Friday, December 1, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

መንግሥት ተጨማሪ 400 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ስንዴ ግዥ ሊፈጽም ነው

ተዛማጅ ፅሁፎች

በአገሪቱ ባጋጠመ የስንዴ እጥረት ምክንያት መንግሥት ተጨማሪ 400 ሺሕ ሜትሪክ ስንዴ ግዥ ሊፈጽም መሆኑ ታወቀ፡፡ ግዥውን የሚያከናውነው የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ነው፡፡

ከሳምንታት በፊት በተከፈተ የስንዴ ግዥ ጨረታ ሦስት የውጭ ኩባንያዎች፣ 400 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ስንዴ በ3.5 ቢሊዮን ብር እንዲያቀርቡ መጠየቁ ይታወሳል፡፡

በጨረታው ያሸነፉት አምሮፓ፣ ኤዲኤም ኢንተርናሽናልና ቡንጂ ኤስኤ የተባሉ ኩባንያዎች ሲሆኑ፣ ስንዴውን በተጠቀሰው ዋጋ እንዲያቀርቡ ተጠይቀዋል፡፡

በዚህም ቡንጂ የተባለው ኩባንያው ከአጠቃላዩ የስንዴ መጠን ግማሹን (200 ሺሕ ሜትሪክ ቶን) በ61.7 ሚሊዮን ዶላር እንዲያቀርብ የተጠየቀ ሲሆን፣ አምሮፓ በ29.9 ሚሊዮን ዶላር፣ እንዲሁም ኤዲኤም በ30.84 ሚሊዮን ዶላር በነፍስ ወከፍ 100 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ስንዴ እንዲያቀርቡ መጠየቃቸው አይዘነጋም፡፡

ነገር ግን በጨረታው አነስተኛ ዋጋ አቅርቦ የነበረው ዊፋግ መብሩክና አፕላስ የተባሉ የሁለት ኩባንያዎች ጥምረት ጨረታውን ማሸነፍ ይገባናል በማለት፣ ቅሬታቸውን ለመንግሥት ግዥዎችና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ አቅርበው ነበር፡፡

ዊፋግ በጨረታው አነስተኛ ዋጋ ያቅርብ እንጂ፣ በነበረው የቴክኒክ ግምገማ ከሕጋዊነት ጋር በተያያዘ መመዘኛዎችን ባለማለፉ ጨረታውን መውደቁ ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለገንዘብ ሚኒስቴር ያቀረበው አዲሱ የ400 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ስንዴ ግዥ ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ መንግሥቱ ከበደ ግዥው መጠየቁን ለሪፖርተር አረጋጋጠዋል፡፡

አሁን በግዥ ሒደት ላይ ያለው 400 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ስንዴና ፈቃድ ያገኘው ተጨማሪ 400 ሺሕ ሜትሪክ ስንዴ ግዥ፣ በአገሪቱ የተፈጠረውን እጥረት ያረጋጋል ተብሏል፡፡

የንግድ ሥራ ኮርፖሬሽን ባለፉት ሦስት ወራት ካከፋፈለው 100 ሺሕ ሜትሪክ ስንዴ በተጨማሪ፣ ሌላ 100 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ስንዴ በሳምንታት ውስጥ ወደ አገር ውስጥ አስገብቶ ለተጠቃሚዎች እንደሚያከፋፍል ተገልጿል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በየወሩ 650 ሺሕ ኩንታል ስንዴ ለዱቄት ፋብሪካዎችና ለመንግሥት ተቋማት እንደሚያከፋፍል ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች