‹‹ጣሊያን በጨረቃ ሲገሰግስ አድሮ እሰፈሬ ድረስ መጥቶ ገጠመኝ፡፡ አምላከ ኃያላን ረድቶኝ ፈጀሁት፡፡ ደስ ብሎኛል ደስ ይበልህ!››
ዳግማዊ አፄ ምኒልክ፣ ባሕር ተሻግሮ ድንበር አቋርጦ የመጣውን ወራሪውን የጣሊያን ሠራዊት የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም. በዓድዋ ጦርነት ድል ማድረጋቸውን አስመልክቶ በወሩ መጋቢት 23 ቀን 1888 ዓ.ም. ለፈረንሣዊው ሙሴ ሞንዶን ከጻፉለት የምሥራች ደብዳቤ የተገኘ ኃይለ ቃል ነው፡፡