት እንዲኖረው ሆኖ እንዲቋቋም ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን የረቂቅ ሕጉ ማብራርያ ሰነድ ይገልጻል፡፡

ረቂቅ ሕጉ ተቋሙ ተልዕኮውን በሕግ መሠረት እንዲወጣ የሚያስችሉ ትርጓሜዎችን ያካተተ ነው፡፡

በዚህም መሠረት ዜና ማለት ‹‹በበርካታ ሰዎች ወይም ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ላይ አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚፈጥርን አዲስ ክስተት የሚያመላክት፣ ተሞክሮ ማስተላለፍ የሚችል፣ የታዳሚዎችን ፍላጎት በማሟላት ሕዝቦችን ከራሳቸውና ከአካባቢያቸው ጋር ሊያገናኛቸው የሚችል ሐሳብ፣ ኹነት፣ ክስተት ወይም መረጃ ሲሆን የሕዝብን አስተያየት፣ የሞኒተሪንግ ውጤት፣ ወቅታዊ ትንታኔን ያካትታል፤›› ሲል ትርጓሜ ሰጥቶታል፡፡

በረቂቅ አዋጁ መሠረት ኢዜአ የራሱን አቅም ማሳደግና በገንዘብ መደጎም፣ ብሎም ተወዳዳሪ መሆን ይችል ዘንድ ገቢ በሚያስገኙ ሥራዎች መሰማራት ይችላል፡፡ ከእነዚህም መካከል በአደባባዮች በሚሰቀሉ ማሳያ ስክሪኖች ማስተዋወቂያዎችን ማሰራጨትና ኹነቶችን ማዘጋጀት ይገኙበታል፡፡

በተጨማሪም የተቋሙን አቅም ለመገንባት የተሻለ ሙያዊ አቅም ለመገንባት የተሻለ ሙያዊ አቅም ያላቸውን ባለሙያዎች ከገበያው ተወዳድሮ ለማግኘትና ይዞ ለማቆየት፣ እንዲሁም ምቹ የሥራ አካባቢ ለመፍጠር የሚያስችለው ነፃነት እንዲኖረው የሚያስችል ድንጋጌ በረቂቁ ተካቷል፡፡

የዜና አገልግሎት ነፃነቱን ጠብቆ መሥራት እንዲቻለው ተጠሪነቱ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሆን፣ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በምክር ቤቱ የሚሾም ዳይሬክተር እንደሚመራም በረቂቁ ተመልክቷል፡፡

ምክር ቤቱ ኢዜአን እንደገና ለማቋቋም የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ለተጨማሪ ዕይታ ለሕግ፣

 ፍትሕና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቶታል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...