ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ ‹‹ዓለም ዓቀፍ አዝማሚያዎችና የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ›› በሚል ርዕስ ጥር 6፣ 2011 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሚሲዮኖችና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሚሠሩ ዲፕሎማቶች ባደረጉት ገለጻ ላይ የተናገሩት።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምክንያቱንም እንዲህ አያይዘው ገልጸውታል፡፡ ‹‹የባሕር በር የሌለው በከፍተኛ ኃያላን መንግሥታት እየተወረረ ያለ ቀጣና ውስጥ እንኳን አንሰን፣ ባለንበትኳ መቆም ከባድ ነው፡፡ መፍትሔው ምጣኔያዊ ሀብት ትስስርን ከኤርትራ ከጂቡቲና ከሶማሊያ ጋር መፍጠር ነው፡፡››
ከ1994 ዓ.ም. ጀምሮ በሥራ ላይ ያለው የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነትና አገራዊ ደኅንነት ፖሊሲና ስትራቴጂ እንደሚሻሻል ያወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ፖሊሲው ሲቀረጽ ያልነበሩና አሁን ላይ እየተስፋፉ የመጡት የማኅበራዊ ሚዲያና ሳይበር ቴክኖሎጂ በውጭ ግንኙነቱ ላይ የሚኖረው ጥቅምና ሥጋትም በማሻሻያው ላይ እንደሚካተትም ተናግረዋል።