Monday, April 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊ50 በመቶው የእናቶች ሞት ከደም መፍሰስ ጋር የተያያዘ ነው

50 በመቶው የእናቶች ሞት ከደም መፍሰስ ጋር የተያያዘ ነው

ቀን:

20 በመቶ አፍላ ወጣቶች ከ18 ዓመታቸው በፊት ያረግዛሉ

በኢትዮጵያ ለ13ኛ ጊዜ እየተከበረ በሚገኘው የጤናማ እናትነት ወር በአዲስ አበባ ብቻ 50 በመቶ እናቶች ከወሊድ ጋር በተያያዘ የደም መፍሰስና በሚያስከትላቸው ውስብስብ ችግሮች እንደሚሞቱ ተገልጿል፡፡

‹‹በደም መፍሰስ ምክንያት የሚከሰተውን የእናቶች ሞት በጋራ እንከላከል›› በሚል መሪ ቃል የጤናማ እናትነት ወር በዘውዲቱ ሆስፒታል ሲከበር የተገኙት የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዮሐንስ ጫላ (ዶ/ር)፣ በደም መፍሰስ ምክንያት የሚሞቱ እናቶችን ለመታደግ ተጠሪነታቸው ለአዲስ አበባ ጤና ቢሮ በሆኑ 12 ሆስፒታሎችና 97 ጤና ጣቢያዎች ተገልጋይን አክባሪ፣ ሩህሩህና ተንከባካቢ የጤና ባለሙያዎችን ለማፍራት እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ለእናቶች ሞት ቀዳሚ ምክንያት የሆነውን ከእርግዝና ጋር የተያያዘ ደም መፍሰስን ለመግታት፣ የጤና ባለሙያዎች ከሚያደርጉት እገዛ ጎን ለጎን ኅብረተሰቡ ደም እንዲለግስና ባህልን እንዲያደርገው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ አሚር አማን (ዶ/ር)፣ በኢትዮጵያ በጤና ተቋማት የሚወልዱ እናቶች ቁጥር ዝቅተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር አሚር እንደሚሉት፣ 72 በመቶ የሚሆኑ እናቶች በቤት ውስጥ ይወልዳሉ፡፡ ይህም ከመጠን በላይ ለሆነ ደም መፍሰስ ስለሚያጋልጣቸው ለህልፈት የሚዳርጉበት አጋጣሚ በርካታ ነው፡፡

ሚኒስቴሩ የቤት ውስጥ ወሊድን ለማስቀረትና የእናቶችን ሞት ለመቀነስ፣ ጤና ተቋማትን የማስፋፋትና አገልግሎትን የማሳደግ ሥራ እያከናወነ ቢሆንም፣ እናቶች በጤና ተቋም የሚወልዱበት አጋጣሚ ዝቅተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

እናቶች በሕክምና ተቋማት እንዲወልዱ የኅብረተሰቡ ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር አሚር፣ ኅብረተሰቡ እናቶች ከእርግዝና በፊት፣ በእርግዝና ጊዜና በኋላም በጤና ተቋማት ክትትል እንዲያደርጉ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በኢትዮጵያ ከ33 በመቶ በላይ የኅብረተሰቡን ክፍል የሚወክሉት ወጣቶችና አፍላ ወጣቶች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ 40 በመቶው በ18 ዓመታቸው ያገባሉ፡፡

20 በመቶ ያህሉ ደግሞ 18 ዓመት ሳይሞላቸው የሚያረግዙ ሲሆን፣ ለተለያዩ የጤና ችግሮች ተጋላጭነታቸውም የጎላ ነው፡፡ የአፍላ ዕድሜ እርግዝና በአብዛኛው የሚከሰተው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ በሚገኙ፣ ዝቅተኛ የትምህርት ደረጃ ባላቸውና በገጠር አካባቢ በሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ነው፡፡

በአብዛኛው እርግዝናው የሚከሰተው በጋብቻ ምክንያት መሆኑን የጠቆመው መረጃው፣ እርግዝናው የሚያስከትላቸውንም ችግሮች አስፍሯል፡፡

የአፍላ እርግዝና፣ ለከፍተኛ ደም ግፊትና ደም ማነስ፣ ቀኑ ያልደረሰ ሕፃን ለመውለድ፣ ንጽሕናውን ላልጠበቀ የፅንስ ማቋረጥና ለተወሳሰበ ምጥና ፊስቱላ ለመጋለጥና ከማኅበራዊ ሕይወት ለመስተጓጎል ምክንያት ነው፡፡

ችግሩን ለመቆጣጠር የእርግዝና መቆጣጠሪያን እንደ አማራጭ ያቀረበው መረጃው፣ የእርግዝና መቆጣጠሪያ በዓመት ስድስት ሚሊዮን ያልታቀዱ እርግዝናዎችን፣ 2.1 ሚሊዮን ያልታቀዱ ውልደቶችን፣ 3.2 ሚሊዮን የፅንስ ማቋረጥንና 5600 የእናቶች ሞትን ሊያስቀር እንደሚችልም አስፍሯል፡፡

በኢትዮጵያ የእናቶችን ሞት ለመቀነስ የተለያዩ ሥራዎች በመከናወን ላይ ቢሆኑም፣ አሁንም በዓመት ከ11 ሺሕ እስከ 13 ሺሕ የሚሆኑ እናቶች ከወሊድ ጋር በተያያዘ ይሞታሉ፡፡ ከ50 በመቶ በላይ ለሚሆነው የእናቶች ሞት ምክንያቱ ከወሊድ ጋር የተያያዘ ሲሆን፣ ለዚህም ቀዳሚው መንስኤ ደም መፍሰስ ነው፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ30ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ13ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘው የጤናማ እናትነት ወር፣ በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ሲዘከር ዶ/ር አሚር፣ ዶ/ር ዮሐንስና ተጋባዥ እንግዶች ደም ለግሰዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...

‹‹ደስታ›› የተባለችው አማርኛ ተናጋሪ ሮቦት በሳይንስ ሙዚየም

‹‹እንደ ሮቦት ዋነኛው አገልግሎቴ ውስብስብ የሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶችንና አሠራሮችን...