የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ ላፀደቃቸው የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽንና ለዕርቀ ሰላም ኮሚሽን አባልነት፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ታጭተው የቀረቡለትን ግለሰቦች በአብላጫ ድምፅ አፀደቀ።
ምክር ቤቱ ማክሰኞ ጥር 28 ቀን 2011 ዓ.ም. ከቀትር በኃላ ባካሄደው ስብሰባው አስቀድሞ የተመለከተው፣ ለአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን በዕጩነት የቀረቡለትን 41 አባላት ነው።
ለምክር ቤቱ ተልኮ በነበረው በጠቅላይ ሚኒስትሩ የታጩ አባላት ዝርዝር ውስጥ ስምንት ያህሉ በተለያዩ ምክንያቶች በሌሎች ዕጩዎች እንዲተኩ መደረጉን፣ በምክር ቤቱ የመንግሥት ተጠሪ ተገልጾ ማንነታቸው ተዋውቋል።
የዕጩዎቹ ዝርዝር በተለያዩ ሚዲያዎች ቀድሞ ሲገለጽ፣ አንዳንዶቹ ፈቃደኝነታቸው ሳይጠየቅ የታጩ መሆናቸውን በማኅበራዊ ድረ ገጾች ሲገልጹ ነበር፡፡
ከእነዚህም መካከል በአዲስ አበባ የዩኒቨርሲቲ የፌዴራሊዝም መምህር አሰፋ ፍሰሐ (ዶ/ር) አንዱ ናቸው።
ለምክር ቤቱ ተልኮ ከነበረው ዝርዝር ውስጥ እንዲተኩ የተደረጉ ስምንት ዕጩዎች በቀለ ከተማ (ፕሮፌሰር)፣ አቶ ፋንታሁን አየነው፣ ብርሃኑ በላይ (ዶ/ር)፣ አምባሳደር አብዱል ዋሴ፣ አሰፋ ፍስሐ (ዶ/ር)፣ ዳዊት መኮንን (ዶ/ር)፣ ይሰሐቅ አሰፋ (ፕሮፌሰር)፣ ዳዊት ወንድማገኝ (ዶ/ር) ናቸው።
የምክር ቤቱ አባላት በቀረቡት ዕጩዎች ላይ ካሰሟቸው የተቃውሞ አስተያየቶች መካከል በዕጩነት የቀረቡት አባላት ሙሉ በመሉ ገለልተኛ አይደሉም የሚል ሲሆን፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና ፖለቲከኞች በዕጩነት መቅረባቸው ተገቢ አለመሆኑን በመግለጽ ተከራክረዋል።
በሌላ በኩል የአስተዳደር ወሰን ጥያቄ ከሚነሳባቸው አካባቢዎች በተወሰነ መጠን ሲወከሉ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ጭራሹኑ ባለመወከላቸው ሚዛን የጠበቀ አለመሆኑን ክርክር አድረገዋል፡፡
ዕጩዎቹ የብሔር ወይም የማንነት ውክልናን እንዲያሟሉ ሳይሆን በእውቀት ላይ በመመሥረት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ መሆኑን፣ ኃላፊነቱንም የሚወጡት በጋራ በሚሰጡት ውሳኔ እንደሆነ በመንግሥት ተጠሪው በኩል ምላሽና ማብራሪያ ተስጥቷል።
ቀጥሎ ለቀረበው የዕርቀ ሰላም ኮሚሽን በዕጩነት 42 አባላት የቀረቡ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ላይ ተቃውሞ በልዩ ሁኔታ ቀርቧል።
ምክር ቤቱ የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን የቀረቡትን አባላት በ22 ተቃውሞና በአራት ድምፅ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ ሲያፀድቅ፣ ለዕርቀ ሰላም ኮሚሽን የቀረቡትን አባላት በ16 ተቃውሞ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል፡፡
ለአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን የተሰየሙ አባላት ዝርዝር
- ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) – የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት
- ጥላሁን እንግዳ (ፕሮፌሰር) – የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር
- ጣሰው ገብሬ (ዶ/ር) – የቀድሞው የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት
- ወ/ሮ መዓዛ ብሩ – ጋዜጠኛ
- አምባሳደር ሸምሰዲን አህመድ – ዲፕሎማት
- ኦባንግ ሜቶ (ዶ/ር) – የሰብዓዊ መብት ተሟጋች
- መስፍን አርአያ (ዶ/ር) – በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሕክምና ባለሙያ
- ወ/ሮ አማረች አግደው – አማካሪ
- ኡስታዝ አቡበከር አህመድ – የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ አማካሪ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ
- ወልደ አምላክ በእውቀት (ፕሮፌሰር) – የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር
