አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
- አንድ ኪሎ ከግማሽ የተከተፈ የበግ ሥጋ
- 3 መካከለኛ ጭልፋ በቁመቱ የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት
- 1 ኪሎ ግራም በስሱ የተቆረጠ ድንች
- 1 ሊትር ቪጅቴብል ስቶክ (የአትክልት መረቅ)
- 4 የሾርባ ማንኪያ ዘይት
- 1 የሻይ ማንኩያ የደቀቀ ፐርስሊ
- 1 የሻይ ማንኪያ ጨው
- 1 የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
- 3 የሾርባ ማንኪያ የገበታ ቅቤ
አዘገጃጀት
- ሥጋውን የዳቦ መጋገሪያ ትሪ ላይ አድርጐ በጨውና በቁንዶ በርበሬ መለወስ፤
- ድንቹንና ሽንኩርቱን ለብቻው መቀላቀል፤
- የተለወሰውን ሥጋ ከሥር አድርጐ የድንቹንና የሽንኩርቱን ቅልቅል ከላይ ድስት ውስጥ በመጨመር ማልበስ፤
- መረቁን መጨመር (መረቁ ድንቹን መሸፈን የለበትም)፤
- ከላዩ ዘይት መጨመር፤
- ፉርኖ ቤቱን አሙቆ ድስቱን በመክተት እንዲበስል መተው፤
- አልፎ፣ አልፎ ድንቹን በጭልፋ ከሥጋው ጋር እንዲጣበቅ ጫን እያደረጉ እንዲበስል ማድረግ፤
- ሲበስል ድንቹ ላይ ቅቤውን በማቅለጥ አፍስሶ የደቀቀ ፐርስሊ ነስንሶ ለገበታ ማቅረብ፤ ለብቻ ወይም ከቅልቅል አትክልት ጋር ማቅረብ ይቻላል፡፡
- ደብረወርቅ አባተ ‹‹የውጭ ምግቦች አዘገጃጀት›› (1993 ዓ.ም.)