Sunday, June 16, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ከቡና ሻይና ቅመማ ቅመም በሰባት ወራት ውስጥ ከ370 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተገኝቷል

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

በ2011 በጀት ዓመት ሰባት ወራት ውስጥ 157,513.62 ቶን የቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ምርት በመላክ 548.92 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 120,006.14 ቶን (ከዕቅዱ 76.19 በመቶ) በመላክ 374.73 ሚሊዮን ዶላር ወይም የዕቅዱን 68.27 በመቶ ገቢ እንደተገኘ ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን የተገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡

ባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ለውጭ ገበያ ከተላከው አኳያ ሲነፃፀር በመጠን የ6,628.89 ቶን ወይም 5.23 በመቶ እንዲሁም በገቢ በኩል የ57.99 ሚሊዮን ዶላር ወይም የ13.40 በመቶ ቅናሽ ተመዝግቦበታል፡፡

በጥር ወር ብቻ 16,546.86 ቶን የቡና ምርት በመላክ 59.27 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ቢታቀድም፣ 11,165.50 ቶን ቡና (ከዕቅዱ 67.48 በመቶ የተፈጸመበት) በመላክ 33.66 ሚሊዮን ዶላር ወይም 56.80 በመቶ ገቢ ተገኝቷል፡፡ የወሩ አፈጻጸም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነፃፀር በመጠን የ2,342.14 ቶን (17.34 በመቶ)  እና በገቢ 19.74 በመቶ ቅናሽ አሳቷል፡፡

በበጀት ዓመቱ ሰባት ወራት 147,992.57 ቶን የቡና ምርት በመላክ 534.37 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 114,273.46 ቶን ቡና (ከዕቅዱ 77.22 በመቶ) በመላክ 367.60 ሚሊዮን ዶላር (ከዕቅዱ 68.79 በመቶ) ገቢ ተገኝቷል፡፡ አፈጻጸሙ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በመጠን የ6,536.81 ቶን (5.41 በመቶ) እና የ56.18 ሚሊዮን ዶላር ወይም የ13.26 በመቶ ቅናሽ አስመዝግቧል፡፡  

በጥር ወር 569.534 ቶን የቅመማ ቅመም ምርት በመላክ 0.77 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 161.54 ቶን የቅመማ ቅመም ምርት (ከዕቅዱ 28.36 በመቶ) ተልኮ 0.22 ሚሊዮን ዶላር (ከዕቅዱ 28.54 በመቶ) ገቢ ተገኝቷል፡፡ የ2011 በጀት ዓመት የጥር ወር አፈጻጸም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነፃፀር በመጠን 173.48 ቶንና በገቢ 0.23 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ አሳይቷል፡፡

በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሰባት ወራት 7,742.93 ቶን የቅመማ ቅመም ምርት በመላክ 10.81 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 4,530.19 ቶን የቅመማ ቅመም ምርት (ከዕቅዱ 58.51 በመቶ) ተልኮ 5.16 ሚሊዮን ዶላር (ከዕቅዱ 47.77 በመቶ) ገቢ ተገኝቷል፡፡ የ2011 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሰባት ወራት አፈጻጸም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በመጠን 24.47 ቶንና በገቢ 1.2 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ አሳይቷል፡፡

በጥር ወር 17,386.74 ቶን የቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ምርት በመላክ 60.69 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 11,545.42 ቶን (ከዕቅዱ 66.40 በመቶ) በመላክ 34.20 ሚሊዮን ዶላር (ከዕቅዱ 56.34 በመቶ) ገቢ ተገኝቷል፡፡ አፈጻጸሙ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወር ከተላከው ጋር ሲነፃፀር በመጠን 2,490.35 (17.74 በመቶ) ቶን ቅናሽና በገቢ ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ አፈጻጸም ተመዝግቧል፡፡

በጠቅላላው በሁሉም ምርቶች ዘንድ የታየው አፈጻጸም ከወትሮውም ከታቀደው አኳያ በገቢም ሆነ በመጠን ቅናሽ የተመዘገበበት ሆኗል፡፡ በስድስት ወራት የዘርፉ የወጪ ንግድ አፈጻጸም መሠረት ከቡና፣ ከሻይና ከቅመማ ቅመም ከ340 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱ መዘገባችን ይታወሳል፡፡ በመንፈቅ ዓመት ወደ 132 ሺሕ ቶን ገደማ በላይ ቡና ወደ ውጭ በመላክ ከ475 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ እንደሚገኝ ቢታቀድም፣ በውጤቱ ግን 103 ሺሕ ቶን በመላክ 334 ሚሊዮን ዶላር ገደማ መገኘቱን መዘገባችን  ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች