Tuesday, July 23, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የመሬት ሊዝ ጨረታ ለማውጣት ዝግጅት እየተደረገ ነው

ተዛማጅ ፅሁፎች

ለተለያዩ ግንባታዎች መሬት በሊዝ ጨረታና በምደባ ከማቅረብ ተቆጥቦ የቆየው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ከሳምንታት በኋላ በርካታ ቦታዎችን በጨረታ ለማቅረብ እየተዘጋጀ መሆኑ ተመለከተ፡፡

ምክትል ከንቲባ ታከሉ ኡማ (ኢንጂነር) የከተማውን ቁልፍ በተረከቡ ማግሥት በመሬትና መሬት ነክ አገልግሎቶች የተንሠራፋው ብልሹ አሠራር እስኪስተካከል ድረስ፣ የመሬት አቅርቦትም ሆነ አገልግሎት አሰጣጥ እንዲቆም አድርገው ነበር፡፡

በዚህ መሠረት ሐምሌ 21 ቀን 2010 ዓ.ም. የወጣውና በሒደት ላይ የነበረው 30ኛው የሊዝ ጨረታ ታግዷል፡፡

ከዚያ በኋላ ላለፉት ሰባት ወራት የመሬት ሊዝ ጨረታ አልወጣም፣ ለግል ባለሀብቶችም በምደባ (በድርድር) መሬት አልቀረበም፡፡

ከ2011 ዓ.ም. በፊት በነበሩት ሁለት ዓመታትም ቢሆን በከተማ አስተዳደሩ ዕቅድ መሠረት መሬት ለገበያ አልቀረበም፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት በየወሩ በሊዝ ጨረታ ለማቅረብ ቢያቅድም፣ ከ2009 ዓ.ም. ጀምሮ ለጨረታ መሬት የቀረበው ሦስት ጊዜ ብቻ ነው፡፡

የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመያዝ የሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካወጣቸው ደንብና መመርያዎች ጋር የሚጣረስ በመሆኑ፣ ግዙፍ የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን ለመገንባት መሬት በድርድር እንዲሰጣቸው የጠየቁ ባለሀብቶች ካለመስተናገዳቸውም በላይ፣ የከተማ አስተዳደሩ ለኢንዱስትሪ ግንባታ በተናጠል የሚቀርብ የቦታ ጥያቄ ማስተናገድ በማቆሙ ባለኢንዱስትሪዎችም አልተስተናገዱም፡፡

ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ራሱን መልሶ በማደራጀት ላይ የሚገኘው የከተማው መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ የሚያካሂደውን ሪፎርም እያገባደደና የመሬት ዝግጅቱንም ጎን ለጎን እያከናወነ የሚገኝ በመሆኑ፣ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ መሬት ለገበያ እንደሚያቀርብ ተመልክቷል፡፡

በተጨማሪም በሚቀጥሉት ዓመታት በመኖሪያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበራት አማካይነት ለሚካሄዱ የመኖሪያ ቤት ግንባታዎች የሚሆን አንድ ሺሕ ሔክታር መሬት እየተዘጋጀ መሆኑን ከከተማ አስተዳደሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች