Monday, March 27, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የኢትዮጵያ ባንኮች ማኅበር ለሦስት ባለሙያዎች የዕውቅና ሽልማት ሰጠ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ባንኮች ማኅበር በባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ለበርካታ ዓመታት ሲያገለግሉ የነበሩና ከ16 የግል ባንኮች ውስጥ ትልልቅ የሚባሉትን ሦስት የግል ባንኮች በፕሬዚዳንትነት ሲመሩ ለነበሩ ባለሙያዎች ዕውቅና ሰጠ፡፡

ማኅበሩ በባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምሥጋና በማቅረብ ዕውቅና የሰጣቸው የቀድሞዎቹ የአቢሲኒያ፣ የወጋገንና የንብ ኢንተርናሽናል ባንኮች ፕሬዚዳንቶች ናቸው፡፡

 ሐሙስ የካቲት 21 ቀን 2011 ዓ.ም. በሒልተን ሆቴል በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ከማኅበሩ ዕውቅናና ሽልማት የተሰጣቸው የቀድሞ የአቢሲኒያ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉጌታ አስማረ፣ የቀድሞ የወጋገን ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ገብረ እግዚአብሔር አርዓያና የቀድሞ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ክብሩ ፎንዣ ናቸው፡፡ የባንኮች ማኅበር በባንክ ኢንዱስትሪውና ለማኅበሩ ያደረጉትን አስተዋጽኦ በማስታወስ ያበረከተውን ሽልማትና ማስታወሻ ለተሰናባቾቹ ፕሬዚዳንቶች የሰጡት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች