Monday, April 15, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የገበያ መናጋት የገጠማቸው የሪል ስቴት ኩባንያዎች ስብሰባ ተጠሩ

ተዛማጅ ፅሁፎች

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) የሪል ስቴት ኩባንያዎች ባጋጠሟቸው ወቅታዊ ችግሮች ላይ ለመምከር፣ ለዛሬ ረቡዕ ጥር 8 ቀን 2011 ዓ.ም. ስብሰባ ጠሩ፡፡

በተለያዩ ውስብስብ ችግሮች ውስጥ የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ የሪል ስቴት ዘርፍ፣ መሰንበቻውን አዳዲስ ችግሮች ገጥመውታል፡፡

የሪል ስቴት ኩባንያዎች የቤት ሽያጭ ገበያው ብቻ ሳይሆን፣ ተዓማኒነታቸው ጭምር ጥያቄ ውስጥ በመግባቱ፣ ችግሩ በፍጥነት በሚፈታበት መንገድ ላይ ምክትል ከንቲባው እንዲያነጋግሯቸው ሲጠይቁ ሰንብተዋል፡፡

በሪል ስቴት አልሚዎች ጥያቄ መሠረት ምክትል ከንቲባው ስብሰባውን መጥራታቸው ታውቋል፡፡

የሪል ስቴት አልሚዎች በአሁኑ ወቅት የገጠማቸው ችግር ማጠንጠኛ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ከታኅሳስ 8 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ለ15 ቀናት ለሪል ስቴት ኩባንያዎች ምንም ዓይነት አገልግሎት እንደማይሰጥ በማስታወቁ፣ ከዚህ በኋላም በማግሥቱ ታኅሳስ 9 ቀን 2011 ዓ.ም. የፌዴራል ፖሊስ በማዕከልና በአሥሩም ክፍላተ ከተሞች ለሚገኙ የመሬት ተቋማት 28 የሪል ስቴት ኩባንያዎች እንዲታገዱና መረጃዎቻቸውን እንዲልኩለት ደብዳቤ በመጻፉ ነው፡፡

ከዚህ በኋላ በአዲስ አበባ በሚገኙ የሪል ስቴት ኩባንያዎች የገበያ መናጋት፣ የተዓማኒነት ጥያቄና የአገልግሎት አሰጣጥ መቆም ውዥንብር ፈጥሯል፡፡

የሪል ስቴት ኩባንያዎች ሙሉ ለሙሉ በሚያስብል ደረጃ ከደንበኞቻቸው ጋር ውዝግብ ውስጥ የገቡ ሲሆን፣ አብዛኞቹ የተጀመረው ማጣራት በፍጥነት ተጠናቆ አጥፊውና አልሚው ተለይቶ ይፋ እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡

ነገር ግን በ15 ቀናት ውስጥ ማጣራት ተደርጎ አገልግሎት ይሰጣል ከተባለ አንድ ወር ቢቆጠርም፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ባለመጀመሩ በችግር ውስጥ ለሚገኘው ሪል ስቴት ዘርፍ አሳሳቢ መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡

ዛሬ በተጠራው ውይይት የሪል ስቴት ኩባንያዎች ያሉባቸውን ችግሮች ለከተማው ምክትል ከንቲባ በሰፊው ያቀርባሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ በውይይቱ ላይ በአዲስ አበባ ከተማ ትልልቅ ሥራዎችን ያከናወኑ የሪል ስቴት ኩባንያ ባለቤቶች ይገኛሉ ተብሏል፡፡

በተለይ ከ1996 ዓ.ም. ወዲህ 130 የሚጠጉ ሪል ስቴት ኩባንያዎች ከአሥር ሺሕ እስከ 50 ሺሕ ሔክታር መሬት ድረስ ወስደዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች