የባርሴሎና እና የሲዲኒ ኦሊምፒክ የ10 ሺሕ ሜትር ባለወርቋ ደራርቱ ቱሉ ሰሞኑን የምሥራቅ አፍሪካ ዞን አትሌቲክስን በምክትል ፕሬዚዳንትነት ለመምራት ተመርጣለች፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው የዞኑ ጉባዔ ክፍለ አህጉሩን በመወከል የአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን የቦርድ አባል አንድትሆንም መርጧታል፡፡ ባለፈው ኅዳር ወር የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት የነበረው ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ድንገት ሥልጣኑን በፈቃዱ መልቀቁን ተከትሎ ኮሎኔል ደራርቱ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ሆና መሰየሟ ይታወሳል፡፡ ፎቶው ደራርቱ (ከተቀመጡት ከግራ) በተመረጠችበት ጉባዔ ላይ ከሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ሆና ያሳያል፡፡