የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ሐሙስ ጥር 30 ቀን 2011 ዓ.ም. ባደረገው መደበኛ ስብሰባ፣ የ12 የምክር ቤት አመራር አባላትን ያለ መከሰስ መብት አነሳ፡፡ ያለ መከሰስ መብታቸው ከተነሳባቸው የምክር ቤት አባላት ውስጥ፣ ስድስቱ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ምንጮች ለሪፖርተር አረጋግጠዋል፡፡
ያመለከሰስ መብታቸው የተነሳው የምክር ቤት አባላት፣
1. አቶ መሐመድ ረሺድ ኢሳቅ – የቀድሞ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ
2. አቶ ከደር አብዲ – የቀድሞ ንግድና ኢንዱስተሪ ቢሮ ኃላፊና የሶሕዴፖ ማዕከላዊ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ
3. አቶ አህመድ አብዲ – የክልሉ የቀድሞ የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊና የክልሉ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ከሥልጣናቸው ሲለቁ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የነበሩ
4. ወ/ሮ ፈርቱን አብዲ መህዲ – የውኃ ልማት ቢሮ ኃላፊ
5. ወ/ሮ ሱአድ አህመድ ፋራህ – የቀድሞ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር
6. አቶ አብዲሀሊም መሐመድ – የውኃ ልማት ምክትል ቢሮ ኃላፊ
7. ወ/ሮ ማጅዳ መሐመድ – የርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ
8. ወ/ሮ አያን ጉላንዴ – የጎዴ ከተማ የፋይናንስና አስተዳድር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ
9. አቶ መሐሙድ ሔርዮ – የትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ
10. አቶ አብዲ መሐመድ አባስ – የአርብቶ አርደርና ገጠር ልማት ቢሮ ኃላፊ
11. አቶ መሐመድ ቢሌ (ሚግ) – የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ
12. ወ/ሮ ነስራ ሐሰን – የርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት አማካሪ የነበሩ ናቸው፡፡
ያለ መከሰስ መብታቸው ከተነሳው ውስጥ ወ/ሮ ፈርቱን አብዲና አቶ አህመድ አብዲ ከአገር ውጭ መሆናቸው ታውቋል፡፡
ያለ መከሰስ መብታቸው ከተነሳባቸው አመራሮች በተጨማሪ፣ ስምንት የክልሉ ባለሥልጣናት በቁጥጥር ሥር እንደሚውሉ ምንጮች ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