ኢትዮጵያ ባሕር ተሻግሮ ድንበር አቋርጦ በመጣው ወራሪው የጣሊያን ሠራዊት ላይ በንጉሠ ነገሥቷ በዳግማዊ ምኒልክ ጠቅላይ አዝማችነት፣ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም. ዓድዋ ላይ በተደረገው ጦርነት ድል የተቀዳጀችበት 123ኛ ዓመት በታሪካዊው ቦታና በመላዋ ኢትዮጵያ ተከብሮ ውሏል፡፡ በጥቁሩ ዓለም አንፀባራቂ የሆነውን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ያስከበረው የዓድዋ ድል፣ ከታሰበባቸው መንገዶች አንዱ ወጣቶች ከአዲስ አበባ፣ ከሐረርና ከመቐለ ተነስተው በእግር ተጉዘው ዓድዋ ከተማ የደረሱበት ነው፡፡ ፎቶዎቹ በዓሉ ዓምና በአዲስ አበባ ከተማ በልዩ ልዩ መሰናዶዎች ሲከበር የተነሱ ናቸው፡፡