Thursday, December 1, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናበጎንደር የተሰማራው የመከላከያ ኃይል አምስት ሰዎችን በቁጥጥር ሥር አዋለ

  በጎንደር የተሰማራው የመከላከያ ኃይል አምስት ሰዎችን በቁጥጥር ሥር አዋለ

  ቀን:

  ከእሑድ የካቲት 10 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ በአማራ ክልል በምዕራብና በማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች የተፈጠረውን የፀጥታ ችግርና ግጭት ለማረጋጋት በአካባቢው የተሰማራው የመከላከያ ሠራዊት፣ አምስት ግለሰቦችን ከእነ ትጥቃቸው በቁጥጥር ሥር ማዋሉ ታወቀ፡፡

  በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል ሁለቱ በግድያ፣ ሁለቱ ሁከት በማነሳሳትና አንዱ በፀጥታ ማስከበር ሥራ ላይ የተሰማራ ፓትሮል ላይ በመተኮስ ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥራ መዋላቸውን፣ በአገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ 33ኛ ዓባይ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ዓለሙ አየለ ለሪፖርተር አስታውቀዋል፡፡

  ሠራዊቱ በአካባቢው ከተሰማራ ወዲህ የፀጥታ ሁኔታው መሻሻል ማሳየቱን የገለጹት ዋና አዛዡ፣ አሁንም ቢሆን ግን በሰዎች ዘንድ የፀጥታ ሥጋት በመኖሩ ሙሉ በሙሉ ወደነበረበት አለመመለሱን ገልጸዋል፡፡

  በሠራዊቱ የሰላም ማስከበር ተግባርም የአስፋልትም ሆነ የገጠር መንገዶች መከፈታቸውን፣ እንዲሁም የተዘጉ የመንግሥት ተቋማት አገልግሎት እንዲጀምሩ ለማስቻል እየተሠራ እንደሚገኝ ብርጋዴር ጄኔራል ዓለሙ አስረድተዋል፡፡

  በየደረጃው ከክልል እስከ ቀበሌ የኮማንድ ፖስት አደረጃጀት መዘርጋቱን ገልጸውም፣ የሚዲያ ተደራሽነት በሌለባቸው የገጠር አካባቢዎች ስለፀጥታና ሰላም ማስከበር ከኅብረተሰቡ ስለሚጠበቁ ተግባራት ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ በትብብር እየተከናወነ ነው ሲሉ አክለዋል፡፡

  በምዕራብና በማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች በተፈጠረ ግጭትና የፀጥታ ችግር የአገር መከላከያ ሠራዊት እንዲገባ መደረጉ የሚታወቅ ሲሆን፣ የዚህ ዓላማም ከግጭቶች ጋር ተያይዞ መንገዶችን ማስከፈት፣ በግጭቶች ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች ሕጋዊ ከለላና ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደ ቀዬያቸው እንዲመለሱ ማድረግና በድርጊቱ የተሳተፉትን በቁጥጥር ሥር ማዋል ናቸው፡፡

  በዚህም መሠረት በመንገዶች ግራና ቀኝ አምስት ኪሎ ሜትሮች ዙሪያ የጦር መሣሪያ ታጥቆ መንቀሳቀስ ሙሉ ለሙሉ የተከለከለ ሲሆን፣ ይኼንን ተላልፎ የሚገኝ ኃይል በቁጥጥር ሥር እንደሚውል፣ ከዚህ በላይ ከሆነም ተመጣጣኝ የሆነ ኃይል ዕርምጃ እንደሚወሰድበት ዋና አዛዡ ለሪፖርተር አብራርተዋል፡፡

  ነገር ግን ይህ ተልዕኮ በጅምላ ትጥቅ የማስፈታት ተልዕኮ እንደሌለውና ማንም ትጥቁን ይዞ አካባቢውን መጠበቅ እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

  በተጠርጣሪነት ከተያዙ ግለሰቦች እጅ አምስት የክላሽኒኮቭ መሣሪያዎች መያዛቸው፣ ከዚህ በተጨማሪ 130 ያህል ከቀዬአቸው የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ዕርቀ ሰላም በማውረድ ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ መደረጉ ታውቋል፡፡  

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...