- ነጋሶ ጊዳዳ (ዶ/ር) – ፖለቲከኛና የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት
- ወ/ሮ ራሔል መኩሪያ –
- ያዕቆብ አርሳኖ (ዶ/ር) – ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
- አረጋዊ በርሔ (ዶ/ር) – ፖለቲከኛ
- ደመቀ አጭሶ (ዶ/ር) – ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
- ካሳሁን ብርሃኑ – ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
- ገብሩ ታረቀ (ፕሮፌሰር) – ፖለቲከኛ
- ያዕቆብ ኃይለ ማርያም (ዶ/ር) – ፖለቲከኛ
- በቀለ ቡላዶ (ዶ/ር) – የሜቴክ የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር
- አቶ ሌንጮ ለታ – ፖለቲከኛ
- መረራ ጉዲና (ፕሮፌሰር) – ፖለቲከኛና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
- አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ – ፖለቲከኛ
- አቶ ጉደታ ገለልቻ –
- አቶ አበበ እሸቱ – ፖለቲከኛ
- ጳውሎስ ሊቃ (ዶ/ር) – የሕክምና ባለሙያ
- አቶ ብርሃኑ ተስፋዬ – የሕክምና ባለሙያ
- ፍሰሐ ጽዮን መንግሥቱ (ፕሮፌሰር) – ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
- አበራ ደገፉ (ዶ/ር) – መምህር
- በቀለ ጉተማ (ፕሮፌሰር) – ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
- አቶ የሺዋስ አሰፋ – ፖለቲከኛ
- አቶ ውብሸት ሙላት – የሕግ ባለሙያ
- ወ/ሮ ወርቅነሽ ዳባ
- አቶ ዘገየ አስፋው
- አሸብር ወ/ጊዮርጊስ (ዶ/ር)
- ዳዊት መኮንን (ዶ/ር)
- አቶ ባዩ በዛብህ
- አቶ በለጠ ሞላ
- አቶ ዮናስ ዘውዴ
- አብዱልባሲጥ ምንዳዳ
- አብዱራሂም መሐመድ
- በላይ ንጉሤ (ዶ/ር)
ለዕርቀ ሰላም ኮሚሽን የተሰየሙ አባላት ዝርዝር
- ብፅዕ አቡነ አብርሃም – ከኦርቶዶክስ
- ካርዲናል ብርሃነ እየሱስ – ከካቶሊክ
- ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር እድሪስ – ከእስልምና
- ቤተ መንግሥቱ (ዶ/ር) – ከወንጌላዊያን
- ፓስተር ተስፋዬ ጋቢሶ – ከወንጌላዊያን
- ኡስታዝ አህመዲን ጀበል – ከእስልምና ወጣት ምሁራን
- አቶ ታምሩ ለጋ – ከኦርቶዶክስ ወጣት ምሁራን
- አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ – የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር
- ምሕረት ደበበ (ዶ/ር) – ከሐሳብ መሪዎች
- መጋቢ ሀዲስ እሸቱ ዓለማየሁ – ከሐሳብ መሪዎች
- ጥበበ የማነ ብርሃን (የተከበሩ የዓለም ሎሬት ዶ/ር) – ከምሁራን
- በየነ ጴጥሮስ (ፕሮፌሰር) – ፖለቲከኛ
- አበራ ዴሬሳ (ዶ/ር) – ከምሁራን
- ኡባህ አደም (ዶ/ር) – ከምሁራን
- ደስታ ሓምቶ (ፕሮፌሰር) – ከምሁራን
- አሰፋ ኃይለ ማርያም (ፕሮፌሰር) – ከምሁራን
- ደረጀ ገረፋ (ዶ/ር) – ከምሁራን
- አቶ ደበበ እሸቱ – ከኪነ ጥበብ ባለሙያዎች
- ሙሴ ያዕቆብ (ዶ/ር) – ደራሲ
- ወ/ሪት ብሌን ሳህሉ – የሕግ ባለሙያ
- አቶ ታምራት ኪዳነ ማርያም – የሕግ ባለሙያ
- ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም – ከአገር ሽማግሌዎች
- ቦጋለች ገብሬ (ዶ/ር) – በደቡብ ኢትዮጵያ ታዋቂ የበጎ አድራጎት ሰው
- አቶ አባተ ኪሾ – ከሲዳማ የአገር ሽማግሌዎች
- ካኦ ደምሴ – ከአገር ሽማግሌዎች
- ብርሃኑ ነጋ (ዶ/ር) – ፖለቲከኛ
- ደራሲ አያልነህ ሙላቱ – ከኪነ ጥበብ
- አትሌት ደራርቱ ቱሉ – የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
- ግደይ ዘርዓጽዮን (ዶ/ር) – ፖለቲከኛ
- አህመድ ዘከርያ (ፕሮፌሰር) – ከምሁራን
- ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ – ከታዋቂ ሰዎች
- ሡልጣን ሀንፍሬ አሊሚራህ – ከአገር ሽማግሌዎች
- አትሌት ገብረ እግዚአብሔር ገብረማርያም – ከአትሌቶች
- ልዑል በዕደ ማርያም መኮንን – ከታዋቂ ሰዎች
- ወ/ሮ ትርሐስ መዝገበ – ከበጎ አድራጎት
- ደስታ ሐምቶ (ፕሮፌሰር)
- አቶ ዳሮታ ደጃሞ
- አባ ገዳ ጎበና ሆላ
- ኃይለ ማርያም ካህሳይ (ዶ/ር)
- ዘረሰናይ ዓለምሰገድ (ዶ/ር)
- ሰሎሞን አየለ ደርሶ (ዶ/ር)
- ወ/ሮ የትነበርሽ ንጉሤ