Thursday, June 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምሱዳን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ

ሱዳን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ

ቀን:

የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር በአገሪቱ ከሁለት ወር በፊት የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ አስከትሎ የአንድ ዓመት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል፡፡

መንግሥት ነዳጅና ዳቦ ላይ የሚያደርገውን ድጎማ ከሁለት ወር በፊት ማቋረጡን የተቃወሙ ሱዳናውያን፣ በተለያዩ ጊዜያት ተቃውሞ እየወጡ መንግሥትን ሲያስጨንቁ ፕሬዚዳንቱ በሽር ዝምታን መርጠው ነበር፡፡ ሆኖም ‹‹በኑሮ ተወደደ›› የተቀሰቀሰው ተቃውሞ አቅጣጫውን ለ30 ዓመታት በሥልጣን የቆዩትን አልበሽርን ወደመገርሰሱ በመቀየሩ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለመታወጁ ምክንያት ነው ተብሏል፡፡

ፕሬዚዳንት አልበሽር ቅዳሜ የካቲት 15 ቀን 2011 ዓ.ም. ለሕዝቡ በሰጡት የቴሌቪዥን መግለጫ፣ የ18 ግዛቶችን አስተዳዳሪዎች ከሥልጣን ማንሳታቸውን አስታውቀዋል፡፡

ከቆይታ በኋላም ከሥልጣን በተነሱት ምትክ የደኅንነት አካላት መተካታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የሱዳን የደኅንነት ቢሮ አገልግሎት፣ ፕሬዚዳንቱ መግለጫ ከመስጠታቸው አስቀድሞ፣ ‹‹ሚስተር አልበሽር ከሥልጣን ሊወርዱ ይችላሉ›› ብሎ ነበር፡፡

የዓረቡን ዓለም ከአምስት ዓመታት በፊት የናጠውና ዛሬም በሶሪያ፣ በሊቢያና በየመን አላባራ ካለው ‹‹ዓረብ ስፕሪንግ›› ጋር ተመሳሳይነት አለው የተባለው የሱዳን አመፅ፣ ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ አልበሽርን በመቃወም ላይ አነጣጥሯል፡፡

ሱዳን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ

 

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀም በኋላ ተቃዋሚዎች በኦምዱራማን ከተማ መውጣታቸው፣ ነገር ግን በፖሊስ የአስለቃሽ ጭስ መበተናቸው ታውቋል፡፡

ፕሬዚዳንቱም፣ ፓርላማው ሕገመንግሥቱን ለማሻሻል የያዘውን ቀጠሮ እንዲያራዝም ጠይቀዋል፡፡ የሕገመንግሥቱ መሻሻል ያስፈለገውም አልበሽርን ለቀጣይ ዙር በምርጫ እንዲወዳደሩ ሕገመንግሥታዊ ዕውቅና ለመስጠት ነበር፡፡

ተቃዋሚዎች አገሪቷን ለማናወጥ መነሳታቸውን የሚናገሩት አልበሽር፣ ‹‹አገሪቷ ለአንድ ዓመት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ትቆያለች፡፡ በፌዴራልም ሆነ በአስተዳደሮች ደረጃ መንግሥት ፈርሷል፤›› ብለዋል፡፡

ከሥልጣን በተነሱት 18 አስተዳዳሪዎች ምትክ በመከላከያና በደኅንነት አባላት እንዲተዳደሩ ሹመት የሰጡ ሲሆን፣ ከተሰናባቹ ካቢኔ ውስጥም የውጭ ጉዳይ፣ መከላከያና ፍትሕን ጨምሮ አምስት ሚኒስትሮች ሥራ ላይ እንዲቆዩ ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡

ለ30 ዓመታት በሥልጣን በቆዩት አልበሽር ላይ እንዲህ ለረዥም ጊዜ የአደባባይ ተቃውሞ የገጠማቸው ከ2018 ማብቂያ ጀምሮ ሲሆን፣ በዚህም ከአንድ ሺሕ በላይ ተቃዋሚዎች ታስረዋል፡፡ ከ40 በላይ ደግሞ ከደኅንነት አካላት ጋር በተፈጠረ ግጭት ሞተዋል፡፡

አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንዳሰፈረው፣ ሚስተር አልበሽር ከሥልጣን እስካልወረዱ ድረስ በሱዳን የተጀመረውን ተቃውሞ ማንም እንደማያስቆመው የሠልፉ አስተባባሪዎች ተናግረዋል፡፡

