Tuesday, November 29, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -

  ቤቶች ኮርፖሬሽን ያደረገው የንግድ ቤቶች ኪራይ ጭማሪ በድጋሚ እንዲታይ ተከራዮች ጠየቁ

  - ማስታወቂያ -

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ ከተማ በሚያስተዳድራቸው የንግድ ቤቶች ኪራይ ዋጋ ላይ በቅርቡ ያደረገው ጭማሪ የተጋነነ በመሆኑ በድጋሚ እንዲጠና ተከራዮች ጠየቁ፡፡

  በመዲናዋ የሚገኙ 6,635 ተከራዮች በማኅበራቸው አማካይነት ባሰሙት ቅሬታ፣ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ በሚያከራያቸው ቤቶች ላይ እስከ 15 ሺሕ በመቶ የሚደርስ ጭማሪ ማድረጉ የአገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ ያላገናዘበ፣ አገሪቱ የገጠማትን የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ግምት ውስጥ ያላስገባ፣ ባለድርሻ አካላትን ያላሳተፈና በትክክለኛ መረጃ ያልተደገፈ ነው በማለት ታቃውመውታል፡፡

  የንግድ ቤት ተከራዮች አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዮሐንስ አበበ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ኮርፖሬሽኑ ያደረገው የተጋነነ ጭማሪ የኑሮ ውድነቱን በከፍተኛ መጠን የሚያባብስ ነው፡፡ ‹‹በመርህ ደረጃ የኪራይ ጭማሪን የተቃወመ ነጋዴ የለም፡፡ አጨማመሩን በተመለከተ ግን ፍትሐዊ አይደለም፤›› ያሉት አቶ ዮሐንስ፣ ነጋዴው ኅብረተሰብ የተደረገበትን ጭማሪ ለማካካስ በሸማቹ ላይ ተመሳሳይ ጭማሪ የሚያደርግ በመሆኑ የኑሮ ውድነቱን እንደሚያባብስ ገልጸዋል፡፡

  ‹‹የምግብ ቤት፣ የዳቦ ቤትና የሸቀጣ ሸቀጥ መደብር ባለቤቶች የተጣለባቸውን የተጋነነ የኪራይ ተመን ሊሸከሙት ስለማይችሉ በቀጥታ ወደ ኅብረተሰቡ ነው የሚያስተላልፉት፡፡ ይህ ከፍተኛ የኪራይ ጭማሪ የተደረገው መንግሥት ራሱ ኢኮኖሚው ተቀዛቅዟል እያለ ባለበት ወቅት መሆኑ ግራ አጋብቶናል፤›› ያሉት አቶ ዮሐንስ፣ ኮርፖሬሽኑ ያደረገውን ጭማሪ መነሻ በማድረግ በከተማዋ የሚገኙ የግል ሕንፃ አከራዮችም የዋጋ ጭማሪ ማድረግ መጀመራቸውን ገልጸው፣ ይህም የገበያ አለመረጋጋት እየፈጠረ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

  ከደንበኞች የቀረበውን ቅሬታ በመመልከት የቤቶች ኮርፖሬሽን ባደረገው ጭማሪ ላይ ማሻሻያ ቢያደርግም፣ በደንበኞቹ ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም፡፡ ኮርፖሬሽኑ የተደረገውን የኪራይ ተመን ጭማሪ ተከራዮች በሦስት ዓመት እንዲከፍሉ የሚያስችል ማሻሻያ ቢያደርግም፣ ተከራዮች ተቃውሟቸውን በማኅበራቸው በኩል ማሰማታቸውን ቀጥለዋል፡፡

  ‹‹ተደረገ የተባለው ማሻሻያ ምንም ለውጥ የለውም፡፡ እኛ አሁን የምንጠይቀው ኮርፖሬሽኑ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ የዋጋ ማሻሻያ ጥናት በድጋሚ እንዲሠራ ነው፤›› ብለዋል አቶ ዮሐንስ፡፡

  ኮርፖሬሽኑ በቅርቡ ባወጣው መግለጫ የክፍያ ተመን ማስተካከያ ሳያደርግ ለበርካታ ዓመታት በመዝለቁ፣ የኪራይ ዋጋው ከወቅቱ የገበያ ሁኔታ ጋር የማይጣጣም ሆኖ እንዳገኘው ገልጿል፡፡ ‹‹የኪራይ ተመኑ ከግሉ ዘርፍ ጋር ከፍተኛ ልዩነት ያለው በመሆኑ የንግድ ውድድሩ እንዲዛባ አድርጓል፤›› ብሏል ኮርፖሬሽኑ፡፡ አሁም ቢሆን ያወጣው የኪራይ ተመን ከግሉ ዘርፍ ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ እንደሆነ አስታውቋል፡፡

  የፌዴራል ኪራይ ቤቶች ኮርፖሬሸን የንግድ ቤት ተከራዮች ማኅበር ባወጣው መግለጫ የተላለፈው የቤት ኪራይ ጭማሪ እንዲታገድ፣ የንግዱን ማኅበረሰብ የሚወክሉ ባለሙያዎችን ያሳተፈ ጥናት እንዲሠራ ጠይቋል፡፡ ማኅበሩ ጉዳዩን አስመልክቶ ረቡዕ ጥር 15 ቀን 2011 ዓ.ም. በግሎባል ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡

  በቅርቡ የመንግሥት ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ረሻድ ከማል ለፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ ያቀረቡትን ሪፖርት አስመልክቶ የቋሚ ኮሚቴው አባላት በሰጡት አስተያየት፣ ኮርፖሬሽኑ በቅርቡ በንግድ ቤቶች ላይ ያደረገው ጭማሪ ተመጣጣኝና አቅምን ያገናዘበ ነው ማለታቸው ይታወሳል፡፡ ተከራዮች እያሰሙት ያለው ተቃውሞ ተቀባይነት የሌለውና ወቅቱን ያላገናዘበ መሆኑን በወቅቱ ጠቁመዋል፡፡ ከፍተኛ ጭማሪ እንደተደረገ በማስመሰል እየቀረበ ያለው ቅሬታና ተቃውሞ ተቀባይነት የሚኖረው፣ የንግድ ቤቶቹ በጨረታ ተከራይተው ከሚገኙ ቤቶች ጋር በማወዳደር ዋጋቸው በልጦ ከተገኘ ብቻ ሲሆን መሆኑን የቋሚ ኮሚቴው አባላት አስተያየት መስጠታቸው አይዘነጋም፡፡

  spot_img
  - Advertisement -spot_img

  የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

  - ማስታወቂያ -

  በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች