Tuesday, November 29, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ኪንና ባህልየሀገር ፍቅር ቴአትር ከሕዝብ በሚገኝ መዋጮ ሕንፃ ሊገነባ አቅዷል

  የሀገር ፍቅር ቴአትር ከሕዝብ በሚገኝ መዋጮ ሕንፃ ሊገነባ አቅዷል

  ቀን:

  በተመስገን ተጋፋውና በሔለን ተስፋዬ

  የሀገር ፍቅር ቴአትር ‹‹ትናንት፣ ዛሬ፣ ነገ›› በሚል መሪ ቃል በታሪካዊ ግቢው ከሕዝብና ከመንግሥት በሚገኝ መዋጮ ሕንፃ ሊገነባ ማቀዱን አስታውቋል፡፡ 84 ዓመታትን ያስቆጠረው ቴአትር ቤቱ፣ ነሐሴ 9 ቀን 2010 ዓ.ም. የባለ ይዞታ ካርታ ባለቤት መሆኑን የቴአትር ቤቱ የሰው ኃይል አስተዳደር ኃላፊ አቶ መምህር ጫሞ ገልጸዋል፡፡

  6,856 ካሬ ሜትር ላይ የሚገኘው የሀገር ፍቅር ቴአትር የይዞታውን ካርታ ካገኘ ጀምሮ፤ በፊት የነበሩትን፣ ጣሊያን የሠራቸውን፣ በቅርስነት ተቀምጠው የሚገኙ ከዘመኑ ጋር የሚሄዱ የቴአትር፣ የሙዚቃ፣ የኮንሰርት፣ የፊልምና የሥዕል ጋለሪዎችን እንዲሁም የኢትዮጵያ ባህል የሚገለጽበትን ሕንፃ ለመገንባት እንቅስቃሴ መጀመሩን አርቲስት መምህር ገልጸዋል፡፡

  የሕንፃውን ግንባታ አስመልክቶ ባለፈው ሳምንት በቴአትር ቤቱ በነበረው ውይይት፣ የቴአትር ቤቱ ግንባታ ምን ዓይነት ቦታ ላይ እንደሚያርፍና መንግሥት አሁን ባለው የገንዘብ አቅም የበኩሉን አስተዋጽ ስለማድረጉ ጥያቄ ተነስቷል፡፡

  የሕንፃውን ግንባታ ከከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር፣ ከገንዘብና ኢኮኖሚ፣ ከከተማው አስተዳደር ቢሮና ከኅብረተሰቡ ጋር በመሆን ለመገንባት ዕቅድ ላይ መሆናቸውን መምህር ጫሞ ገልጸዋል፡፡

  የሀገር ፍቅር ቴአትር ሐምሌ 11 ቀን 1927 ዓ.ም. ከዳግማዊ ምኒልክ ሐውልት ወረድ ብሎ በሚገኘው ከቢትወደድ ኃይለ ጊዮርጊስ ሕንፃ ሥር መመሥረቱን አርቲስት ዮሐንስ አፈወርቅ ስለቴአትር ቤቱ ባቀረበው ወፍ በረር ቅኝት ተናግሯል፡፡

  ቴአትር ቤቱ ወራሪው የጣሊያን ጦር 1888 ዓ.ም. ከዓድዋው ሽንፈት 40 ዓመታት በኋላ ኢትዮጵያን ድጋሚ ለመውረር በመጣበት ዋዜማ የተቋቋመ ሲሆን፣ ኢትዮጵያውያን በዘር፣ በጎሳ፣ በሃይማኖት፣ እንዲከፋፈሉ ጣሊያን የሠራውን ሴራ ለማምከንና በኅብረተሰቡ ውስጥ የነበረውን የተሳሳተ አመለካከት ለመቀየር ነበር የኢትዮጵያ ሀገር ፍቅር ማኅበር የተመሠረተው፡፡

  እንግሊዝ፣ ፈረንሣይና ጣሊያን በ1930 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ መሣሪያ እንዳይገባ በማድረጋቸው ኢትዮጵያ ፈተና ውስጥ በመግባቷ ወጣቱ ለአገሩ አንድ ላይ በመሆን ወኔና ተነሳሽነት እንዲኖረው ማኅበሩ የራሱን አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

  ቴአትር ቤቱም ሕዝቡን ለነፃነቱ እንዲታገል በስብከት፣ በዜማ፣ በሥዕል፣  በፉከራ፣ በቀረርቶና በመሳሰሉት ኪነ ጥበባዊ ሥራዎች ያነቃቃ ነበር፡፡ እነዮፍታሔ ንጉሤ፣ አገኘሁ እንግዳ፣ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ የመሳሰሉት ባለቅኔዎች በግጥምና በድርሰት ሕዝቡን ያነቃቁ ነበር፡፡

  ማኅበሩም ወደ ጦር ለሚዘምቱ የትጥቅና የስንቅ ድጋፍ እንዲደረግላቸው በወቅቱ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

  ጣሊያን በማይጨው ጦርነት በለስ ከቀናት በኋላ አዲስ አበባን ሚያዝያ 27 ቀን 1928 ዓ.ም. ይዛ የበላይነቷን መቆናጠጥ ስትጀምር የኢትዮጵያ ሀገር ፍቅር ማኅበር ከአሥር ወራት ተጋድሎ በኋላ እንቅስቃሴው ተቋርጧል፡፡ ገሚሱ የውስጥ አርበኛ ሲሆን፣ የቀረው ደግሞ ጫካ በመግባት የጣሊያንን ጦር መፈታተን ጀመረ፡፡ ጣሊያንም የማኅበር አባላቱን ማሳደድና ያገኘችውን የመግደል ድርጊቷን ቀጠለች፡፡

  ከአምስት ዓመታት የሕዝብ ተጋድሎ በኋላ ጣሊያን ኢትዮጵያን ለቆ ሲወጣ፣ የኢትዮጵያ ሀገር ፍቅር ማኅበር በአቶ መንገሻ ከፈላ አማካይነት ‹‹የወጣቶች ምንጭ ሀገር ፍቅር ማኅበር›› በመባል ሚያዝያ 5 ቀን 1933 ዓ.ም. በድጋሚ ለመቋቋም ችሏል፡፡

  ማኅበሩም ከዚህ በፊት የነበረውን የጣሊያን ግፍና ጭካኔን ለማስታወስ ሲሠራ ቆይቷል፡፡ በመጨረሻም በአቶ መኰንን ሀብተ ወልድ መሪነት በልዑል መኰንን ኃይለ ሥላሴ የበላይ ጠባቂነት ቴአትር ቤቱም አሁን በሚገኝበት ቦታ ላይ ሊመሠረት ችሏል፡፡  

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በችግር የተተበተበው የሲሚንቶ አቅርቦት

  ሲሚንቶን እንደ ግብዓት ተጠቅሞ ቤት ማደስ፣ መገንባት፣ የመቃብር ሐውልት...

  ‹‹የናይል ዓባይ መንፈስ›› በሜልቦርን

  አውስትራሊያ ስሟ ሲነሳ ቀድሞ የሚመጣው በተለይ በቀደመው ዘመን የባህር...

  ‹‹ልብሴን ለእህቴ››

  ለሰው ልጅ መኖር መሠረታዊ ፍላጎት ተብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ ልብስ...

  የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የምርመራ ውጤት እስከምን?

  በፍቅር አበበ የትምህርት ጥራትን፣ ውጤታማነትንና ሥነ ምግባርን ማረጋገጥ ዓላማ አድርጎ...