እ.ኤ.አ. በ1989 በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን የተቆናጠጡት የ75 ዓመቱ አልበሽር፣ ሥልጣንን ላለፉት 30 ዓመታት ሙጥኝ ብለው መያዛቸው ሲያስተቻቸው ቆይቷል፡፡ ሱዳናውያንም የአልበሸርን በሥልጣን ለረዥም ጊዜ መቆየት ተቃውመዋል፡፡ ምንም እንኳን ተቃውሞው የተነሳው ከኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ ቢሆንም፣ እንደ ዓረብ ስፕሪንግ ተቃውሞውም እያየለ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅም ምክንያት ሆኗል፡፡

ከወር በፊት ግብፅን የጎበኙት አልበሸር፣ በሱዳን ያለው ተቃውሞ ከዓረብ ስፕሪንግ የተኮረጀ ነው ብለው ነበር፡፡

እ.ኤ.አ. በ2011 በግብፅ የተቀሰቀሰው አመፅ በ18 ቀናት ውስጥ ከሁለት አሠርት በላይ ግብፅን ገዙትን ሆስኒ ሙባረክ ከሥልጣን ያወረደ ቢሆንም፣ በወቅቱ በሱዳን ተቀስቅሶ የነበረው አመፅ ብዙም ሳይራመድ ነበር የተቀጨው፡፡ አሁን ላይ ደግሞ በሙያ ማኅበራት ጭምር ተጠናክሮ በሽር ላይ ያነጣጠረው ተቃውሞ ቀጥሏል፡፡

የሱዳን የፀጥታ ኃይሎች የካርቱም ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰሮችን ጨምሮ በርካታ ምሁራንን እያሰረ ነው፡፡

ሱዳን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ

 

ሱዳን ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በኋላ

ፕሬዚዳንት ኦማር አል በሽር በሱዳን ለአንድ ዓመት የሚዘልቀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቢያውጁም የአደባባይ ተቃውሞው እንደቀጠለ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

አዋጁ ቢታወጅም ሰዎች ለተቃውሞ ከመውጣት ባለመቆጠቸው፣ ከትላንት በስቲያ ለተቃውሞ ጎዳና መውጣትና መሰባሰብ መታገዱን ሮይተርስ አስነብቧል፡፡

በሱዳኗ ዋና ከተማ ካርቱም እንዲሁበአምዱ ራማንና የናይል ወንዝን ተከትለው በሚገኙ አካባቢዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች ጎዳና ወጥተዋል፡፡

ተፎካካሪ ፓርቲው ኡማ ናሽናል ፓርቲ፣ አመፅ አቀነባበሪዎችና የሱዳን የሙያ ማኅበራት የፕሬዚዳንቱን አዋጅ ያልተቀበሉ ሲሆን፣ ተቃውሞው ተጠናክሮ እንዲቀጥልና አልበሽር ከሥልጣን እንዲወርዱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

እሑድ የካቲት 17 ቀን 2011 ዓ.ም. የደኅንነት አካላት በተቃዋሚዎች ላይ ጥይት መተኮሳቸውና ሦስት ሰዎችን ማቁሰላቸውም ተሰምቷል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀ በኋላ የሱዳን ደኅንት አካላት የቤት ለቤት አሰሳ ጀምረዋል፡፡ የተቃዋሚ ፖለቲካ አቀንቃኞችና ተቃዋሚዎችም እየታደኑ ነው፡፡

በመቶዎች የሚቆጠሩና የታጠቁ ፒክአፕ  (በአካባቢው ነዋሪ በቀድሞዋ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ‹ታቸር› የተሰየሙ) መኪኖች በካርቱም ጎዳናዎች እየተዘዋወሩና ቅኝት እያደረጉ ነው፡፡

ተቃዋሚዎች በበኩላቸው ከዚህ ቀደምም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ እንደነበሩ በመግለጽ አዋጁ ምንም ለውጥ እንደማያመጣ እየተናገሩ ነው፡፡

ሱዳን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ

 

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አስፈላጊነት

ፕሬዚዳንት አልበሽር በኑሮ ውድነት ሰበብ ለተቀሰቀሰው ተቃውሞ ከሁለት ወር በኋላ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ የጎዳና ላይ አመፅ እንዲገታ ቢሉም፣ እስካሁን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ አልሆነም፡፡ ገዥው ናሽናል ኮንግረስ ፓርቲ በሰጠው መግለጫ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የፖለቲካ ስህተቶችን ለማረም ሳይሆን፣ በአገሪቱ የተከሰተውን የኢኮኖሚ ቀውስ ለማረጋጋት እንደሆነ አሳውቋል፡፡ አልበሽርም አዲስ ብሔራዊ መግባባት ላይ የሚያደርስና የታጠቁትን ጨምሮ ሁሉንም የፖለቲካ ኃይሎች ያሳተፈ አካሄድ እንደሚኖር አሳውቀዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...